Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-23 12:49:23
አንድሪው ቴትና ወንድሙ በእስር እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ወሰነ!

አወዛጋቢና ጾተኛ የሚባለው አንድሪው ቴት እና ወንድሙ ትሪስታን በሮማኒያ በእስር እንዲቆዩ ፍርድ ቤቴ ብይን ሰጥቷል።ወንድማማቾቹ ለአራተኛ ወርም በእስር ይቆያሉ ተብሏል።አንድሪውና ትሪስታን በመድፈር፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና የተደራጀ የወንጀል ቡድን አቋቁመዋል በሚልም ክስ እየተመረመሩም ይገኛሉ።ሁለቱም ወንጀሎቹን አልፈጸምንም ሲሉ አስተባብለዋል።

የአንድሪው ቴት ጠበቆች ደንበኛቸው እስከ ሚያዝያ መጨረሻ ድረስ በእስር እንደሚቆይ ተናግረዋል።ቃለ አቀባያቸው ማቲያ ፔትሬስኩ ውሳኔው ቃል እንዳሳጣቸው ነው የተናገሩት።የወንድማማቾቹ ጠበቆች በቡካሬስት ረቡዕ ዕለት በነበረው ዝግ ችሎት ላይ አቃብያነ ህግ ምንም አዲስ ማስረጃ አለማቅረባቸውን ተናግረዋል።የደንበኞቻቸው ታዋቂነት በእስር እንዲቆዩ ለመወሰን የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ማቲያ ፔትሬስኩ እንዳሉት ዳኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአገር ሊወጡ ይችሉ ይሆን ወይም ለህዝብ ስርዓት አደጋ ደቅነዋል ለሚለው ክርክር በቀጥታ ምላሽ እንዲሰጡም ነው የተጠየቁት።ሆኖም ዳኛው በመጨረሻ ሁለቱም ወንድማማቾች እስከ ሚያዝያ ድረስ ለተጨማሪ 30 ቀናት በእስር እንዲቆዩ ወስኗል።የቀጠለው እስር በወንድማማቾቹ ላይ ከፍተኛ ጥላሽት እንደቀባቸውና ስማቸውን ለማደስ ዓመታት እንደሚወስድም ተናግረዋል።

በአሜሪካ የአንድሪው ቴት ጠበቃ በቅርቡ ደፍሮኛል ያለችውን ተጎጂ ከነቤተሰቧ የምታቀርበውን ክስ ካልተወችው በ300 ሚሊዮን ዶላር በስም ማጥፋት ክስ እንደሚመሰረትባት አስፈራርተዋታል ተብሏል።

[BBC]
@EthioipaNews
1.8K viewsedited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 09:24:25 ጌታቸው ረዳ

የሕወሃት ከፍተኛ አመራር ጌታቸው ረዳ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ሰሞኑን ያነሷቸው ቅሬታዎች በከፍተኛ ትኩረት እንደሚታዩ እና ማጣራት እንደሚደረግባቸው መናገራቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

የጦር ጉዳተኞቹ ለእነሱ ተብሎ የተገዛ የሕክምና አቅርቦት እየተሸጠ ስለመሆኑ ነግረውኛል ያለው ዜና ምንጩ፣፣ የጦር ጉዳተኞቹ የጉዳት ካሳ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውንም ጠቅሷል።

የጦር ጉዳተኞቹ ከፍተኛ የሆነ የምግብ፣ የሕክምናና የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው በሰላማዊ ሰልፍና ከጌታቸው ጋር ባደረጉት ውይይት መናገራቸው ተዘግቦ ነበር።

የጦር ጉዳተኞቹ፣ በመቀሌ አካባቢ ኩዊሃ እና ደጀን ሆስፒታል በተባሉ ሁለት ማገገሚያ ማዕከሎች የሚገኙ ናቸው።

@EthioipaNews
3.0K views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 12:21:45
የጠ/ሚ አብይ አህመድ " የመደመር ትውልድ" መጽሃፍ የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ላይ ከ609 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ!!!

ትናንት ምሽት በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በተደረገ የመደመር ትውልድ መጽሃፍ የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ላይ ከ609 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል፡፡

የመደመር ትውልድ መጽሃፍ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ እና ገቢ የማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የተካሄደው በገቢው የሶፍ ዑመር ዋሻ ልማት እና የቱሪስት መዳረሻ ቦታውን ምቹ ለማድረግ በማለም ነው።

በማስተዋወቂያ መርሐ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የተለያዩ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ባለሃብቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ስነ-ስርዓቱ በአባ ገዳዎች ምርቃት ተጀምሮ ፥ የመጽሃፉን ይዘት በተመለከተ አጠር ያለ ዳሰሳ በመምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ዮሴፍ ቤኮ እና ዶ/ር ታደሰ ሌንጮ ተደርጓል። መጽሃፉን የተለያዩ ባለሃብቶች እና ተቋማት በከፍተኛ ገንዘብ በመግዛት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፊርማ ያረፈበትን መጽሃፍ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እጅ ተቀብለዋል።

በዚህም በአጠቃላይ 609 ሚሊየን 220 ሺህ ብር ቃል መገባቱ ነው የተገለጸው፡፡

በስነ-ስርዓቱ መዝጊያ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፥ ˝ይህ መጽሃፍ የጠራ አስተሳሰብ ያለው ትውልድ በመገንባት ኢትየጵያን ወደ ብልፅግና መንገድ የሚመራና የያዘችውን መንገድ ለማስቀጠል የሚያግዝ ነው’’ ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ የወደፊት የሶፍ ዑመር ዋሻ አጠቃላይ ገፅታ ንድፍ በክልሉ የቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነጋ ወዳጆ ለታዳሚው ቀርቧል።

@EthioipaNews
5.1K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 12:16:03
ሰይጣን ቤት ታሸገ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ ታሽገዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች ታሽገዋል::

በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከ100 በላይ የሺሻ ዕቃዎች ፣ በርካታ መዋሰሎች፣ ከ 6 በላይ ሀሺሽ የያዙ እቃዎች እንዲሁም በወቅቱ በቦታው የነበሩ ከ 68 በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን እና ወጣቱን በዚህ እኩይ ድርጊት ላይ እንዲሳተፍ ሲያደርጉ የቆዩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዉለዋል ሲል ከተማ መስተዳደሩ ገልፇል።

@EthioipaNews
4.4K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 09:05:23
በረከት ገበሬዋ በሚል ስም የምትታወቀው ባለሀብት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "የመደመር ትውልድ"መጽሀፍን በ50 ሺህ ዩሮ ገዝታለች!!

በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፈውን "የመደመር ትውልድ" መጽሀፍ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቂያ መርሀ ግብር ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ እየተከናወነ ነው።

በመርሀግብሩ ላይ የተገኘችው በረከት ገበሬዋ በሚል ስም የምትታወቀውና በግብርና ላይ የተሰማራችው ባለሀብት በረከት ወርቁ መጽሀፉን በ50 ሺህ ዩሮ በመግዛት ዓላማውን ደግፋለች።

በረከት ለኢፕድ በሰጠችው አስተያየት፤ እንደተናገረችው፤ በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ አማካኝነት የተፃፈው የመደመር ትውልድ መፅሐፍ ሽያጭ የሚውልበትን አላማ መደገፍ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው ብላለች። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚችለው መጠን ለመፅሀፉ አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባዋል ያለችው በረከት ትውልድን የሚያቀራርብ ፍቅርን የሚያጎለብት ነውና ይህን መርዳት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው ብላለች።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚህ ከባድ ጊዜ ይህን መጽሀፍ እያሳተሙ ለበጎ ተግባር ስለሚያውሉ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እመኝላቸዋለሁ ያለችው በረከት፤ በየክልሉ ያሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ስፍራዎች ስለሚውል መጽሀፉን መግዛት አማራጭ የሌለው መልካም ስራ መሆኑንም አክላለች።

(ኢፕድ)
@EthioipaNews
4.6K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 21:35:13 ረመዳን ሙባረክ

በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ ባለመታየቷ የረመዳን ወር ሐሙስ መጋቢት 14 አንድ ብሎ እንደሚጀምር ታውቋል።

@EthioipaNews
5.2K views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 21:32:21
ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) አረፉ

በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ (ዶ/ር) በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋ እና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። 

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ ከሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ። 

ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ መለየታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት ዘግቧል።

@EthioipaNews
5.3K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 09:04:37
ዜና እረፍት!!

ታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንስቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሄር ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል፡፡

ዶ/ር ተወልደብርሃን በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ አቅራቢያ ባለችው ‹‹አዲ-ስላም›› የተሰኘች የገጠር መንደር የተወለዱ ሲሆን ፣ በቀለም ትምህርት ገፍተው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1955 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተቀበሉ በኋላ የሁለተኛ እና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከዌልስ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ናቸው፡፡

በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ አገልግሎት የተከበረ ሥም ያላቸው ዶክተር ተወልደ በዘርፉ ላደረጉት ምርምርና በጉዳዩ ዙሪያ ከፍተኛ ግንዛቤ እንዲፈጠር ላደረጉት ጥረት በፈረንጆቹ 2000 Right Livlihood Award ሽልማት አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በፈረንጆቹ 2006 ዓመት የተባበሩት መንግሥታት በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጠውን Champions of the Earth ሽልማት አግኝተዋል፡፡ የተማሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በ1997 የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷቸዋል፡፡

ዶ/ር ተወልደ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ፋኩልቲ ዲን ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ ከ1975 እስከ 1983 በነበረው ዘመን ደግሞ የአስመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላ ለብዙ ዓመታት በሚታወቁበት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡

ዶክተር ተወልደ ገብረእግዚአብሔር የደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ወንድም መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ምንጭ :- ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ
@EthioipaNews
1.1K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 09:05:12
አዲሱ የዓባይ ድልድይ የመገጣጠሚያ ሙሌት ሥራ ትናንት ምሽት ተጠናቀቀ።

በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት በሁለቱም አቅጣጫ ሲካሄድ የነበረው ወንዙ መካከል ላይ የመገጣጠሚያ ሙሊት ትናንት ምሽት ተጠናቋል።

ፕሮጄክቱ 94 ነጥብ 15 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ሰኔ 30 ላይ ለትራፊክ ክፍት ይሆናል ተብሏል። የድልድዩ ግንባታ ሲጠናቀቅ በአንድ ጊዜ ስድስት መኪኖችን ማሳለፍ የሚያስችልም ነው።

@EthioipaNews
2.0K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 13:34:45
አላማጣ

"አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም" የራያ አላማጣ ሰልፈኞች
ዛሬ በአላማጣ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ!!

@EthioipaNews
3.3K viewsedited  10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ