Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction
የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.69K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-18 07:42:28 በስራ ላይ ከሚገጥሙን አንዳንድ ከውል አስተዳደር ጋር የተያያዙ ነገሮችን በጥያቄ መልክ እንይ፦

1) ስራ ለመስራት የተዋዋለ ተቋራጭ ድርጅት ሊከፈለው የሚገባ ክፍያ አንሶ እንዲከፈለው ቢደረግ የሚሰራውን ስራ ሊያቆም ይችላል?
2) በተቆጣጣሪ መሀንዲስ የተፈቀደ የኮንትራት ጊዜ ማራዘሚያ ውል ሰጪው ድርጅት (Client) ሊከለክል ይችላል?
3) ተቆጣጣሪ መሀንዲስ የተረጋጋጠ የዕዳ (Negative) የክፍያ ሰርተፍኬት መስጠት ይችላል?

Explanation :-

ከላይ ተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮች አንድ በአንድ እንመልከት።
1) Where a sum due under a contract is not paid in full by the final date for payment and no effective notice to withhold payment has been given, the person to whom the sum is due has the right (without prejudice to any other right or remedy) to terminate the performance of his obligations under the contract to the party by whom payment ought to have been made.  የውል ሰጪው ድርጅት/ግለሰብ (Client) ተቋራጭ ድርጅቱ ስላልተከፈለ ክፍያ የሚገልፅ ደብዳቤ ደርሶት በ45 ቀን ውስጥ ተገቢውን ክፍያ ያልፈፀመ እንደሆነ  ተቋራጭ ድርጅቱ ከ30 ቀን ያላነሰ ጊዜ በውስጥ ውሉን ስለማቋረጥ የሚገልፅ ደብዳቤ በመስጠት ውሉን ሊያቋጥ ይችላል፡፡
2) በመደበኛ የግንባታ ውሎች መሰረት የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄዎችን አግባብነት ያላቸውን መስፈርቶችን በማረጋገጥ እና ውል ሰጪው እንዲያውቀው በማድረግ መስጠት ይችላል፡፡ ይህንን ውሳኔ በባለቤት በኩል መከልከል የሚያስችለው የውል አግባብ የለም፡፡
3) በክፍያ ወቅት ከተሰራው የስራ መጠን በላይ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሊከፈል ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ወቅት ባለቤት እላፊ ተከፍሏ ያለውን መጠን ተቋራጭ ድርጅቱ በ45 ቀናት ውስጥ ተመላሽ እንዲያደርግ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ይገልፃሉ፡፡ ይህ ሁኔታ ተፈፃሚ በማይሆንበት ባለቤት ወለዱን ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ ክፍያውን እንዲያገኝ የውል ሁኔታው ያስገድዳል፡፡

https://t.me/ethioengineers1
242 viewsENG Sintayehu Melese, edited  04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 02:43:04 እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

@BeGetEngineering
1.4K viewsBelay #1, 23:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 18:12:16
" የ24 ሰዓት የጥገና ሥራ እየተካሄደ ነው " - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

የመደርመስ አደጋ የደረሰበትን የጀማ  ወንዝ  የብረት ድልድይ  ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል የ24 ሰዓት የጥገና ሥራ እካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገልጿል።

አንድ መቶ ሜትር ርዝማኔ  ያለው የብረት ድልድይ ትላንት መደርመሱ ይታወቃል።

የአደጋው  ምክንያት ተከታትለው ይጓዙ የነበሩ ሁለት ከባድ የጭነት መኪኖች በአንድ ጊዜ በደልድዩ  ላይ በማለፋቸው ነው።
 
ድልድዩን  ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የኮከብ መስክ አለም ከተማ  መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን የሚያካሂደው “CSCEC ፦China  state construction engineering  company ” የተባለው ተቋራጭ  አስፈላጊውን  የጥገና ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

የመንገድ ተጠቃሚው ሕብረተሰብ ድልድዩ በአጭር ጊዜ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪ ተላልፏል።

ከዚህ በተጨማሪ ከተፈቀደ የክብደት በላይ መጫን በመንገድ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት መንገዶችን ከብልሽት ለመጠበቅ የመንገድ ተጠቃሚዎች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ተብሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
የፎቶ ባለቤት ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር


ስራውን የሰራው የውጭ ድርጅት ከሆነ የሰው ነፍስ ካልጠፋ (ቢጠፋ እንኮ) በቃ አይጠየቅም አይደል ..... ethiopia

https://t.me/ethioengineers1
2.1K viewsENG Sintayehu Melese, 15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 20:57:30 ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተሰጠ ማሳሰቢያ
ከአዲስ አበባ - ሙከጡሪ አለም ከተማ - ደጎሎ መስመር ከሙከጡሪ 72.3 ኪ.ሜ. እርቀት ላይ የሚገኘው የጀማ ወንዝ ድልድይ ከተወሰነላቸው የክብደት መጠን በላይ በጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ሳቢያ ጉዳት ደርሶበታል። በመሆኑም ይህ ድልድይ በአሁኑ ወቅት ለተሽከርካሪዎች አገልግሎት መስጠት የማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል።

ይህንን ድልድይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ለማብቃት እንዲያስችል አስፈላጊውን የጥገና ሰራ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሚከናወን ይሆናል። በመሆኑም የዚህ መስመር ተጠቃሚዎች ለድልድዩ አስፈላጊውን የጥገና ስራ ተከናውኖ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድረስ ሌሎች አማራጮችን እንድትጠቀሙ በማክበር እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
2.9K viewsENG Sintayehu Melese, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 20:06:56
ሰሜን ሸዋ ዞን የጀማ ድልድይ በዛሬው ዕለት መሰበሩ ተሰምቷል።

https://t.me/ethioengineers1
3.0K viewsENG Sintayehu Melese, edited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 14:28:42
ላለፉት 4ወራት ስናሰለጥናቸዉ የነበሩ  ከ120 በላይ የምህንድስና ባለሙያዎችን ሚያዝያ 29/2015 ዓ.ም የምናስመርቅ ሲሆን ይህም ዘርፉ ላይ ላሉ ትልልቅ የምህንድስና ካምፓኒዎች በትልቁ አጋዥ ይሆናሉ ብለን እናምናለን። ለጨረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን :-
አዲስ የትምህርት ፕሮግራም ሚያዝያ 2/2015 የሚጀምር ከላይ ተያይዟል።
New Schedule Starting April 10/2023.
+251995016195 / 0116686857
https://t.me/BeGetEngineering
1.8K viewsBelay #1, edited  11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 18:32:42 በአዲስ አበባ ለህንጻ ግንባታ የተቆፈረ አፈር ተንዶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:19 ሰዓት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ልዩ ቦታዉ መነን  ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ አደጋ መድረሱን የእሳት አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አደጋው በግንባታ ላይ ባለህንጻ  በስራ ላይ የነበሩ 2 ሰራተኞች አፈር ተንዶባቸዉ ህይወታቸዉ አልፏል።

አደጋዉ  መድረሱ ሪፖርት የተደረገለት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ  ሰራተኞች  የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን  እንዲሁም ጸጥታ አካላት በመተባበር የሟቾችን አስከሬን ማዉጣት ስራ እየሰሩ ሲሆን የአንደኛው አስከሬን መገኘቱን የኮሚሽኑ  የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ  ተናግረዋል።
ሁለተኛዋ የአስክሬን ፍለጋ በአሁኑ ሰዓት መቀጠሉን አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል።

(ብስራት ራዲዬ—በትግስት ላቀው
)

https://t.me/ethioengineers1
1.5K viewsENG Sintayehu Melese, edited  15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 22:54:14
የአዲሱ የዓባይ ድልድይ የመገጣጠሚያ ሙሊት ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

ከዓባይ ወንዝ በሁለቱም አቅጣጫ ሲሠራ የቆየውን ድልድይ የመጨረሻ የማገናኘት የሙሊት ሥራ በአሁኑ ሰዓት እየተከናወነ ነው። ከሁለቱም አቅጣጫ ሲሠራ የነበረውን የድልድይ ግንባታ የመገጣጠምን ሙሌት አስመልክቶም የማብሠሪያ ሥነ ሥርዓት በቦታው እየተካሄደ ነው።

በማብሠሪያ ሥነ ሥርዓቱ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)ን ጨምሮ የፕሮጄክቱ መሐንዲሶች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የአዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ምክትል ተጠሪ መሐንዲስ ፍቅረሥላሴ ወርቁ 3 መቶ 80 ሜትር የሚረዝመው አዲሱ የዓባይ ድልድይ ከሁለቱም በኩል ሲሠራ ቆይቶ ዛሬ ምሽት የመገጣጠሚያ ሙሊት ሥራው እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ድልድዩ ከሁለቱም በኩል መገጣጠም የድልድዩን የላይኛውን አካል ማጠናቀቅን የሚያበሥር መሆኑንም ገልፀዋል። አዲሱ የዓባይ ድልድይ በዚህ ዓመት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአግልግሎት ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።


https://t.me/ethioengineers1
1.6K viewsENG Sintayehu Melese, 19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 22:54:13
Core structure (አንኳር የመዋቅር አይነት)

ረዣዥም እና ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን ለመስራት በተለመደው እና በመደበኛው ፍሬም ስትራክቸር መስራት economicalም አይደለም adequateም አይደለም። ስለዚህ የ20ኛው ክፍለዘመን የምህንድስና ጠበብቶች Core structureን አስተዋወቁ።

Core structure ማለት shear wall ( በ አርማታ እና በ ፌሮ የሚሰራ ግንብ ሆኖ የጎንዮሽ ጫናን (lateral load) በበቂ ሁኔታ የሚከላከል ከ ሌሎች ፍሬም መዋቅሮች የተሻለ stability ያለው ነው።
ይህ የመዋቅር እይነት ሾጠጥ (slender) ያለ ነው። ብዙ ጊዜ የቦታውን ይዞታ ኮንክሪት ብቻ ከመከመር መዋቅራዊ ይዘቱም እንዳለ የ አሳንሰር አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል የከተማታችን ብንወስድ የ ህብረት ባንክ ዋና ፅህፈት ቤት ህንፃ (elevator station) የ ኮር ስትራክቸር አንዱ ማሳያ ነው። ብዙ ጊዜ core structure at the centroid of the plan of the building እንዲሆን ይመከራል።


https://t.me/ethioengineers1
1.5K viewsENG Sintayehu Melese, 19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 07:22:10
ከተማዋን በክለብ ቤት መብራት እና ፖስተር አለቅጥ ሊያሳምሯት የሚጥሩት አካሎች ምነው መንቀሳቀሻ ያሳጣውን የከተማዋን የፍሳሽ መስመር ለማስተካከል ሌተቀን ቢጥሩ??

Via:- driving in addis
https://t.me/ethioengineers1
1.5K viewsENG Sintayehu Melese, 04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ