Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ለህንጻ ግንባታ የተቆፈረ አፈር ተንዶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ በአዲስ አበባ ከ | Ethio Construction

በአዲስ አበባ ለህንጻ ግንባታ የተቆፈረ አፈር ተንዶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:19 ሰዓት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ልዩ ቦታዉ መነን  ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ አደጋ መድረሱን የእሳት አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አደጋው በግንባታ ላይ ባለህንጻ  በስራ ላይ የነበሩ 2 ሰራተኞች አፈር ተንዶባቸዉ ህይወታቸዉ አልፏል።

አደጋዉ  መድረሱ ሪፖርት የተደረገለት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ  ሰራተኞች  የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን  እንዲሁም ጸጥታ አካላት በመተባበር የሟቾችን አስከሬን ማዉጣት ስራ እየሰሩ ሲሆን የአንደኛው አስከሬን መገኘቱን የኮሚሽኑ  የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ  ተናግረዋል።
ሁለተኛዋ የአስክሬን ፍለጋ በአሁኑ ሰዓት መቀጠሉን አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል።

(ብስራት ራዲዬ—በትግስት ላቀው
)

https://t.me/ethioengineers1