Get Mystery Box with random crypto!

የአዲሱ የዓባይ ድልድይ የመገጣጠሚያ ሙሊት ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው። ከዓባይ ወንዝ በሁለቱ | Ethio Construction

የአዲሱ የዓባይ ድልድይ የመገጣጠሚያ ሙሊት ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

ከዓባይ ወንዝ በሁለቱም አቅጣጫ ሲሠራ የቆየውን ድልድይ የመጨረሻ የማገናኘት የሙሊት ሥራ በአሁኑ ሰዓት እየተከናወነ ነው። ከሁለቱም አቅጣጫ ሲሠራ የነበረውን የድልድይ ግንባታ የመገጣጠምን ሙሌት አስመልክቶም የማብሠሪያ ሥነ ሥርዓት በቦታው እየተካሄደ ነው።

በማብሠሪያ ሥነ ሥርዓቱ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)ን ጨምሮ የፕሮጄክቱ መሐንዲሶች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የአዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ምክትል ተጠሪ መሐንዲስ ፍቅረሥላሴ ወርቁ 3 መቶ 80 ሜትር የሚረዝመው አዲሱ የዓባይ ድልድይ ከሁለቱም በኩል ሲሠራ ቆይቶ ዛሬ ምሽት የመገጣጠሚያ ሙሊት ሥራው እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ድልድዩ ከሁለቱም በኩል መገጣጠም የድልድዩን የላይኛውን አካል ማጠናቀቅን የሚያበሥር መሆኑንም ገልፀዋል። አዲሱ የዓባይ ድልድይ በዚህ ዓመት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአግልግሎት ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።


https://t.me/ethioengineers1