Get Mystery Box with random crypto!

' የ24 ሰዓት የጥገና ሥራ እየተካሄደ ነው ' - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመደርመስ አ | Ethio Construction

" የ24 ሰዓት የጥገና ሥራ እየተካሄደ ነው " - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

የመደርመስ አደጋ የደረሰበትን የጀማ  ወንዝ  የብረት ድልድይ  ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል የ24 ሰዓት የጥገና ሥራ እካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገልጿል።

አንድ መቶ ሜትር ርዝማኔ  ያለው የብረት ድልድይ ትላንት መደርመሱ ይታወቃል።

የአደጋው  ምክንያት ተከታትለው ይጓዙ የነበሩ ሁለት ከባድ የጭነት መኪኖች በአንድ ጊዜ በደልድዩ  ላይ በማለፋቸው ነው።
 
ድልድዩን  ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የኮከብ መስክ አለም ከተማ  መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን የሚያካሂደው “CSCEC ፦China  state construction engineering  company ” የተባለው ተቋራጭ  አስፈላጊውን  የጥገና ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

የመንገድ ተጠቃሚው ሕብረተሰብ ድልድዩ በአጭር ጊዜ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪ ተላልፏል።

ከዚህ በተጨማሪ ከተፈቀደ የክብደት በላይ መጫን በመንገድ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት መንገዶችን ከብልሽት ለመጠበቅ የመንገድ ተጠቃሚዎች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ተብሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
የፎቶ ባለቤት ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር


ስራውን የሰራው የውጭ ድርጅት ከሆነ የሰው ነፍስ ካልጠፋ (ቢጠፋ እንኮ) በቃ አይጠየቅም አይደል ..... ethiopia

https://t.me/ethioengineers1