Get Mystery Box with random crypto!

ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተሰጠ ማሳሰቢያ ከአዲስ አበባ - ሙከጡሪ አለም ከተማ - ደጎሎ | Ethio Construction

ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተሰጠ ማሳሰቢያ
ከአዲስ አበባ - ሙከጡሪ አለም ከተማ - ደጎሎ መስመር ከሙከጡሪ 72.3 ኪ.ሜ. እርቀት ላይ የሚገኘው የጀማ ወንዝ ድልድይ ከተወሰነላቸው የክብደት መጠን በላይ በጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ሳቢያ ጉዳት ደርሶበታል። በመሆኑም ይህ ድልድይ በአሁኑ ወቅት ለተሽከርካሪዎች አገልግሎት መስጠት የማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል።

ይህንን ድልድይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ለማብቃት እንዲያስችል አስፈላጊውን የጥገና ሰራ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሚከናወን ይሆናል። በመሆኑም የዚህ መስመር ተጠቃሚዎች ለድልድዩ አስፈላጊውን የጥገና ስራ ተከናውኖ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድረስ ሌሎች አማራጮችን እንድትጠቀሙ በማክበር እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር