Get Mystery Box with random crypto!

በስራ ላይ ከሚገጥሙን አንዳንድ ከውል አስተዳደር ጋር የተያያዙ ነገሮችን በጥያቄ መልክ እንይ፦ | Ethio Construction

በስራ ላይ ከሚገጥሙን አንዳንድ ከውል አስተዳደር ጋር የተያያዙ ነገሮችን በጥያቄ መልክ እንይ፦

1) ስራ ለመስራት የተዋዋለ ተቋራጭ ድርጅት ሊከፈለው የሚገባ ክፍያ አንሶ እንዲከፈለው ቢደረግ የሚሰራውን ስራ ሊያቆም ይችላል?
2) በተቆጣጣሪ መሀንዲስ የተፈቀደ የኮንትራት ጊዜ ማራዘሚያ ውል ሰጪው ድርጅት (Client) ሊከለክል ይችላል?
3) ተቆጣጣሪ መሀንዲስ የተረጋጋጠ የዕዳ (Negative) የክፍያ ሰርተፍኬት መስጠት ይችላል?

Explanation :-

ከላይ ተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮች አንድ በአንድ እንመልከት።
1) Where a sum due under a contract is not paid in full by the final date for payment and no effective notice to withhold payment has been given, the person to whom the sum is due has the right (without prejudice to any other right or remedy) to terminate the performance of his obligations under the contract to the party by whom payment ought to have been made.  የውል ሰጪው ድርጅት/ግለሰብ (Client) ተቋራጭ ድርጅቱ ስላልተከፈለ ክፍያ የሚገልፅ ደብዳቤ ደርሶት በ45 ቀን ውስጥ ተገቢውን ክፍያ ያልፈፀመ እንደሆነ  ተቋራጭ ድርጅቱ ከ30 ቀን ያላነሰ ጊዜ በውስጥ ውሉን ስለማቋረጥ የሚገልፅ ደብዳቤ በመስጠት ውሉን ሊያቋጥ ይችላል፡፡
2) በመደበኛ የግንባታ ውሎች መሰረት የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄዎችን አግባብነት ያላቸውን መስፈርቶችን በማረጋገጥ እና ውል ሰጪው እንዲያውቀው በማድረግ መስጠት ይችላል፡፡ ይህንን ውሳኔ በባለቤት በኩል መከልከል የሚያስችለው የውል አግባብ የለም፡፡
3) በክፍያ ወቅት ከተሰራው የስራ መጠን በላይ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሊከፈል ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ወቅት ባለቤት እላፊ ተከፍሏ ያለውን መጠን ተቋራጭ ድርጅቱ በ45 ቀናት ውስጥ ተመላሽ እንዲያደርግ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ይገልፃሉ፡፡ ይህ ሁኔታ ተፈፃሚ በማይሆንበት ባለቤት ወለዱን ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ ክፍያውን እንዲያገኝ የውል ሁኔታው ያስገድዳል፡፡

https://t.me/ethioengineers1