Get Mystery Box with random crypto!

በግንባታ ወቅት መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች በአሁኑ ወቅት የግንባታው ዘርፍ ለቡዙ ዜጎች የስራ | Ethio Construction

በግንባታ ወቅት መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች

በአሁኑ ወቅት የግንባታው ዘርፍ ለቡዙ ዜጎች የስራ እድልን በመፍጠር ለአገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ይሁንና አብዛኛው የሕንጻ ግንባታዎች በህንጻ ህጉ መሰረት በግንባታ ወቅት ማደረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ባለማድረጋቸው የተነሳ በሰው ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ከፈተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የሕዝብ ጤንነትና ደህንነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የሕንፃ ግንባታ ወይም የሕንፃ ግንባታ ማሻሻያና የአገልግሎት ለውጥን በተመለከተ በሀገሪቱ በአጠቃላይ ተፈፃሚ የሚሆን ዝቅተኛውን ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አገራችንም የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 እና እሱን ለማስፈጸም የወጣ የሚንስትሮች ምክር ቤት የሕንጻ ደንብ 243/2003 ወጥቶ በስራ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ጽሁፍ በህጉ ላይ ስለተደነገገው እና በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባ ጥንቃቄ እና ይህንኑ ጥንቃቄ ያለማድረግ ስለሚያስከትለው ሀላፈነት በአጭሩ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

የግንባታ ምንነት እና የሕንፃ አይነቶች በአገራችን ህግ
የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 በአንቀጽ 2 ስር ለተለያዩ ቃላቶች ትርጓሜን የሚሰጥ ሲሆን ይህም፡-
“ግንባታ” ማለት አዲስ ሕንፃ መገንባት ወይም ነባር ሕንፃን ማሻሻል ወይም አገልግሎቱን መለወጥ ነው በማለት ትሩገጓሜ የሰተው ሲሆን፣

“ሕንፃ” ማለት ለመኖሪያ፣ ለቢሮ፣ ለፋብሪካ ወይም ለማናቸውም ሌላ አገልግሎት የሚውል ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ግንባታ ነው፤ በማለት ይገልጸዋል፡፡

የሕንፃ አይነቶች
የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ በአጠቃላይ በአገራችን የሚገኘውን የህንጻ አይነቶችን በሶስት የሚመድብ ሲሆን ይህም፡-

1ኛ ምድብ ‘ሀ’ ሕንፃ
ማለት በሁለት የኮንክሪት ወይም የብረት ወይም ሌሎች ስትራክቸራል ውቅሮች መካከል ያለው ርቀት 7 ሜትር ወይም ከዚያ በታች የሆነ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ወይም ማናቸውም ከሁለት ፎቅ በታች የሆነ የግል መኖሪያ ቤት ነው፡፡

2ኛ ምድብ ‘ለ’ ሕንፃ
ማለት በሁለት የኮንክሪት ወይም የብረት ወይም ሌሎች ስትራክቸራል ውቅሮች መካከል ያለው ርቀት ከ7 ሜትር በላይ የሆነ ወይም ባለሁለት ፎቅና ከሁለት ፎቅ በላይ የሆነና በምድብ ‘ሐ’ የማይሸፈን ሕንፃ ወይም በምድብ ‘ሀ’ የተመደበ እንደሪል ስቴት ያለ የቤቶች ልማት ነው፡፡

3ኛ ምድብ ‘ሐ’ ሕንፃ
ማለት የሕዝብ መገልገያ ወይም ተቋም ነክ ሕንፃ፣ የፋብሪካ ወይም የወርክሾፕ ሕንፃ ወይም ከመሬት እስከ መጨረሻው ወለል ከፍታው ከ12 ሜትር በላይ የሆነ ማናቸውም ሕንፃ ነው፡፡

በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች
የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 እና ይህን ለማስፈጸም በወጣው የሚንስትሮች ምክር ቤት የሕንጻ ደንብ ቁጥር 243/2003 መሰረት በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች በመዘርዘር የሚያስቀምጡ ሲሆኑ ይህም፡-

 ማንኛውም ግንባታ በግንባታው አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን፣ የግንባታው ሠራተኞችን፣ የሌሎች ግንባታዎችን ወይም ንብረቶችን ደህንነት በማያሰጋ መንገድ ዲዛይን መደረግና መገንባት አለበት፡፡

 ማንኛውም የሕንፃ ባለቤት አዲስ የሕንፃ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት በአካባቢው ቀደም ብሎ የተሠሩ ሕንፃዎችን እና የመሠረተ ልማት አውታሮችን አገልግሎት የሚያውኩ፣ የአካባቢውን ወይም አዋሳኙን ደህንነትና ጤንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ እና የትራፊክ ፍሰትን የሚያስተጓጉሉ ሁኔታዎችን ማስወገድና ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡

 ከግንባታ ጋር የተያያዘ ቁፋሮ የማንኛውንም ንብረት ወይም አገልግሎት ደህንነት ጉዳት ላይ የሚጥል ሲሆን የግንባታ ቦታው ባለቤት የንብረቱን ወይም የአገልግሎቱን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡ ለሚሠሩ ግንባታዎች የሕንፃው ባለቤት የሚከተላቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በጽሁፍ እንደአስፈላጊነቱም በዲዛይንና በዝርዝር ትንታኔ በማስደገፍ ለሕንፃ ሹሙ በማቅረብ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

 አጎራባቹ የቴክኒክ ዕውቀት ካለው በራሱ፣ ከሌለው ደግሞ በሚወክለው ባለሙያ ገንቢው የሚያደርገው የቅድሚያ ጥንቃቄ ዝግጅት ንብረቱን ከአደጋ መከላከል መቻሉ እንዲገለጽለት መጠየቅ እና በግንባታም ወቅት ከግንባታው ባለቤት ጋር በመነጋገር መከታተል ይችላል፡፡
 የተቆፈረው ጉድጓድ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ወይም በጉድጓዱ ውስጥ መሠረት በሚገነባበት ጊዜ ባለቤቱ ወይም ቁፋሮውን ያካሄደው ሰው ጉድጓዱን ለደህንነት በማያሰጋ ሁኔታ መጠበቅ አለበት፡፡

 ከግንባታ ጋር የተያያዘ ቁፋሮ የማንኛውንም ንብረት ወይም አገልግሎት ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል መሆኑ ሲገመት የግንባታ ቦታው ባለቤት በቅድሚያ የመከላከያ ዘዴዎችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለከተማው አስተዳደር ወይም ለተሰየመው አካል በማቅረብ የፅሁፍ ፈቃድ ማግኘት አለበት፡፡

 ማንኛውም አዲስ የሚገነባ ህንፃ መሠረት ጭነት በነባር መሠረቶች፣ የአገልግሎት መስመሮች ወይም ሌሎች ሥራዎች ላይ ችግር የሚፈጥር መሆን እንደሌለበት በህጉ ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎችን አለማድረግ ሚያስከትልው ሀላፊነት

በግንባታ ወቅት መደረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ባለማድርግ የሚደርስን ጉዳት በተመለከተ የፍትሐብሄር ተጠያቂነት እንዳለ ሆነ በህንጻ አዋጅ እና ደንቡ ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ የግንባታ ሥራ ፈቃድን በሚሰጡ የመንግሥት ኃላፊዎች እና ይህንኑ እንዲያከናውኑ ሃላፊነት በተሰጣቸው ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች፣ በተመዘገቡ ባለሙያዎች ወይም ሥራ ተቋራጮች፣ አንዲሁም በግንባታ ባለቤቶች ለሚፈፀሙ ጥፋቶች እንደ ሁኔታው አስተዳደራዊ መቀጮ እና የወንጀል ተጠያቂነት እንዳለባቸው በህጉ ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

አስተዳደራዊ መቀጮ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሕንጻ ደንብ ቁጥር 243/2003 ላይ የወንጀልና የፍትሐ ብሔር ኃላፊነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁን ወይም ይህንን ደንብ በሚተላለፍ የግንባታ ባለቤት ላይ የከተማው አስተዳደር ወይም የተሰየመው አካል እንደ ሕንፃው ደረጃ የገንዘብ መቀጮን ይጥላል፡፡ ለአብነትም በግንባታ ወቅት መወሰድ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ሳይወስድ በምድብ ለ ህንጻ ስር የሚመደብ ህንጻ መገንባት በ3000 (ሶስት ሺ) ብር የገንዘብ መቀጮ ያሚያስቀጣ ሲሆን የሚሰራው ህንጻ ምድብ ሐ ህንጻ ሲሆን ቅጣቱ በ5000 (አምስት ሺ) ብር የገንዘብ መቀጮ ይሆናል በማለት ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ሌላው የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 አንቀጽ 56 መሰረት በአዋጁ ላይ በተመለከቱት የህግ መጣስ ተግባሮች ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ የተመዘገበ ባለሙያ ወይም ሥራ ተቋራጭ በፍርድ ከተወሰነበት የእሥራት ቅጣት በተጨማሪ ጥፋተኛው ከአምስት ዓመት ጀምሮ ጥፋተኛ በተባለበት አንቀጽ እስከ ተመለከተው ከፍተኛ የእሥራት ዘመን ድረስ የሙያ ወይም የሥራ ፈቃዱ ይታገዳል በማለት አስቀምጧል፡፡

የወንጀል ተጠያቂነት