Get Mystery Box with random crypto!

የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 መሰረት የአዋጁን ድንጋጌዎች በመተላለፍ የግንባታ ሥራ ፈቃድን በ | Ethio Construction

የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 መሰረት የአዋጁን ድንጋጌዎች በመተላለፍ የግንባታ ሥራ ፈቃድን በሚሰጡ የመንግሥት ኃላፊዎች እና ይህንኑ እንዲያከናውኑ ሃላፊነት በተሰጣቸው ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች፣ በተመዘገቡ ባለሙያዎች ወይም ሥራ ተቋራጮች፣ እንዲሁም በግንባታ ባለቤቶች የሚፈፀሙ ጥፋቶች እንደሁኔታው ከ6 ወር ጀምሮ እስከ 15 አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ500 (አምስት መቶ) ብር እስከ 50000 (ሀምሳ ሺ) ብር የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በ1996 የወጣው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 501 የህንጻ ስራ ደንቦችን መጣስ በሚል ርእስ ስር ማንም ሰው ማንኛውንም አይነት የህንጻ ስራ ወይም የህንጻ ማፍረስ ስራ ሲቆጣጠር፣ ሲመራ ወይም ሲፈጽም በህግ የተደነገገውን ወይም በህንጻ ስራ ሙያ ወይም ልምድ የሚሰራባቸውን የጥንቃቄ ደንቦችን አስቦ በመጣስ የህዝብን ደህንነት ወይም የሰዎችን ሕይወት፣ ጤንነት ወይም አካል ወይም የሌላውን ሰው ንብረት አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ ከ3 ወር በማያንስ ቀላል እስራት እና በመቀጮ የሚቀጣ ሲሆን ወንጀሉ የተፈጸመው በቸልተኝነት እንደ ሆነ ከ1 አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና በመቀጮ እንደሚያስቀጣ ያመለክታል፡፡

በአጠቃላይ ማንኛውም የሕንፃ ግንባታ ሥራ በሚከናወንበት ወቅት ጉዳት እንዳያደርስ የግንባታ ሥፍራውን ተቀባይነት ባላቸው ቁሶች መከለል፣ በቁፋሮ ወቅት ከመሬት በታች ሊኖሩ የሚችሉ የመሠረተ ልማት መሥመሮች እንዳይጎዱ፣ በአካባቢው የትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል፣ ተቀጣጣይነት ያላቸውን የግንባታ ቁሳቁሶች በአያያዝ ጉድለት ለእሳት አደጋ እንዳይጋለጡ በማድረግ፣ በግንባታ ሥራ ላይ ለተሠማሩ ሠራተኞችና ጐብኚዎች የደህንነት መጠበቂያዎችን በማሟላት፣ ለግንባታ የሚውሉ የኬሚካል ውጤቶች በአጠቃቀም ወቅት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ እና ብናኝ ጭስና አንጸባራቂ ጨረር የመሳሰሉ አዋኪ ነገሮች አካባቢውን እንዳይረብሹ ተገቢው ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይክቶሬት የተዘጋጀ


https://t.me/ethioengineers1