Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.29K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-02-22 19:10:29
የአሜሪካ ኤምባሲን እናመሰግናለን
U.S. Embassy Addis Ababa


የዓድዋው ጀግና ፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ መኖሪያ ቤት የነበረውን አሜሪካን ግቢ የሚገኘው የቅርስ ቤት ነባር ታሪካዊ ይዘቱን መልሶ የሚያስገኘውን የቅርስ ጥገና ስራ (እድሳት) የአሜሪካ ኤምባሲ ባደረገው ድጋፍ ስራው ተጠናቆ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል።

ቅርሶቻችን በራሳችን መጠበቅ፣ መታደስ እና እንክብካቤ መደረግ የሚገባቸው ቢኾንም፤ ከእኛ ቸልታ አንጻር እየወደቁ እየፈረሱ የሚጠፉ ቅርሶቻችንን መልሶ ሕይወት ለመዝራት የአሜሪካ ኤምባሲ ድጋፍ ሲያደርግ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም።

ኤምባሲው ከዚህ ቀደም በላሊበላ የሚገኙትን ቤተ ሩፋኤል እና ቤተ ሚካኤል ውቅር አብያተክርስቲያናትን ተመሳሳይ የቅርስ ጥገና ስራ መደገፉ ይታወሳል።

እናመሰግናለን።


Yared shumete
https://t.me/ethioengineers1
1.5K viewsENG Sintayehu Melese, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 18:51:25
አቃቂ ቃሊቲ

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በስራ ላይ የነበሩ ሶስት ወጣቶች ከአራተኛ ፎቅ ላይ ወድቀዉ ህይወታቸው አለፈ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ልዩ ቦታው ማደያ አካባቢ በግንባታ ላይ ካለ ህንጻ ላይ በስራ ላይ የነበሩ 3 ወጣቶች ወድቀዉ ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ተናግረዋል፡፡

አደጋው በዛሬው እለት ከቀኑ 9፡10 የተከሰተ ሲሆን ሶስቱ ሰራተኞች በስራ ላይ እንዳሉ ከአራተኛ ፎቅ ተንሽራተው  የኤሌክትሪክ መብራት ሀይል ሽቦ ላይ ወድቀው ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ተገልጿል፡፡

ይህን መሰል አደጋ በተደደጋሚ እየተከሰተ ነዉ ያሉት አቶ በቀለ ፤ በተለይም በቀን ስራ ላይ ያሉ ግለሰቦች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደርጉ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ተናግረዋል፡፡

መረጃው የብስራት ሬዲዬ ነው።


https://t.me/ethioengineers1
2.8K viewsENG Sintayehu Melese, edited  15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 09:41:58
ዳሎል የቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ላለፉት 18 ዓመታት ሲሰጥ የቆየውን የአድቫንስድ ኳንቲቲ ሰርቬይንግ ስልጠና ከየካቲት 19/2015 ጀምሮ ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:00 በመስጠት በ12 ሳምንታት ለማጠናቀቅ ምዝገባ በማከናወን ላይ ይገኛል። በአይነቱ ልዩ የሆነውን ይህን ስልጠና መካፈል የምትፈልጉ የትምህርት ማስረጃችሁንና 3,000 ብር በመያዝ ሳሪስ በሚገኘው የካዲስኮ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በመገኘት እስከ ቅዳሜ የካቲት 18/2015 ከቀኑ 6:00 ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911439855 ይደውሉ።
944 viewsENG Sintayehu Melese, 06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 09:41:58 የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋን በኢትዮዽያ የሚቃኝ ሪፖርት።

ይህ ሪፖርት ወረቀት በማገላበጥ ብቻ በሶስት ቀን የውስጥ እኤአ በ2013 ዓም የተሰራ (Desk Research) ቢሆንም የአገራችንን የርዕደ መሬት ተጋላጭነት ዘርዘር ባለ መልኩ የሚያመላክት ነው።

የተያያዘውን PDF አውርደው መመልከት ይቻላሉ።

Assessing seismic risk in Ethiopia By Siân Herbert, 2013

https://t.me/ethioengineers1
929 viewsENG Sintayehu Melese, 06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 19:48:28
For the 2 Months Project Planning & Contact Administration, here is summary of the package with our Instructor's profile (Eng. Fikru Kinfu Gebrekiristos)
Class Option 1.
Tuesday & Thursday evening,11:30-1:30
Class Option 2.
Saturday 8:00-12:00

+251995016195
https://t.me/BeGetEngineering
1.4K viewsENG Sintayehu Melese, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 19:48:28
The Urban Center Presents Half-Day skill trainings | በከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል የሚዘጋጁ የተለያዩ የግማሽ ቀን የክህሎት ስልጠናዎች

እባክዎን ይህንን ቅፅ ይሙሉ፡
cutt.ly/n3K4h8q

@theurbancenter
1.4K viewsENG Sintayehu Melese, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 19:48:28 የግንባታ ፍቃድ አጠያየቅ እና የወሰንተኛ ጉዳይ

የማሻሻያ፣ የመጠቀሚያ ፈቃድ፣ ጊዜያዊ ግንባታ ወይም የማፍረስ ሥራ ለማከናወን የሚቀርብ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ ሲኖር በተናጠል በተዘጋጀላቸው (ማለትም  ለአዲስ ለማስፋፊያ ወይም ለማሻሻያ ግንባታ ቅፅ፣ ለግንባታ እድሳት ፈቃድ ቅፅ፣ ለግንባታ ማፍረስ ፈቃድ ቅጽ፣ ለአገልግልት ለውጥ ቅጽ፣ ለጊዜያዊ ግንባታ ቅጽ) በመሙላት የግለሰብ ከሆነ በአመልካቹ ተፈርሞ፣ በመንግስታዊ፣ በሕዝባዊ እና የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተያዘ ወይም የሚተዳደር ከሆነ በኃላፊው ተፊርሞ እና የድርጅቱ ማህተም አርፎበት ጥያቄው መቅረብ ይኖርበታል።

ማንኛውም የግንባታ ፈቃድ ጠያቂ ስለወሰንተኞቹ ትክክለኛ መረጃ በወሰንተኛ ግንባታ መግለጫ ቅጽ ላይ ወሰንተኛውን በማስሞላትና በማስፈረም ማቅረብ አለበት፣ ቅፁን ለመሙላት ፈቃደኛ በማይሆን ወሰንተኛ የከተማ አስተዳደሩ ቅፁን የማስሞላት ሃላፊነት አለበት። ወሰን ላይ የሚገነባ የምግብ ማብሰያና መሰል አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች ግድግዳ የእሳት ቃጠሎን በተሻለ ሁኔታ መከላከል በሚችል ድፍን የግድግዳ ቁሳቁስ መገንባት አለበት እንዲሁም ጭስ እና እንፋልት ወደወሰነተኛ መውጣት የለበትም።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ አንድ ዓይነት ስታንዳርድ ፕላኖች ያላቸው ግንባታዎች የየራሳቸው የግንባታ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።

ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማካተት ይኖርበታል፣ ወለልና በላይ ያለው ማንኛውም ግንባታ (የምድር በታች ወለል ቢኖረውም ባይኖረውም) ከወሰን ሁለት ሜትርና ከዚያ በታች ተጠግቶ የሚሰራ ከሆነ በቅድሚያ የወሰን ላይ ግንባታ ቅጽ መሙላትና ስምምነት ማግኘት ይኖርበታል፣ ለፈቃድ የሚቀርበው ስትራክቸራል ዲዛይን የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መዋቅር ይዘት ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፤ የሚቀርበው የዲዛይን ሠነድ የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መጠን ለምሳሌ የኃይል ሚዛን (Load) ከግምት ያስገባበት አግባብ ማመልከት አለበት፣ በወሰንተኛ ነባር ግንባታ ደህንነት ላይ ምንም አይነት መናጋት እንዳይፈጠር በቁፋሮና በግንባታ ሂደት መወሰድ የሚኖርበትን የሚያሳይ የጥንቃቄ ንድፍ ለፍቃድ ከሚቀርበው ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት።

አየር ማስገቢያ ሳይኖረው ብርሃን ብቻ የሚያስገባ ግንባታ ወሰን ላይ ለመሥራት ለዚሁ ተብለው በተዘጋጁና አሳልፈው በማያሳዩ ውፍረታቸው ከ5 ሳ.ሜ የማያንስ የመስታወት ግርግዳ መጠቀም ይቻላል ይህም በሚቀርበው ዲዛይን ላይ በግልጽ መጠቀስ ሲኖርበት ወሰን ላይ የተሰራ ከሆነ ወሰንተኛው እንደማንኛውም ድፍን የግድግዳ አካል አስጠግቶ ሊሰራበት ስለማይከለከል የብርሃን ማስገቢያ መስፈርት ለሚጠየቅበት ተጨማሪ ወይም አማራጭ የብርሃን ምንጭ ማመልከት አለበት።

ማንኛውም ሰው ግንባታውን እስከ ወሠን አስጠግቶ ማከናወን ይችላል ሆኖም ወሠን ላይ ለመገንባት ያቀደ ሰው በአዋሳኙ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርገውን የመከላከያ ዘዴዎች ለአጎራባቹ ማሳወቅ ይኖርበታል።

ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቀ ድረስ በአጎራባቹ አደጋና ችግር በማያስከትል ሁኔታ መከናወን አለበት።

በማንኛውም ጊዜ ወሰንተኛው ግንባታውን እንዲከታተል መፍቀድ  አለበት።

በማንኛውም የግንባታ ወቅት ለሚፈጠር ችግር ገንቢው ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል።

በአዋጁ፣ በደንቡ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባረቀቀው የሕንጻ መመሪያ (Building Directives) እና በሌሎች የማስፈጸሚያ ሰነድች ላይ የተገለፁትን መስፈርቶች ያላሟላ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ በግንባታ መጠየቂያ ቅጽ ላይ በተመለከተው ቦታ ያልተሟላበትን ምክንያት በመግለፅ ተመላሽ መደረግ ይኖርበታል።


https://t.me/ethioengineers1
1.3K viewsENG Sintayehu Melese, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 16:42:17
ዳሎል የቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ላለፉት 18 ዓመታት ሲሰጥ የቆየውን የአድቫንስድ ኳንቲቲ ሰርቬይንግ ስልጠና ከየካቲት 19/2015 ጀምሮ ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:00 በመስጠት በ12 ሳምንታት ለማጠናቀቅ ምዝገባ በማከናወን ላይ ይገኛል። በአይነቱ ልዩ የሆነውን ይህን ስልጠና መካፈል የምትፈልጉ የትምህርት ማስረጃችሁንና 3,000 ብር በመያዝ ሳሪስ በሚገኘው የካዲስኮ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በመገኘት እስከ ቅዳሜ የካቲት 18/2015 ከቀኑ 6:00 ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911439855 ይደውሉ።
1.2K viewsENG Sintayehu Melese, 13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 13:18:16
ኮንትራቱ ተቋረጠ

የአደይ አበባ ብሄራዊ ስታድየምን የሚገነባው የቻይናው ተቋራጭ ውል እንዲቋረጥ ተወሰነ።

የአደይ አበባ ብሄራዊ ስታድየምን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው የቻይናው ተቋራጭ ባቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ ላይ መግባባት ባለመቻሉ ከተቋራጪ ጋር የተገባው ውል እንዲቋረጥ መወሰኑን ሪፖርተር ዘግቧል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በነበረው ውል ላይ 225 በመቶ የዋጋ ማስተካከያ በማድረግ 12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመክፈል ቢስማማም ኩባንያው 17 ቢሊዮን ብር እንዲከፈለው ሌላ የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ በማቅረቡ ውሉ እንዲፈርስ መደረጉን ዘገባው አክሏል።


https://t.me/ethioengineers1
1.9K viewsENG Sintayehu Melese, 10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 11:17:37
For the 2 Months Project Planning & Contact Administration, here is summary of the package with our Instructor's profile (Eng. Fikru Kinfu Gebrekiristos)
Class Option 1.
Tuesday & Thursday evening,11:30-1:30
Class Option 2.
Saturday 8:00-12:00

+251995016195
https://t.me/BeGetEngineering
1.8K viewsBelay #1, 08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ