Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.29K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-02-03 20:54:24
የግንባታ ዲዛይን ከተሰራ በኋላ የሚመለከተው የመንግሥት ቢሮ ዲዛይኖቹን (All drawings, details and BOQ) አይቶ እስከማረጋገጥ (መርምሮ አስተያየት ከመስጠት እስከማጽቀድ) የሚወስድበት ጊዜ በመመሪያ የተደነገገ ሲሆን ከፍተኛው ውስብስብነት እና ግዝፈት ላላቸው ሕንጻዎች (ምድብ ሐ) የሚወስደው ጊዜ 21 ቀን ነው።

አንድ የግንባታ ፍቃድ ከ21 ቀን በላይ የማጽደቂያ ጊዜ ሊራዘምበት አይገባም።

የህንጻ መመሪያና ስታንዳርድ  ቁጥር 3/2015  (4.8)


https://t.me/ethioengineers1
2.4K viewsENG Sintayehu Melese, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 09:25:07
Twin stairs

Twin stairs are very similar to branch stairs in certain respects. Not only does it look stylish, it takes up less space than a bifurcated staircase.

The twin staircase consists of two curved symmetrical staircases that start on two sides from the basement and end next to each other on the upper floors. They do not share a landing anywhere along the stairs, nor do they converge on a single wider staircase. They are two separate staircases that are identified as a single element due to their symmetrical nature.


https://t.me/ethioengineers1
2.0K viewsENG Sintayehu Melese, 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 19:28:50
BEGET ENGINEERING PLC.
●  Detail Schedule for the New 2 Months Advanced level  Class package  Starting on January 30/2022
● ጥር 22 / 2015 የሚጀምር አዲስ ለ 2 ወር የሚቆይ ኘሮግራም
Optional Departments

1)  Building Advanced Structural Design 
2) Bridge Design 
3) Project Planning & Contract Administration 
4) Interior Design 
5) Water Supply & Sewerage 
6) Highway Design 
7) Accounting
for Engineering companies
+251995016195
Megenagna, Marathon Bldg, Office No. 614
Telegram:- https://t.me/BeGetEngineering
2.7K viewsENG Sintayehu Melese, 16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 19:28:50
Raft or Mat Foundations :

Raft or mat foundations are the types of foundation which are spread across the entire area of the building to support heavy structural loads from columns and walls.

እነዚህን የምንጠቀመው መሬቱ የመሸከም አቅሙ ትንሽ ከሆነና spread footing ስንጠቀም የህንጸውን ስፋት ከ50 ፐርሰንት በላይ ከሸፈኑት ነው።

አንዳንዴ ግን spread footing ከ 50 ፐርሰንት በላይ ቢሸፍኑትም ለ spread footing negative reinforcement ስለማንጠቀም ከ Mat ይልቅ ኢኮኖሚካል ሊሆኑ ይችላሉ ምክንያቱም Mat negative & positive reinforcement ይጠቀማሉ፡፡

https://t.me/ethioengineers1
2.5K viewsENG Sintayehu Melese, edited  16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 08:42:50
በግንባታ ላይ ያሉ የፍሊንት ስቶን ቤቶች እንዳይሸጡ ፣ እንዳይለወጡ ታገዱ።

የመኖርያ ቤቶችን ሰርቶ ለመሸጥ የተቋቋመው ፍሊንት ስቶን አክስዮን ማህበር ፣ ቤት ለመግዛት ከተመዘገቡ ግለሰቦች ጋር በገባው ውዝግብ ሳቢያ በቦሌ ክፍለ ከተማ ያለው የአደይ በሻሌ ሳይት ላይ ያሉ ጅምር ግንባታ ቤቶች በፍርድ ቤት እንደታገዱበት ዋዜማ ዘግባለች።

እግዱ የተላለፈው ፍሊንት ስቶን ይህን ሳይት በሁለት አመት ከሁለት ወር ውስጥ ቤት ሰርቼ አስረክባቹሀለሁ ብሎን በሰባት አመትም አላስረከበንም” ያሉ 213 ግለሰቦች ፣ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ያቀረቡትን ክስ ተከትሎ ነው።

ከሳሶቹ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ውሳኔ እልባት እስኪያገኝ ድረስም ሳይቱ እግድ እንዲወጣበት በጠየቁት መሰረት ችሎቱ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ የሚገኙ ጅምር የመኖርያ ቤቶች እንዳይሸጡ ፣ እንዳይለወጡ ፣ በማንኛውም ሁኔታ ወደ 3ኛ ሰው ሳይዞሩ ታገደው ባሉበት ሁኔታ እንዲቆዩ አዟል።


https://t.me/ethioengineers1
2.0K viewsENG Sintayehu Melese, 05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 21:26:44 ኢትዮጵያ የምትጠቅምባቸው የኮንስትራክሽን ሕጎች

ሀገራችን ኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማስተዳደር የምትጠቀምባቸው አዋጆች (Decree)፣ ደንቦች (regulations)፣ መመሪያዎች (Directives)፣ ስታንዳርዶች (Manuals)፣ የውል ሰነዶች (Contract Conditions)፣ ህጎች (Laws and codes)፣ ጋዜጦች (Negarit) አሏት። እነዚህን ማሕቀፎች በሁለት ምድብ መመደብ  (ዓለም አቀፋዊ እና ሀገር አቀፋዊ) ማለት እንችላለን። 

1ኛ) በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የኮንስትራክሽን ውል ማህቀፎች፦ FIDIC MDBS (Federation Internationale Des Ingenieurs-Conseils)፣ EU condition of contract፣ NEC- new engineering contract, UK (በተለይ ለውኃ ቁፋሮ ውል የሚውል) ናቸው። ከዚህ ባሻገር የተለያዩ ማኑዋሎችን እንደ መሪ ልኬት (በተለይ የግንባታ ግብአቶችን ጥራት በቤተሙከራ ለመለካት) እንጠቀማለን።
ከእነዚህም ውስጥ:- American Society Testing Materials (ASTM), American Association of State Highway and Transportation Officials (AASHTO) ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ Indian Standards (IS) እና British Standard (BS)  አልፎ አልፎ ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው።

2ኛ) የሀገር ውስጥ ማሕቀፎች፦ Building and Transport Construction Design Authority (BaTCoDA - የግንባታ ሥራዎችንና ግብአቶችን መጠን ለማስላት)፣ Public Procurement Agency (PPA - ለጨራታ እና የስምምነት ውል ሰነድ አስተዳደር)፣ Civil Code, Civil Procedural codes, Ministry of Works and Urban Development Standard Conditions of Contract (MOWUD Directives), FDRE constitution, ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ (Negarit Gazieta), በየጊዜው የሚሻሻሉ የሕንጻ መመሪያዎች እና ስታንዳርዶች፣ የሙያ እና የሥራ ፍቃድ አዋጆች የመሳሰሉት ይገኙበታል።

በእርግጥ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ አይችሉም የሚባሉ የሀገሪቱ ህጎች አይኖሩም ማለት ይከብዳል፣ ምክንያቱም ሁሉም ህጎች ከቦታ፣ ከሥራ፣ ከሰው ኃይል፣ ከመብትና ግዴታ፣ ከንብረት፣ ከወንጀልና ፍትሕ ጋር የተያያዙ ስለሆነ እና የኮንስትራክሽ ሴክተሩም እነዚህ ሁሉ የሚገኙበት ኢንዱስትሪ ስለሆነ ነው።

Via Abraham Tebeje እናመሰግናለን


https://t.me/ethioengineers1
2.7K viewsENG Sintayehu Melese, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 21:17:19 ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች እና አሰራሮች ይዘን በ Tiktok ለእናንተ ለማድረስ  ዝግጅታችንን  እያጠናቀቅ ሰለሆነ  በጣም አጭር በሚባል ጊዜ ውስጥ  የምንጀምር ይሆናል።

tiktok.com/@ethioengineers
tiktok.com/@ethioengineers
2.6K viewsENG Sintayehu Melese, edited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 16:14:14
BEGET ENGINEERING PLC.
●  Detail Schedule for the New 2 Months Advanced level  Class package  Starting on January 30/2022
● ጥር 22 / 2015 የሚጀምር አዲስ ለ 2 ወር የሚቆይ ኘሮግራም
Optional Departments

1)  Building Advanced Structural Design 
2) Bridge Design 
3) Project Planning & Contract Administration 
4) Interior Design 
5) Water Supply & Sewerage 
6) Highway Design 
7) Accounting
for Engineering companies
+251995016195
Megenagna, Marathon Bldg, Office No. 614
Telegram:- https://t.me/BeGetEngineering
3.7K viewsENG Sintayehu Melese, 13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 21:09:51 ወደ እንጂኔሪንግ ሙያ ለመግባት ፍላጎት ላላቸው 12 ክፍል ተመራቂ ተማሪዎች ምክርዎ ምንድን ነው?
ለሃሳብ እና ኣስተያየት

@Ethiocon143bot
4.2K viewsENG Sintayehu Melese, edited  18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 19:55:37 በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ/Variation/  
   
ቫሬሽን/variation/ ምን አይነት ትርጉም ሊሰጠው ይችላል?

*በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ(variation) የሚባለው በዋናነት የግንባታ ስራ ጥራትን፣መጠን፣ዲዛይን፣የግንባታ ቁሳቁስ፣የስራ ጊዜ፣የግንባታ ማከናወኛ ቦታ መጠን የመሳሰሉትን የማሻሻል፣የመጨመር ወይም የመቀነስን የሚመለከት የኮንስትራክሽን ውል መሰረታዊ ነጥብ ነው፡፡
*ስለዚህ ቫሬሽን የዋናውን የኮንስትራክሽን ውል ይዘት/object of the contract/ በመጠኑ የመለወጥ ባህሪ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
*PPA 2011 ክሎስ 15.1 ይሄንኑ አረዳድ በሚያጠናክር ሁኔታ ለቫሬሽን ትርጉም ይሰጠዋል፡፡

ቫሬሽን ኦርደር/variation order/ የሚባለውስ ምንድን ነው? ማነው ኦርደር ሰጭው? በቃል ኦርደር መስጠት ይቻላል? በምን አይነት መልኩ ነው ትእዛዝ የሚሰጥ? በዚህ ረገድ ህጉ ምን ይላል?

*ቫሬሽን ኦርደር ከመሀንዲሱ ለተቋራጩ በጽሁፍ የሚሰጥ የስራ ለውጥ ትእዛዝ ነው፡፡
*አማካሪ መሀንዲሱ ለግንባታ ስራው መልካም አፈጻጸም ሲባል የስራ ለውጥ ትእዛዝ አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነ ትእዛዝ መስጠት ይችላል፡፡
*በመጀመሪያ ግን በአማካሪ መሀንዲሱ አማካይነት ለተቋራጩ ስለለውጥ ስራው ባህሪና ምንነት ማሳወቂያ/ኖቲስ/ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ኖቲስ እንደደረሰው ተቋራጩ የለውጥ ስራውን አስመልክቶ ትሮፖዛል ያቀርባል፡፡ፕሮፖዛሉም የጊዜ ማራዘሚያ/ስኬጁል፣የዋጋ ሁኔታን የሚያካትት ይሆናል፡፡(PPA 15.3)
*የስራ ለውጥ ትእዛዝ በጽሁፍ ነው መደረግ እንዳለበት PPA 2011 ክሎስ 15.2 ያስቀምጣል፡፡አንዳንዴ ግን አማካሪ መሀንዲሱ በቃል የቫሬሽን ትእዛዝ መስጠት እንደሚችል PPA 2011 ክሎስ 15.2(a) ላይ ፈቃጅ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን በቶሎ የለውጥ ስራ ትእዛዙ ወደ ጽሁፍ መቀየር ይኖርበታል፡፡
እዚህ ጋር አብሮ የሚታየው ነገር የአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎች በጽሁፍ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ይሄውም ስለውሎች በጠቅላላው በሚመለከተው የውል ህግ አንቀጽ 1724 ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
*አንድ ውል የሚሻሻለው ደግሞ ከመጀመሪያው ውል ጋር ተመሳሳይ በሆነ ፎርም ነው፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1722 ላይ "ዋናውን ውል የመለወጥ ጉዳይ ለዚሁ ውል በተደነገገው አጻጻፍ(ፎርም) መሰራት አለበት፡፡" በሚል የተደነገገው የሚያስገነዝበውም ቫሬሽን ዋናውን ውል በከፊል የመለወጥ ሁኔታ ስለሚኖረው ከዋናው የኮንስትራክሽን ውል ጋር በተመሳሳይ የአጻጻፍ ፎርም በጽሁፍ መደረግ ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ለዚህ ነው በመርህ ደረጃ ቫሬሽን በጽሁፍ መደረግ አለበት የሚባለው፡፡

የስራ ለውጥ ውል/change agreement/ ምን ማለት ነው? ከህግ አንጻር በዚህ ረገድ ምን ነጥቦች ሊነሱ ይችላሉ?

*PPA 2011 ክሎስ 15.9 ላይ እንደተቀመጠው በየስራ ለውጥ ውል የሚባለው ከቫሬሽን ኦርደር በኋላ አሰሪው/ተወካይ መሀንዲሱ እና ተቋራጩ በጽሁፍ የሚስማሙበት የማሻሻያ ውል ነው፡፡ ሆኖም በዚህ የፒፒኤ ትርጉም ጸሀፊው አይስማማም፡፡ምክንያቱም አማካሪው ስራ ለመቆጣጠር እንጅ ውል ለመዋዋል በአማካሪነት ውሉ ላይ ብዙ ጊዜ ስልጣን አይኖረውም፡፡በተቋራጭና አሰሪ መካከል የተደረገ የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ በሚደረግ ስምምነት/ውል ሊሻሻል ከሚችል በስተቀር አማካሪ መሀንዲሱን ውል እንዲዋዋል እስከመፍቀድ የሚደርስ ትርጓሜ መሰጠቱ ተገቢነት የለውም፡፡
*የስራ ለውጥ ውሎች ቀን፣ቁጥርና ቅደምተከተል ይሰጣቸዋል፡፡(ፒፒኤ15.10)
*ሌላው የስራ ለውጥ ውል ወደኋላ ሄዶ እንደማይሰራና ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ብቻ አስገዳጅ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.10 ላይ ተቀምጧል፡፡

በቫሬሽን የተሰሩ ስራዎች የዋጋ አወሳሰን/Valuation of variation/ በምን ሁኔታ ይከናወናል?

*የተሰራው ተጨማሪ ስራ ከሆነ እና በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ላይ ዋጋ ተተክሎለት ካለ በዚያው የዋጋ ሬት የሚሰላ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.5(a) ላይ ተቀምጧል፡፡
*በቫሬሽን የሚሰራው ስራ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ያልተካተተ አዲስ የስራ አይተም ከሆነ በመሀንዲሱና ተቋራጩ በስምምነት በወቅታዊ ዋጋ የሚሰላ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.5(b) ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
*በቫሬሽን የተካተተው የስራ አይተም ዋጋው በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ላይ የተካተተ ቢሆን እንኳ የተጋነነ ከሆነ በመሀንዲሱ ሊስተካከል እንደሚችል ደግሞ PPA 2011 ክሎስ 15.5(c) ይገልጻል፡፡
*ቫሬሽኑ የተከሰተው በተቋራጩ ጥፋት ከሆነ ደግሞ በአሰሪው ለተቋራጩ ዋጋ አይከፈልበትም በሚል PPA 2011 ክሎስ 15.5(d) በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

ቫሬሽን እስከስንት ፐርሰንት ይፈቀዳል? በፍርድ ቤቶች አካባቢ ያለው የህጉ አረዳድስ ምን ይመስላል?

*የቫሬሽኑ መጠን ከ25% በላይ በሆነ ጊዜና ከተቋራጩ ጥፋት ባልሆነ ሁኔታ የተከሰተ ከሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ስለብልጫው መጠንና ስለዋጋው ከአሰሪው መስሪያ ቤት ጋር በመመካከር ይወስናል በሚል PPA 2011 ክሎስ 15.7 ላይ ተቀምጧል፡፡
የቫሬሽን መጠን ከመጀመሪያው ዋጋ ከ30% በላይ መብለጥ እንደሌለበት በአስገዳጅ ሁኔታ PPA 2011 ክሎስ 15.8 ላይ ተቀምጧል፡፡
*በዚህ በጀኔራል ኮንዲሽን ከተቀመጠው ተርሰንት/ከገደቡ በላይ በቫሬሽን ስራ ተሰርቶ ቢገኝስ ምን ይሆናል? እንግዲህ በዚህ ረገድ ጀኔራል ኮንዲሽኑም ሆነ አግባብነት ያለው የግዥ አዋጅና መመሪያ ግልጽ ምላሽ አያስቀምጥም፡፡ ሆኖም ግን ተቋራጩ ስራውን እስከሰራው ድረስ አሰሪው አላግባብ በተቋራጩ ድካምና ገንዘብ በልጽጐ እንዲቀር ፈቃጅ ህግ ሊኖር አይችልም፡፡ፍትሀዊም አይሆንም፡፡
*ስለዚህ በዚህ ረገድ በአማካሪ መሀንዲሱ እውቅና እና ትእዛዝ በቫሬሽን ለተሰሩ ስራዎች  ከገደቡ በላይ ያለፈ ቢሆንም እንኳ አሰሪው ለተቋራጩ ሊከፍለው እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ5ዳኞች እንደህግ በሚቆጠር ሁኔታ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ ይሄውም አስገዳጅ ውሳኔ በሰ/መ/ቁ 71972 ቅጽ 14 ገጽ 25 ላይ ይገኛል፡፡ 
ቫሬሽን ከሙስና ጋር ምን ያገናኘዋል?
*በዚህ ረገድ የኢፌዴሪ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የኪራይ ሰብሳቢነት መንስኤዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በሚል በመስከረም 2010ዓ.ም ባዘጋጀው የውይይት ሰነድ ላይ ቫሬሽን ለሙስና አንዱ ምንጭ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
*ይሄውም ለምሳሌ ያህል የማይጣጣሙ ዲዛይኖችና የስራ ዝርዝር መኖር አንዱ ነው፡፡
*ሌላኛው ደግሞ ሆነ ብሎ የስራ ዝርዝር መዝለል/omission of work item/ ነው፡፡
በአይነቱ አዲስ የሆነ ተጨማሪ ስራ/unrelated and new item of additional work/ ሲያጋጥምስ በየትኛው ህግ የሚታይ ይሆናል?
*በመርህ ደረጃ አሰሪው መስሪያ ቤት በውል ውስጥ የሌሉትን ስራዎች በአዲስ ዋጋ እንዲሰራቸው ስራ ተቋራጩን ለማዘዝ እንደሚችል በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3284(1) ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
4.2K viewsENG Sintayehu Melese, edited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ