Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction
የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.63K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2023-01-26 18:32:09
#Ethiopia  | አዲሱን የሲሚንቶ መሸጫ

የመሸጫ ተመኑ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋልም ተብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የመሸጫ ዋጋ በኩንታል

ዳንጎቴ ሲሚንቶ 1 ሺህ 106 ብር ከ85 ሳንቲም

ደርባ ሲሚንቶ 1 ሺህ 67 ብር ከ33 ሳንቲም

ካፒታል ሲሚንቶ 1 ሺህ 52 ብር ከ25 ሳንቲም

ኩዩ ሲሚንቶ 1 ሺህ 65 ብር ከ25 ሳንቲም መሸጫ ዋጋ እንደተቆረጠላቸው ተገልጿል።

በአጠቃላይ ሁሉም የሲሚንቶ ምርቶች ከ1 ሺህ 200 ብር በታች እንደሚሸጡ ነው የተገለጸው።

በክልል እና ዞኖችም የመሸጫ ዋጋ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግም ተነግሯል፡፡

https://t.me/ethioengineers1
4.8K viewsENG Sintayehu Melese, edited  15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 17:58:44
የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ስንት ጊዜ ነው የዋጋ ተመን እየወጣለት በገዥዎች ላይ አሉታዊ ተጽኖ የሚያደርሰው

እያለ ሰው እየጠየቀ ነው።

በቅርቡ የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ተስተካክሎ ነበር፥

ብር 590 → 683 → 795 → 1,200 → ...

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ከደቂቃዎች በፊት የሚከተለውን መግለጫ ሰጥቷል

የሲሚንቶ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከ1200 ብር በታች እንዲሆን ተወሰነ

አዲስ አበባ 18/5/205(ንቀትሚ) በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች የሲሚንቶ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ 1200 ብር በታች እንዲሆን መወሰኑን የሲሚንቶ አምራቾች ቦርድ አስታውቋል፡፡

ቦርዱ በቅርቡ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ተግባራዊ በተደረገው የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ መሰረት የሲሚንቶ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎችና የመሸጫ ዋጋውን አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ አዱኛ በቀለ እንደገለጹት የሲሚንቶ ግብይትና ስርጭትን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ቁጥር 940/2015 ተግባራዊ በመደረጉ ሲስተዋል የነበረውን የሲሚንቶ እጥረትና የዋጋ ንረት ማስታገስ የተቻለ ሲሆን ሲሚንቶ አዲስ በተተመነው የመሸጫ ዋጋ ከቀጣይ ሣምንት ጀምሮ ገበያ ላይ ይውላል፡፡

በመመሪያው መነሻነት አዲስ በተተመነው ዋጋ መሰረት ሁሉም የሲሚንቶ አይነቶች በኩንታል ከ1 ሺ 200 ብር በታች በሆነ ዋጋ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ከተሞች ለገበያ ይቀርባል፡፡

ለዚህ መመሪያ ተግባራዊነትም አምራቾች፣ ቸርቻሪዎች፣ ሸማቾችና ተቆጣጣሪ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡም ቦርዱ ጥሪ አቅርቧል
፡፡

https://t.me/ethioengineers1
4.1K viewsENG Sintayehu Melese, 14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 11:16:57
#AddisAbaba

ከ2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ሀይሌ ግራንድ አዲስ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል በይፋ ስራ ጀመረ።

በመዲናችን አዲስ አበባ በየካ ክፍለ ከተማ ላም በረት መናኽሪያ አካባቢ በ15 ሺህ ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈውና ባለቤትነቱ የሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ የሆነው የሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ስምንተኛ መዳረሻ " ሀይሌ ግራንድ አዲስ አበባ " ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመሩ ዛሬ ተገልጿል።

2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት "ሃይሌ ግራንድ አዲስ አበባ" እ.ኤ.አ ከጥቅምት 01/2022 ጀምሮ በሙከራ ደረጃ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

ሆቴሉ ለ450 ሰራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለ120
#አዲስ_ተመራቂ ሰራተኞች ስልጠና በመስጠት ስራ እንዱጀምሩ መደረጉ ተገልጿል።

ሆቴሉ በውስጡ ፦

- 130 ክላሲክ ፤ 14 ስዊት ፤ 12 ፕሪሚየር እና 1 ፕሬዝዳንሻል ባጠቃላይ 175 አልጋዎችን የያዘ 157 ምቹና ሰፊ የመኝታ ክፍሎችን
- 4 ሬስቶራንቶች እና 2 PDR ፤
- 4 ባር፤
- 1pastery & coffe shop፤ 
- 1 የተሟላ የባህል ምግብ አዳራሽ፤
- 8 የስብሰባ አዳራሾች እና 2 ትላልቅ Ballrooms
- የጤና እና የውበት መጠበቂያ ማዕከል
- ጂም እንዲሁም 200 ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ይዟል።

Tikivha
https://t.me/ethioengineers1
4.3K viewsENG Sintayehu Melese, 08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 17:42:58
#የጨረታ_ማስታወቂያ

ቢሮው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ የሚገነባውን B+G+10 የአርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ማዕከል ግንባታን ለማከናወን ፍላጎት ያላቸውን ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾችን እየጋበዘ ጥር 11 /2015 የወጣውን  ሄራልድ ጋዜጣ መመልከት እንደምትችሉ ያሳውቃል፡፡

https://t.me/ethioengineers1
6.0K viewsENG Sintayehu Melese, 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 08:59:27
ውድ የእትዮ ኮንስትራክሽን ቤተሰቦች ይህን ዜና መዘገባችንን ታስታውሳላችሁ .......

ህግ ይዞታል ተብለን ነበር ታድያ ከየት ደረሰ ?
የአደጋው መክንያት ምን እንደሆነ ተጠንቶ ይገለፃል ተብሎ ነበር እስካሁን የተባለ ነገር የለም .....

*እንደዚህ አይነት ነገሮች happen ሲያደርጉ ጊዜያዊ news ከመሆን ውጭ ፍትህ አገኙ ሲባል ሰምተን አናውቅም .....ሀዋሳ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ጨምሮ


*መፍትሔ(ፍትህ) እስካልተሰጣቸው ድረስ ስህተቶች መማሪያ ልሆኑ አይችልም የአንድ ሰሞን ዜና ከመሆን ውጭ

*እትዮ ኮንስትራክሽን መጠየቁን ይቀጥላል ......ከተሳሳትኩ እታረማለሁ ....የተለየ መረጃ ካላችሁ ላኩልኝ ....እንማማርበታለን

ለሃሳብ እና ኣስተያየት  ይጠቀሙ

@Ethiocon143bot

https://t.me/ethioengineers1
5.6K viewsENG Sintayehu Melese, edited  05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 13:59:28
BEGET ENGINEERING PLC.
●  Detail Schedule for the New 2 Months Advanced level  Class package  Starting on January 30/2022
● ጥር 22 / 2015 የሚጀምር አዲስ ለ 2 ወር የሚቆይ ኘሮግራም
Optional Departments

1)  Building Advanced Structural Design 
2) Bridge Design 
3) Project Planning & Contract Administration 
4) Interior Design 
5) Water Supply & Sewerage 
6) Highway Design 
7) Accounting
for Engineering companies
+251995016195
Megenagna, Marathon Bldg, Office No. 614
Telegram:- https://t.me/BeGetEngineering
5.4K viewsENG Sintayehu Melese, 10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 13:59:28
Suspended Scaffolding

In suspended scaffolding, the working platform is suspended from roofs with the help of wire ropes or chains etc., it can be raised or lowered to our required level. This type of scaffolding is used for repair works(ለጥገና ሥራዎች) ,pointing, paintings(ለቀለም) etc.

https://t.me/ethioengineers1
4.4K viewsENG Sintayehu Melese, edited  10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 20:59:07 ለአንድ ህንፃ መፍረስ መክንያት ይሆናል ተብለው  ብዙ ልህቃን የሚስማሙበት ጉዳይ:-

አንድ ህንፃ የተለያዩ structural member (column , beam , slab..etc) ውቅር ነው ስዋቀርም ሁሉም የየራሳቸው አገልግሎት አላቸው የህንፃው ህልውና የመፍረስና ያለመፍረስ ዋስትና ተገብውን አገልግሎት በተገቢው መንገድ የመስጠት ሀላፊነትና የህንፃው የአገልግሎት እድሜ የሚወሰነው well designed structural member መሆኑ እሙን ነው።

The reasons a building collapses can be due to
poor structural design,
poor compliance with specifications
poor quality control
faulty construction methodology foundation failure
extraordinary loads and corruption. Natural disaster is also identified as a cause of building collapse.

በመሆኑም በእኛ አገር በስፋት ከሚስተዋለው ምክንያቶች መሀከል
poor structural design
faulty construction
poor quality control and corruption ዋነኞቹ ናቸው።

አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል ? እንዴት??

ህንጻው መሸከም ከሚችለው ባነሰ በትንሽዬ ሎድ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች ነው
1,በ Fatigue
2, Creep ነው

1,Fatigue
ሎዶቹ ትንንሽዬ ቢሆኑም እንኳን በሎድ ድግግሞሽ የተነሳ የህንጻው ጥንካሬ ሲደክም የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በአብዛኛው የሚከሰተው ድልድዮች ላይ ነው - የመኪና ድግግሞሽ፡፡

2,Creep
አንድ ሎድ አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜ በመቀመጡ ሳቢያ Strain ሲጨምር የሚፈጠር ነው፡፡

#ETHIO CONSTRUCTION

@ethioengineers1
5.2K viewsENG Sintayehu Melese, 17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 21:25:15 #የቅድሚያ_ክፍያ (Advance Payment)

በዚህ ፅሁፍ ቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው? አላማውስ? አቅራቢውና ተጠቃሚውስ ማን ነው? ያለባቸው ግዴታስ ምን ይመስላል? የሚሉትን ነጥቦች እንዳስሳለን

የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና በኮንስትራክሽን ዉሎች ከሚዘወተሩ የዋስትና አይነቶች አንዱና የተለመደዉ ነው፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ የቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው እሚለውን እንይ፡፡ በመንግስት ግዢ አዋጁ አንቀፅ 48 ላይ በመንግስት ገዥ አፈፃፀም ጊዚ አቅራቢዎች ከክፍያው ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቅርቡ የቅድሚያ ክፍያ እንደሚስጥ ይገልፃል፡፡
ይህ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ከጠቅላላው የውሉ ዋጋ ሰላሳ ፐርሰንት (30%) መበለጥ እንደለለበትና ሊከፈል የሚችለው የገንዘብ መጠንም በጨረታ መመሪያው ላይ መገለፅ እንደሚገባው የመንግስት ግዢ መመሪያ አንቀፅ 16.26.1 ያስገድዳል፡፡
ተዋዋይ ተቋራጮችም ይህንን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ለማግኘት ከማመለከቻ ጋር የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታዎች ያልተገደበ ዋስትና (Unconditional Bak Guarantee) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሐገር ውስጥ ተቋራጮች ሲሆኑ በሁኔታዎች የተገደበ ዋስትና ከኢንሹራንስ ተቋማት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የሚያቀርቡትም ዋስትና ከሚጠይቁት የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በዋስትናው ምትክ ከመሰረታቸውና ከሚከታተላቸው ባለሰልጣን መስሪያ ቤት የሚያቀርቡት ደብዳቤ እንደ ዋስትና ተቀባይነት ይኖረዋል ሲል የመመሪያው አንቀፅ 16.20.5(ሐ) ይደነግጋል፡፡
ከዚህም በፊት ግን ተቋራጩ በግዢ ስነ-ስርዓቱ ያሸነፈውን ዉል መፈረምና የውል ማስከበሪያ ገንዘብ ወይም ዋስትና ያቀረበ መሆን አለበት (አዋጅ ቁ.649/2001፣ አንቀፅ 48/2/)፡፡
በአዋጁ አንቀፅ 78(3) መሰረት የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ አዋጁንና መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ያወጣው መደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ [The Public Procurement Agency Standard Bidding Document: General Condition of Contracts: PPA-2011] ክሎስ 60(1) ላይ የቅድሚያ ክፍያው ለተቋራጩ መከፈል ያለበት ተቋራጩ ስራውን ለመጀመር የሚያወጣውን ወጪ ለመሸፈን እነዲረዳው ታስቦ ሲሆን ይህም የሚከፈለው ተቋራጩ ለግንባታ ስራው የሚያገለግሉ ማሽኖችን ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን መግዛቱን ወይም ማዘዙን የሚያሳይ መረጃ ሲያቀርብ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ በስራው ጊዜያትም ገንዘቡን እነዚህን ዕቃዎችና ማሽኖችን ለመግዛትና ወደ ግንባታ ቦታው ለማንቀሳቀስ/ለማዘዋወር የተጠቀመበት መሆኑን የሚያሳይ ፋክቱር/Invoices ለኢንጂነሩ በማቅረብ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በተጨባጭ የሚስተዋለው ችግር  ቡዙ ጊዜ ተቋራጮች የቅድሚያ ክፍያውን ለታለመለት አላማ አያውሉም የሚል ሲሆን ይህም ችግር በተለይ በግንባታው ዘርፍ በተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ ይህም ትልቁ ችግር መነሻው እነዚህ ተቋማት ምንም የሚያቅርቡት ዋስትና ሳይኖር ባቋቋማቸው መስሪያ ቤት ደብዳቤ ላይ ብቻ ተማምኖ ክፍያው ስለሚሰጣቸው ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ወይም በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የኢንሹራንስ ዋስትና ያቀረቡ ተቋራጮችን አሰሪው/ተዋዋዩ የመንግስት አካል አስፈላጊ ሲሆን፡ የቅድሚያ ክፍያው ገቢ የሚደረግበትና ከውሉ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ብቻ በመንግስትና በኢንተረፕራይዙ ወይም በኮንትራክተሩ ተወካዮች በጋራ ፊርማ ወጪ የሚደረግ የተለየ የባንክ አካውንት እንዲከፈት ሊያዝ ይችላል፤ ገንዘቡም ለታሰበለት አላማ ብቻ እንዲውል የተለየ ስምምነት መፈራረም አለበት፡፡
ስለዚህ የቅድሚያ ክፍያ ማለት ተቋራጩ ለስራው ማስጀመሪያ የሚሆኑትን የተለያዩ የግንባታ መሳሪያዎች መግዢያነት የሚውል በአሰሪው የመንግስት መስሪያ ቤት በቅድሚያ የሚከፈለው ገንዘብ ነው፡፡ ይህም ምንም ስራ ሳይሰራ የሚከፈል ገንዘብ ስለሆነ ለተቋራጩ ዕዳ ወይም ብድር ነው፡፡ ስለሆነም ተቋራጩ ብድሩን እንዲምልስ ይገደዳል ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ተቋራጩ ይህንን ብድር እንዴት ይመልሳል የሚለው አንዳንድ ጊዜ በግንባታ ውሎች ላይ አለመግባባት ያስነሳል፡፡ በግዢ መመሪያው አንቀፅ 16.26.9 ላይ እንደተገለፀው ለተቋራጮችና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተከፈለ የቅድሚያ ክፍያ በውሉ አፈፃፀም የተለያዩ ደረጃዎች ላይ በክፍያ ሰርተፍኬት ፀድቀው ከሚከፈሏቸው እያንዳንዱ ክፍያዎች ላይ እየተቀነሰ ሙሉ የቅድሚያ ክፍያው እስኪመልስ ድረስ የመንግስት መስሪያ ቤቱ ያስቅራል፡፡ ይህም ማለት ተቋራጩ የወሰደውን የቅድሚያ ክፍያ ሙሉውን ከአንድ ወይም ከሁለት ክፍያዎች ላይ የመክፈል ግዴታ የለበትም፡ አሰሪ መስሪያ ቤቱም ሙሉ ክፍያውን አንዴ ቀንሶ ማስቀረት አይችልም ማለት ነው፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንዳድ ጊዜ ሙሉ ቅድሚያ ከፍያውን በአንዴ ቀንሰው በማስቀረት ከተቋራጮች ጋ እሰጣገባ ሲገጥሙ ይስተዋላል፡፡ ይህ ከህጉ አግባብ ውጭ ነው፡፡
የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ ሙሉውን ሳይመለስ በተለያዩ ምክንያቶች ውሉ ቢቋረጥ የአሰሪ መስሪያ ቤቱ የከፈለውን ገንዘብ ማስመለስ እንዲያስችለው ተቋራጩ የሚያቀርበው ዋስትና ክፍያው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስገዳጅነት እንደሚኖውም መመሪያው ይገልፃል፡፡ ውሉ ቢቋረጥ እንኳን ያልተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው ወዲያውኑ ካለምንመ መቃወሚያ እንዲከፍል ይገደዳል ይላል የመደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ ክሎስ 60.7፡፡

Written By: Girum Getu----Assistant Lecturer @ Wolkite University; School of Law

https://t.me/ethioengineers1
5.5K viewsENG Sintayehu Melese, edited  18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 17:29:23
BEGET ENGINEERING PLC.
●  Detail Schedule for the New 2 Months Advanced level  Class package  Starting on January 30/2022
● ጥር 22 / 2015 የሚጀምር አዲስ ለ 2 ወር የሚቆይ ኘሮግራም
Optional Departments

1)  Building Advanced Structural Design 
2) Bridge Design 
3) Project Planning & Contract Administration 
4) Interior Design 
5) Water Supply & Sewerage 
6) Highway Design 
7) Accounting
for Engineering companies
+251995016195
Megenagna, Marathon Bldg, Office No. 614
Telegram:- https://t.me/BeGetEngineering
5.2K viewsENG Sintayehu Melese, 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ