Get Mystery Box with random crypto!

በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ/Variation/       ቫሬሽን/variation/ ምን አይ | Ethio Construction

በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ/Variation/  
   
ቫሬሽን/variation/ ምን አይነት ትርጉም ሊሰጠው ይችላል?

*በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ(variation) የሚባለው በዋናነት የግንባታ ስራ ጥራትን፣መጠን፣ዲዛይን፣የግንባታ ቁሳቁስ፣የስራ ጊዜ፣የግንባታ ማከናወኛ ቦታ መጠን የመሳሰሉትን የማሻሻል፣የመጨመር ወይም የመቀነስን የሚመለከት የኮንስትራክሽን ውል መሰረታዊ ነጥብ ነው፡፡
*ስለዚህ ቫሬሽን የዋናውን የኮንስትራክሽን ውል ይዘት/object of the contract/ በመጠኑ የመለወጥ ባህሪ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
*PPA 2011 ክሎስ 15.1 ይሄንኑ አረዳድ በሚያጠናክር ሁኔታ ለቫሬሽን ትርጉም ይሰጠዋል፡፡

ቫሬሽን ኦርደር/variation order/ የሚባለውስ ምንድን ነው? ማነው ኦርደር ሰጭው? በቃል ኦርደር መስጠት ይቻላል? በምን አይነት መልኩ ነው ትእዛዝ የሚሰጥ? በዚህ ረገድ ህጉ ምን ይላል?

*ቫሬሽን ኦርደር ከመሀንዲሱ ለተቋራጩ በጽሁፍ የሚሰጥ የስራ ለውጥ ትእዛዝ ነው፡፡
*አማካሪ መሀንዲሱ ለግንባታ ስራው መልካም አፈጻጸም ሲባል የስራ ለውጥ ትእዛዝ አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነ ትእዛዝ መስጠት ይችላል፡፡
*በመጀመሪያ ግን በአማካሪ መሀንዲሱ አማካይነት ለተቋራጩ ስለለውጥ ስራው ባህሪና ምንነት ማሳወቂያ/ኖቲስ/ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ኖቲስ እንደደረሰው ተቋራጩ የለውጥ ስራውን አስመልክቶ ትሮፖዛል ያቀርባል፡፡ፕሮፖዛሉም የጊዜ ማራዘሚያ/ስኬጁል፣የዋጋ ሁኔታን የሚያካትት ይሆናል፡፡(PPA 15.3)
*የስራ ለውጥ ትእዛዝ በጽሁፍ ነው መደረግ እንዳለበት PPA 2011 ክሎስ 15.2 ያስቀምጣል፡፡አንዳንዴ ግን አማካሪ መሀንዲሱ በቃል የቫሬሽን ትእዛዝ መስጠት እንደሚችል PPA 2011 ክሎስ 15.2(a) ላይ ፈቃጅ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን በቶሎ የለውጥ ስራ ትእዛዙ ወደ ጽሁፍ መቀየር ይኖርበታል፡፡
እዚህ ጋር አብሮ የሚታየው ነገር የአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎች በጽሁፍ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ይሄውም ስለውሎች በጠቅላላው በሚመለከተው የውል ህግ አንቀጽ 1724 ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
*አንድ ውል የሚሻሻለው ደግሞ ከመጀመሪያው ውል ጋር ተመሳሳይ በሆነ ፎርም ነው፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1722 ላይ "ዋናውን ውል የመለወጥ ጉዳይ ለዚሁ ውል በተደነገገው አጻጻፍ(ፎርም) መሰራት አለበት፡፡" በሚል የተደነገገው የሚያስገነዝበውም ቫሬሽን ዋናውን ውል በከፊል የመለወጥ ሁኔታ ስለሚኖረው ከዋናው የኮንስትራክሽን ውል ጋር በተመሳሳይ የአጻጻፍ ፎርም በጽሁፍ መደረግ ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ለዚህ ነው በመርህ ደረጃ ቫሬሽን በጽሁፍ መደረግ አለበት የሚባለው፡፡

የስራ ለውጥ ውል/change agreement/ ምን ማለት ነው? ከህግ አንጻር በዚህ ረገድ ምን ነጥቦች ሊነሱ ይችላሉ?

*PPA 2011 ክሎስ 15.9 ላይ እንደተቀመጠው በየስራ ለውጥ ውል የሚባለው ከቫሬሽን ኦርደር በኋላ አሰሪው/ተወካይ መሀንዲሱ እና ተቋራጩ በጽሁፍ የሚስማሙበት የማሻሻያ ውል ነው፡፡ ሆኖም በዚህ የፒፒኤ ትርጉም ጸሀፊው አይስማማም፡፡ምክንያቱም አማካሪው ስራ ለመቆጣጠር እንጅ ውል ለመዋዋል በአማካሪነት ውሉ ላይ ብዙ ጊዜ ስልጣን አይኖረውም፡፡በተቋራጭና አሰሪ መካከል የተደረገ የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ በሚደረግ ስምምነት/ውል ሊሻሻል ከሚችል በስተቀር አማካሪ መሀንዲሱን ውል እንዲዋዋል እስከመፍቀድ የሚደርስ ትርጓሜ መሰጠቱ ተገቢነት የለውም፡፡
*የስራ ለውጥ ውሎች ቀን፣ቁጥርና ቅደምተከተል ይሰጣቸዋል፡፡(ፒፒኤ15.10)
*ሌላው የስራ ለውጥ ውል ወደኋላ ሄዶ እንደማይሰራና ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ብቻ አስገዳጅ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.10 ላይ ተቀምጧል፡፡

በቫሬሽን የተሰሩ ስራዎች የዋጋ አወሳሰን/Valuation of variation/ በምን ሁኔታ ይከናወናል?

*የተሰራው ተጨማሪ ስራ ከሆነ እና በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ላይ ዋጋ ተተክሎለት ካለ በዚያው የዋጋ ሬት የሚሰላ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.5(a) ላይ ተቀምጧል፡፡
*በቫሬሽን የሚሰራው ስራ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ያልተካተተ አዲስ የስራ አይተም ከሆነ በመሀንዲሱና ተቋራጩ በስምምነት በወቅታዊ ዋጋ የሚሰላ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.5(b) ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
*በቫሬሽን የተካተተው የስራ አይተም ዋጋው በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ላይ የተካተተ ቢሆን እንኳ የተጋነነ ከሆነ በመሀንዲሱ ሊስተካከል እንደሚችል ደግሞ PPA 2011 ክሎስ 15.5(c) ይገልጻል፡፡
*ቫሬሽኑ የተከሰተው በተቋራጩ ጥፋት ከሆነ ደግሞ በአሰሪው ለተቋራጩ ዋጋ አይከፈልበትም በሚል PPA 2011 ክሎስ 15.5(d) በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

ቫሬሽን እስከስንት ፐርሰንት ይፈቀዳል? በፍርድ ቤቶች አካባቢ ያለው የህጉ አረዳድስ ምን ይመስላል?

*የቫሬሽኑ መጠን ከ25% በላይ በሆነ ጊዜና ከተቋራጩ ጥፋት ባልሆነ ሁኔታ የተከሰተ ከሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ስለብልጫው መጠንና ስለዋጋው ከአሰሪው መስሪያ ቤት ጋር በመመካከር ይወስናል በሚል PPA 2011 ክሎስ 15.7 ላይ ተቀምጧል፡፡
የቫሬሽን መጠን ከመጀመሪያው ዋጋ ከ30% በላይ መብለጥ እንደሌለበት በአስገዳጅ ሁኔታ PPA 2011 ክሎስ 15.8 ላይ ተቀምጧል፡፡
*በዚህ በጀኔራል ኮንዲሽን ከተቀመጠው ተርሰንት/ከገደቡ በላይ በቫሬሽን ስራ ተሰርቶ ቢገኝስ ምን ይሆናል? እንግዲህ በዚህ ረገድ ጀኔራል ኮንዲሽኑም ሆነ አግባብነት ያለው የግዥ አዋጅና መመሪያ ግልጽ ምላሽ አያስቀምጥም፡፡ ሆኖም ግን ተቋራጩ ስራውን እስከሰራው ድረስ አሰሪው አላግባብ በተቋራጩ ድካምና ገንዘብ በልጽጐ እንዲቀር ፈቃጅ ህግ ሊኖር አይችልም፡፡ፍትሀዊም አይሆንም፡፡
*ስለዚህ በዚህ ረገድ በአማካሪ መሀንዲሱ እውቅና እና ትእዛዝ በቫሬሽን ለተሰሩ ስራዎች  ከገደቡ በላይ ያለፈ ቢሆንም እንኳ አሰሪው ለተቋራጩ ሊከፍለው እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ5ዳኞች እንደህግ በሚቆጠር ሁኔታ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ ይሄውም አስገዳጅ ውሳኔ በሰ/መ/ቁ 71972 ቅጽ 14 ገጽ 25 ላይ ይገኛል፡፡ 
ቫሬሽን ከሙስና ጋር ምን ያገናኘዋል?
*በዚህ ረገድ የኢፌዴሪ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የኪራይ ሰብሳቢነት መንስኤዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በሚል በመስከረም 2010ዓ.ም ባዘጋጀው የውይይት ሰነድ ላይ ቫሬሽን ለሙስና አንዱ ምንጭ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
*ይሄውም ለምሳሌ ያህል የማይጣጣሙ ዲዛይኖችና የስራ ዝርዝር መኖር አንዱ ነው፡፡
*ሌላኛው ደግሞ ሆነ ብሎ የስራ ዝርዝር መዝለል/omission of work item/ ነው፡፡
በአይነቱ አዲስ የሆነ ተጨማሪ ስራ/unrelated and new item of additional work/ ሲያጋጥምስ በየትኛው ህግ የሚታይ ይሆናል?
*በመርህ ደረጃ አሰሪው መስሪያ ቤት በውል ውስጥ የሌሉትን ስራዎች በአዲስ ዋጋ እንዲሰራቸው ስራ ተቋራጩን ለማዘዝ እንደሚችል በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3284(1) ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡


https://t.me/ethioengineers1