Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction
የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.69K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-15 21:46:32
answer

Suppose the dimensions of a slab are
- length = 4.5m
- width = 3.6m
- thickness = 15cm = 0.15m
- mix ratio = 1:2:4

I, Find the the volume of concrete
II, how many bag of cements required
III, find the volume of sand required
Iv, find the volume of aggregate required
v, what’s the grade of the concrete 
   given the mix ratio


https://t.me/ethioengineers1
2.3K viewsENG Sintayehu Melese, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 19:25:53 EXTERNAL VACANCY
2.2K viewsENG Sintayehu Melese, 16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 16:28:28
BeGet Engineering Plc, Class Starting May 1
Class Option 1, For 2 Months Advanced Level Package
Class Option 2, For Separate Software Need
( online options are also available! )
+251995016195 / 0116686857
For more join @BeGetEngineering
1.0K viewsBelay #1, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 21:56:39 𝕡𝕣𝕚𝕞 𝕔𝕠𝕒𝕥/ፕራይም ኮት

ለአዲሥ ቤት ሠሪዎች ትልቅ የምሥራች፤

◆ ለልሥን ሥራ የሚዉል አዲሥ ቴክኖሎጂ፤

◆ የተለመደዉን ልሥን(cement plastering) ሥራን ሙሉ በሙሉ የሚያሥቀር፤

◆ prime coat ሲጠቀሙ ሚያገኙዋቸዉ ጥቅሞች፦

     ❶ ገንዘብ ቆጣቢ ነዉ፤ cement plastering ሰለሚያሥቀር፤

     ❷ ጊዜና ጉልበት ይቆጥባል
ምንም ሣያሥፈለግዉ ወዲያዉ እንዳለቀ በ48 ሠዐት ውሥጥ ቀጣዩን ሥራችን መጀመር ያሥችለናል፤

   ❸ ምንም ዓይነት side effect/የጎንዮሽ ጉዳት በባለሙያዎች ላይ የለዉም፤

☞ prim coat ቀጥታ
        ◆block     ◆beam
         ◆column ◆slab
ላይ መጠቀም እንችላለን፤

☞ ትላልቅ ፕሮጀክቶች አና ህንፃወች እሄን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፤

☞ ከፈለጉ እቃዉን ይዘዙን፤ ፕራይም ኮት (material) እና ጂፕሰም ያሉበት ቦታ ድረሥ አናመጣለን፤

☞ ብቁ እና የሠለጠኑ ባለሞያወች አሉን፤

☞ በተመቾት ጊዜ ደዉለዉ ያናግሩን፤
       

0953138434 /0912285606


ወይም @Ethiocon143bot
1.7K viewsENG Sintayehu Melese, edited  18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 20:53:31 የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት ሲሚንቶ ለማገበያየት ያዋጣው እንደኾነ ለመወሰን ጥናት እያደረገ መኾኑን ሪፖርተር አስነብቧል። ድርጅቱ ጥናቱን አጠናቆና ከመንግሥት አስፈቅዶ ግብይቱን ከጀመረ፣ በኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ግብይት ሲሚንቶ በድርጅቱ ታሪክ የመጀመሪያው ይኾናል። የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት አንድን ምርት ለማገበያየት ፍቃድ የሚያገኘው ከንግድ ሚንስቴር ነው። የሲሚንቶ የአገር ውስጥ ምርትና ግብይት በአሁኑ ወቅት በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ የተያዘ እንደዳኾነ በተደጋጋሚ ተነግሯል

ዋዜማ።


https://t.me/ethioengineers1
1.9K viewsENG Sintayehu Melese, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 21:45:01 እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
@BeGetEngineering
616 viewsBelay #1, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:43:09
Class Option 2, For Separate Software Need
+251995016195 / 0116686857
https://t.me/BeGetEngineering
1.9K viewsBelay #1, 11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:43:09
Class Option 1, For 2 Months Advanced Level Package
+251995016195 / 0116686857
https://t.me/BeGetEngineering
1.9K viewsBelay #1, 11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 20:51:24 የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 መሰረት የአዋጁን ድንጋጌዎች በመተላለፍ የግንባታ ሥራ ፈቃድን በሚሰጡ የመንግሥት ኃላፊዎች እና ይህንኑ እንዲያከናውኑ ሃላፊነት በተሰጣቸው ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች፣ በተመዘገቡ ባለሙያዎች ወይም ሥራ ተቋራጮች፣ እንዲሁም በግንባታ ባለቤቶች የሚፈፀሙ ጥፋቶች እንደሁኔታው ከ6 ወር ጀምሮ እስከ 15 አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ500 (አምስት መቶ) ብር እስከ 50000 (ሀምሳ ሺ) ብር የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በ1996 የወጣው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 501 የህንጻ ስራ ደንቦችን መጣስ በሚል ርእስ ስር ማንም ሰው ማንኛውንም አይነት የህንጻ ስራ ወይም የህንጻ ማፍረስ ስራ ሲቆጣጠር፣ ሲመራ ወይም ሲፈጽም በህግ የተደነገገውን ወይም በህንጻ ስራ ሙያ ወይም ልምድ የሚሰራባቸውን የጥንቃቄ ደንቦችን አስቦ በመጣስ የህዝብን ደህንነት ወይም የሰዎችን ሕይወት፣ ጤንነት ወይም አካል ወይም የሌላውን ሰው ንብረት አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ ከ3 ወር በማያንስ ቀላል እስራት እና በመቀጮ የሚቀጣ ሲሆን ወንጀሉ የተፈጸመው በቸልተኝነት እንደ ሆነ ከ1 አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና በመቀጮ እንደሚያስቀጣ ያመለክታል፡፡

በአጠቃላይ ማንኛውም የሕንፃ ግንባታ ሥራ በሚከናወንበት ወቅት ጉዳት እንዳያደርስ የግንባታ ሥፍራውን ተቀባይነት ባላቸው ቁሶች መከለል፣ በቁፋሮ ወቅት ከመሬት በታች ሊኖሩ የሚችሉ የመሠረተ ልማት መሥመሮች እንዳይጎዱ፣ በአካባቢው የትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል፣ ተቀጣጣይነት ያላቸውን የግንባታ ቁሳቁሶች በአያያዝ ጉድለት ለእሳት አደጋ እንዳይጋለጡ በማድረግ፣ በግንባታ ሥራ ላይ ለተሠማሩ ሠራተኞችና ጐብኚዎች የደህንነት መጠበቂያዎችን በማሟላት፣ ለግንባታ የሚውሉ የኬሚካል ውጤቶች በአጠቃቀም ወቅት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ እና ብናኝ ጭስና አንጸባራቂ ጨረር የመሳሰሉ አዋኪ ነገሮች አካባቢውን እንዳይረብሹ ተገቢው ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይክቶሬት የተዘጋጀ


https://t.me/ethioengineers1
960 viewsENG Sintayehu Melese, edited  17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 20:51:24 በግንባታ ወቅት መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች

በአሁኑ ወቅት የግንባታው ዘርፍ ለቡዙ ዜጎች የስራ እድልን በመፍጠር ለአገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ይሁንና አብዛኛው የሕንጻ ግንባታዎች በህንጻ ህጉ መሰረት በግንባታ ወቅት ማደረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ባለማድረጋቸው የተነሳ በሰው ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ከፈተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የሕዝብ ጤንነትና ደህንነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የሕንፃ ግንባታ ወይም የሕንፃ ግንባታ ማሻሻያና የአገልግሎት ለውጥን በተመለከተ በሀገሪቱ በአጠቃላይ ተፈፃሚ የሚሆን ዝቅተኛውን ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አገራችንም የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 እና እሱን ለማስፈጸም የወጣ የሚንስትሮች ምክር ቤት የሕንጻ ደንብ 243/2003 ወጥቶ በስራ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ጽሁፍ በህጉ ላይ ስለተደነገገው እና በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባ ጥንቃቄ እና ይህንኑ ጥንቃቄ ያለማድረግ ስለሚያስከትለው ሀላፈነት በአጭሩ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

የግንባታ ምንነት እና የሕንፃ አይነቶች በአገራችን ህግ
የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 በአንቀጽ 2 ስር ለተለያዩ ቃላቶች ትርጓሜን የሚሰጥ ሲሆን ይህም፡-
“ግንባታ” ማለት አዲስ ሕንፃ መገንባት ወይም ነባር ሕንፃን ማሻሻል ወይም አገልግሎቱን መለወጥ ነው በማለት ትሩገጓሜ የሰተው ሲሆን፣

“ሕንፃ” ማለት ለመኖሪያ፣ ለቢሮ፣ ለፋብሪካ ወይም ለማናቸውም ሌላ አገልግሎት የሚውል ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ግንባታ ነው፤ በማለት ይገልጸዋል፡፡

የሕንፃ አይነቶች
የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ በአጠቃላይ በአገራችን የሚገኘውን የህንጻ አይነቶችን በሶስት የሚመድብ ሲሆን ይህም፡-

1ኛ ምድብ ‘ሀ’ ሕንፃ
ማለት በሁለት የኮንክሪት ወይም የብረት ወይም ሌሎች ስትራክቸራል ውቅሮች መካከል ያለው ርቀት 7 ሜትር ወይም ከዚያ በታች የሆነ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ወይም ማናቸውም ከሁለት ፎቅ በታች የሆነ የግል መኖሪያ ቤት ነው፡፡

2ኛ ምድብ ‘ለ’ ሕንፃ
ማለት በሁለት የኮንክሪት ወይም የብረት ወይም ሌሎች ስትራክቸራል ውቅሮች መካከል ያለው ርቀት ከ7 ሜትር በላይ የሆነ ወይም ባለሁለት ፎቅና ከሁለት ፎቅ በላይ የሆነና በምድብ ‘ሐ’ የማይሸፈን ሕንፃ ወይም በምድብ ‘ሀ’ የተመደበ እንደሪል ስቴት ያለ የቤቶች ልማት ነው፡፡

3ኛ ምድብ ‘ሐ’ ሕንፃ
ማለት የሕዝብ መገልገያ ወይም ተቋም ነክ ሕንፃ፣ የፋብሪካ ወይም የወርክሾፕ ሕንፃ ወይም ከመሬት እስከ መጨረሻው ወለል ከፍታው ከ12 ሜትር በላይ የሆነ ማናቸውም ሕንፃ ነው፡፡

በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች
የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 እና ይህን ለማስፈጸም በወጣው የሚንስትሮች ምክር ቤት የሕንጻ ደንብ ቁጥር 243/2003 መሰረት በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች በመዘርዘር የሚያስቀምጡ ሲሆኑ ይህም፡-

 ማንኛውም ግንባታ በግንባታው አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን፣ የግንባታው ሠራተኞችን፣ የሌሎች ግንባታዎችን ወይም ንብረቶችን ደህንነት በማያሰጋ መንገድ ዲዛይን መደረግና መገንባት አለበት፡፡

 ማንኛውም የሕንፃ ባለቤት አዲስ የሕንፃ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት በአካባቢው ቀደም ብሎ የተሠሩ ሕንፃዎችን እና የመሠረተ ልማት አውታሮችን አገልግሎት የሚያውኩ፣ የአካባቢውን ወይም አዋሳኙን ደህንነትና ጤንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ እና የትራፊክ ፍሰትን የሚያስተጓጉሉ ሁኔታዎችን ማስወገድና ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡

 ከግንባታ ጋር የተያያዘ ቁፋሮ የማንኛውንም ንብረት ወይም አገልግሎት ደህንነት ጉዳት ላይ የሚጥል ሲሆን የግንባታ ቦታው ባለቤት የንብረቱን ወይም የአገልግሎቱን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡ ለሚሠሩ ግንባታዎች የሕንፃው ባለቤት የሚከተላቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በጽሁፍ እንደአስፈላጊነቱም በዲዛይንና በዝርዝር ትንታኔ በማስደገፍ ለሕንፃ ሹሙ በማቅረብ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

 አጎራባቹ የቴክኒክ ዕውቀት ካለው በራሱ፣ ከሌለው ደግሞ በሚወክለው ባለሙያ ገንቢው የሚያደርገው የቅድሚያ ጥንቃቄ ዝግጅት ንብረቱን ከአደጋ መከላከል መቻሉ እንዲገለጽለት መጠየቅ እና በግንባታም ወቅት ከግንባታው ባለቤት ጋር በመነጋገር መከታተል ይችላል፡፡
 የተቆፈረው ጉድጓድ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ወይም በጉድጓዱ ውስጥ መሠረት በሚገነባበት ጊዜ ባለቤቱ ወይም ቁፋሮውን ያካሄደው ሰው ጉድጓዱን ለደህንነት በማያሰጋ ሁኔታ መጠበቅ አለበት፡፡

 ከግንባታ ጋር የተያያዘ ቁፋሮ የማንኛውንም ንብረት ወይም አገልግሎት ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል መሆኑ ሲገመት የግንባታ ቦታው ባለቤት በቅድሚያ የመከላከያ ዘዴዎችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለከተማው አስተዳደር ወይም ለተሰየመው አካል በማቅረብ የፅሁፍ ፈቃድ ማግኘት አለበት፡፡

 ማንኛውም አዲስ የሚገነባ ህንፃ መሠረት ጭነት በነባር መሠረቶች፣ የአገልግሎት መስመሮች ወይም ሌሎች ሥራዎች ላይ ችግር የሚፈጥር መሆን እንደሌለበት በህጉ ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎችን አለማድረግ ሚያስከትልው ሀላፊነት

በግንባታ ወቅት መደረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ባለማድርግ የሚደርስን ጉዳት በተመለከተ የፍትሐብሄር ተጠያቂነት እንዳለ ሆነ በህንጻ አዋጅ እና ደንቡ ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ የግንባታ ሥራ ፈቃድን በሚሰጡ የመንግሥት ኃላፊዎች እና ይህንኑ እንዲያከናውኑ ሃላፊነት በተሰጣቸው ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች፣ በተመዘገቡ ባለሙያዎች ወይም ሥራ ተቋራጮች፣ አንዲሁም በግንባታ ባለቤቶች ለሚፈፀሙ ጥፋቶች እንደ ሁኔታው አስተዳደራዊ መቀጮ እና የወንጀል ተጠያቂነት እንዳለባቸው በህጉ ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

አስተዳደራዊ መቀጮ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሕንጻ ደንብ ቁጥር 243/2003 ላይ የወንጀልና የፍትሐ ብሔር ኃላፊነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁን ወይም ይህንን ደንብ በሚተላለፍ የግንባታ ባለቤት ላይ የከተማው አስተዳደር ወይም የተሰየመው አካል እንደ ሕንፃው ደረጃ የገንዘብ መቀጮን ይጥላል፡፡ ለአብነትም በግንባታ ወቅት መወሰድ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ሳይወስድ በምድብ ለ ህንጻ ስር የሚመደብ ህንጻ መገንባት በ3000 (ሶስት ሺ) ብር የገንዘብ መቀጮ ያሚያስቀጣ ሲሆን የሚሰራው ህንጻ ምድብ ሐ ህንጻ ሲሆን ቅጣቱ በ5000 (አምስት ሺ) ብር የገንዘብ መቀጮ ይሆናል በማለት ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ሌላው የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 አንቀጽ 56 መሰረት በአዋጁ ላይ በተመለከቱት የህግ መጣስ ተግባሮች ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ የተመዘገበ ባለሙያ ወይም ሥራ ተቋራጭ በፍርድ ከተወሰነበት የእሥራት ቅጣት በተጨማሪ ጥፋተኛው ከአምስት ዓመት ጀምሮ ጥፋተኛ በተባለበት አንቀጽ እስከ ተመለከተው ከፍተኛ የእሥራት ዘመን ድረስ የሙያ ወይም የሥራ ፈቃዱ ይታገዳል በማለት አስቀምጧል፡፡

የወንጀል ተጠያቂነት
936 viewsENG Sintayehu Melese, 17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ