Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction
የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.69K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-09 10:38:59
ግድብ (Dam) ማለት ገዝፈ አካል ሲሆን የውንዝን ሸለቆ ላይ ተገንብቶ የውሃን ተፋሰስ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚገታ ነው።

ይህ መግታት (blockage) በውሃ ተፋሰስ ላይ መታቆርን (reservoir) ይፍጥራል ይህም ወሃውን ለተፈለገው አገልግሎት እንዲውል ቀሊል ያደርገዋል ። ይህ አጋጅ ገዝፈ አካል ወይም ግድብ ከተለያዩ ቁሶች ይሰራል ፦ ኮንክሪት፣ የድንጋይና አፈር መደምደም (compaction) ወዘተ...
.
ግድም በዋነኛነት ለነዚህ አገልግሎቶች ይገነባል፦
1- ጎርፍን ለመቆጣጠር - for flood control
2- ለውሃ አቅርቦት እና የመስኖ ስራ - for water supply and irrigation
3- የኤሌትሪክ ሃይልን ለማመንጨት - for electric power generation
4- የአንድን ወንዝ ፍሰት ለመመጠን እና ለመቆጣጠር - for regulation or balancing of a river flow

#Hydraulics
3.3K viewsENG Sintayehu Melese, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 10:38:59
የከተማ ባለብዙ ወለል ህንጻዎች

የከተማ ባለብዙ ወለል ህንጻዎች፣ አቀማመጣቸውና የውጭ ቅርጻቸው ከብርሀን እና ከንፋስ አንጻር እንዴት መሆን እንዳለበት አሳብ የሚሰጡ ምስሎች ተያይዘዋል፡፡

Via 07sketches


https://t.me/ethioengineers1
2.2K viewsENG Sintayehu Melese, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 04:35:58 ለግንባታ ከሚውሉ ቁሳቁሶች ውስጥ ኮንክሪት፣ የአስፋልት ኮንክሪት፣ እንደ ብረት እና አልሙኒየም ያሉ ጠንካራ ብረታ ብረቶች፣ የፕላስቲ ውጤቶችና የመሳሰሉት ይገኙበታል።

የቁሶች ጥናት የግንባታ አካላትን ከተለያየ ጥቃት ለመከላከል የሚውሉ ቅባቶችና የመከላከያ ንጣፎችን፣ እንዲሁም አንድን የብረት አይነት ከሌላ የብረት አይነት ጋር
በማደባለቅ ለግንባታ ተስማሚ የሆነ ሌላ አይነት የብረት አይነት ማምረት የመሳሰሉ ስራዎችንም ያጠቃልላል።

የቁሶች ጥናት የትግበራ ፊዚክስና (applied physics) የኬሚስትሪ
እውቀቶችን የያዘ የምህንድስና ዘርፍ ነው።

በቅርቡ እየተስፋፋ የመጣው የናኖ ሳይንስ ወይም ቴክኖሎጂን (ናኖ ሳይንስ የአንድን ቁስ የአቶምና የሞሎኪዮል አወቃቀር በመቀየር በተፈጥሮ የማይገኙ ለየት ያለ ባህሪ ያላቸውን ቁሶች ለመስራት የሚደረግ ጥረት ነው) ደረጃ
ተንተርሶ በአሁኑ ጊዜ የቁሶች ጥናት ከፍተኛ የሆነ የምርምር ድርሻን
ይዞ ይገኛል። የቁሶች ጥናት ምህንድስና በምርምር ምህንድስናና
የግንባታ አካላት ከጥቅም ውጪ የመሆን መንስኤን ለማጥናት
በሚደረጉ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

8,
የአወቃቀር ምህንድስና (ስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ)

የአወቃቀር ምህንድስና የህንጻዎችን፣ የድልድዮችን፣ የማማዎችን፣
ማቋረጫ ድልድዮችን፣ የዋሻዎችን፣ በባህርና ላይ የሚገነቡ
ለነዳጅ ወይም ለዘይት ማውጫ የሚያገለግሉ ሰው ሰራሽ መሬቶችን
እና ማማዎችንና እንዲሁም እነኚህን የመንገድየመሳሰሉ የግንባታ አካላትን
በተመለከተ የአወቃቀር ንድፍና (structural design) የአወቃቀር
ትንታኔ (structural analysis) ላይ  የሲቪል ምህንድስና
ዘርፍ ነው።
የአወቃቀር ትንታኔ (structural analysis) ጉልበቶች በግንባታ
አካላት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ የሚያተኩርመመዘን ላይ ትኩረት ያደርጋል።
የአወቃቀር ምህንድስና በግንባታ አካላት ላይ የሚያርፉ ጉልበቶችን
ለምሳሌ የራሱ የግንባታ አካሉ ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ የሚያርፉ
ሌሎች ቋሚና ተቀሳቃሽ ክብደቶች፣ የንፋስ ግፊት ፣ የሙቀት ለውጥ፣
የውሃ ግፊት፣ የመሬት ጫና፣ የመሬት ፣ በረዶ እና የመሳሰሉትን
የመለየትና፣ በእነኝህ ጉልበቶች አማካኝነት በግንባታ አካላቱ ውስጥ
የሚከሰቱ ውስጣዊ ጫናዎችንና ርእደትጉልበቶችን (internal stresses
and forces) የማስላትና የግንባታ አካላቱ እነኝህን ጉልበቶች
ተቋቁመው አገልግሎት እንዲሰጡ መጠናቸውንና የሚሰሩበትን ቁስ
ላይ ያተኩራል። የአወቃቀር ምህንድስና ባለሙያው የግንባታ
አካላቱ ተጠቃሚዎችን ደህንነትን መንደፍበሚጠብቅ መልኩ (llimit state of
carrying capacity) እንዲሁም ግንባታ አካላቱ ከተሰሩበት አላማ
አንጻር የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጎ (limit state
of serviceablity) መንደፍ ይጠበቅበታል።
እንደ ንፋስ እና የመሬት ርእደት አይነት ጉልበቶች በቀላሉ ለመተንበይ
አስቸጋሪ በመሆናቸው በአወቃቀር ምህንድስና ስር እንደ ንፋስ
ምህንድስና እና የመሬት ርእደት ምህንድስናን የመሳሰሉ ንኡስ ዘርፎች
እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኖዋል።
በአወቃቀር ምህንድስና ውስጥ የንድፍና የትንታኔ ስራ የግንባታ አካሉ
ቋሚ ጉልበቶችን ፣ተለዋዋጭ ጉልበቶችን (እንደ ንፋስና የመሬት ርእደት
ያሉ) ወይም ጊዜያዊ ጉልበቶችን (ለምሳሌ በግንባታ ጊዜ ጥቅም ላይ
የግንባታ ማሽኖች ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ በተንቀሳቃሽ
ነገሮች አማካኝነት ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶች እና የመሳሰሉት)
የሚውሉለመሸከም የሚያስፈልገውን ጥንካሬና ጠጣርነት መወሰን እንዲሁም
የግንባታ አካሉ ሚዛኑን ጠብቆ መቆም መቻሉን ማረጋገጥ ያካትታል።
ከዚህም በተጨማሪ የንድፍና ትንታኔ ስራ  ዋጋ መተመን፣
የግንባታውን ተግባራዊነት ማረጋገጥ፣ ግንባታው ውበት የተላበሰ
መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም የሃብት የግንባታውንአጠቃቀምና የተፈጥሮ ሚዛንን
በጠበቀ መልኩ ግንባታው እንዲከናውን ማስቻልን ያካትታል።

9,ቅየሳ

ቅየሳ የአንድን የመሬት ገጽ ወይም የግንባታ አካል አቀማጥ ለማወቅ
የሚደረግ የልኬት ስራ ነው። የቅየሳ ስራ  ስራ የሚውሉ እንደ
ውሃ ልክ (level) ወይም ቴዎዶላይት (አግድምና ሽቅብ ማእዘንን
ለመለካት የሚችል አጉሊ መነጽር) ያሉ ለቅየሳመሳሪያዎች በመጠቀም
በሁለት የልኬት ቦታዎች መካከል ከልኬት ቦታው አንጻር የሚኖረውን
የቦታ ልዮነት ለማወቅ የማእዘን (angle) ፣ የአግድም ቁመትና
የሽቅብ ቁመት ልኬቶችን በመውሰድና የሂሳብ ስሌትን በመጠቀም
የመሬት ገጽን ወይም የግንባታ አካልን አቀማመጥ የመወሰን ተግባር
ነው። ከኮምፒውተር እውቀት ማደግ ጋር በተያያዘ አውቶማቲክ የሆኑ
እንደ የኤሌክትሪክ ርቀት መለኪያዎች በመፈልሰፋቸው እንደ ቶታል
ስቴሽን ፣ ጂፒኤስ፣ የጨረር ዳሰሳ (laser scanning) የመሳሰሉ
መሳሪያዎች ባህላዊ የሆኑ መሳሪያዎችን በመተካት ላይ ናቸው።
ትራንስፖርት ምህንድስና
የትራንስፖርት ምህንድስና ሰዎችንና ቁሳቁስን ከቦታ ወደ ቦታ በደህንነት
፣ በተቀላጠፈና ምቹ በሆነ መንገድ ማጓጓዝ ላይ ትኩረት ያደርጋል።
ይህንን አላማማ ለማሳካትም የመኪና፣ የባቡር፣ የውሃና የአየር ማረፊያ
መንገዶች እንዲሁም የወደቦች ንድፍ፣ ግንባታና ጥገና ስራዎች
በትራንስፖርት ምህንድስና ውስጥ ሰፊ ድርሻ ይይዛሉ። የትራንስፖርት
ምህንድስና በውስጡ የትራንስፖርት ንድፍ ስራ (transportaion
design) ፣ የትራንስፖርት ግንባታ እቅድ (transportation
planning)፣ የትራፊክ ምህንድስና (traffic engineering)፣ የከተማ
ልማት ምህንድስና፣ የመንገድ ንጣፍ ምህንድስና የመሳሰሉ ንኡስ
የሙያ ዘርፎችን የያዘ ነው።


https://t.me/ethioengineers1
2.5K viewsENG Sintayehu Melese, 01:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 10:45:21 ዋና ዋና የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች

1,የወደብ (የባህር ዳርቻ) ምህንድስና

የወደብ ምህንድስና የወደብ አካባቢን የማልማትና የማስተዳደር
ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ ወደብን ለመጓጓዣ ስራ ከማዋል
በተጨማሪ፣ በወደብ አካባቢ የሚከሰቱ የውሃ መጥለቅለቅ
አደጋዎችን፣ የአፈር መሸርሸርና እና የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን
የመከላከል ስራ የሚያከናውን የምህንድስና ዘርፍ ነው።


2,የግንባታ ምህንድስና

የግንባታ ምህንድስና የግንባታ ሂደትን የማቀድ፣ የማስፈጸም፣
ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝና የማቅረብ፣
እንዲሁም የግንባታ ቦታውን ለሚፈለገው የግንባታ አካል እንዲውል
በግንባታው አካባቢ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ መሟላቱን
የማረጋገጥ፣ የግንባታ ቦታው ለግንባታ ስራ ደህንነትና ምቹነት ያለው
መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም አግባብ የሆነ የግንባታ መሬት
አጠቃቀምን የሚከታተልና የሚያስፈጽም የምህንድስና ዘርፍ ነው።
የግንባታ ተቋራጮች በሌሎች የሲቪል ምህንድስና አገልግሎቶች ላይ
ከተሰማሩ የአገልግሎት ተቋሞች አንጻር የተሰማሩበት መስክ ከፍተኛ
የንግድ አደጋ ወይም መዋዠቅ ስለሚከሰትበት የግንባታ መሃንዲሶች
አብዛኛውን ጊዜያቸውን ንግድን በተመለከቱ ጉዳዮች ለምሳሌ ያህል
የግንባታ ውሉን በመገምገም እና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን
ጉዳዮች በማርቀቅ፣ የግንባታ ግብአቶችን አቅርቦት ፍሰት
በመቆጣጠር፣ እንዲሁም የግንባታ እቃዎች የገበያ ዋጋ መረጃን
በመሰብሰብ ላይ ያውላሉ።

3,የመሬት ርዕደት ምህንድስና

የመሬት ርዕደት ምህንድስና መሬት ርዕደት በሚያይልባቸው አካባቢዎች
የሚሰሩ የግንባታ አካላት፤ የመሬት ርዕደትን ተቋቁመው እንዲዘልቁ
ለማድረግ የግንባታ አካላቱን አወቃቀር በተለየ መልኩ ትኩረት
በመስጠት የሚያጠናና መፍትሄ የሚሰጥ የምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ
የምህንድስና ዘርፍ የአወቃቀር ምህንድስና ዘርፍ አካል ነው። የመሬት
ርዕደት ምህንድስና ዋነኛ አላማው በመሬትና በግንባታ አካሉ እንዲሁም
በግንባታ አካላቱ መካካል በመሬት ርዕደት ጊዜ የሚኖረውን
መስተጋብር መረዳትና የግንባታ አካሉ የመሬት ርዕደት ሂደቱን አልፎ
አገልግሎት እንዲሰጥ አወቃቀሩን፣ የግንባታ ቁስ አመራረጡን
እንዲሁም መሰል የግንባታ መፍትሄዎችን በየሀገራቱ ጥቅም ላይ ከዋሉ
የግንባታ መስፈርቶች ጋር በሚስማማ መልኩ መተግበር ነው።


4,የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና

የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ከጤና ጥበቃ ምህንስና ጋር ተጓዳኝ የሆነ
የምህንድስና ዘርፍ ሲሆን፣ የጤና ጥበቃ ምህንድስና በአመዛኙ የንጹህ
ውሃ መጠጥ አቅርቦትና የአካባቢ ቆሻሻ ፍሳሽ አወጋገድ ላይ ሲያተኩር፤
የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ሰፋ ባለ መልኩ የአካባቢ ብክለት
የሚያስከትሉና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ጎጂ ኬሚካሎችን እና ቆሻሻዎችን
መቆጣጠርና ማስወገድ ይጨምራል። የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና፤
የማህበረሰብ ጤና ምህንድስና እና የአካባቢ ጤና ምህንድስና በሚል
አጠራርም ይታወቃል።
የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና በኬሚካል ውህደቶች፣ በባዮሎጂካል
ሂደቶች እንዲሁም በሙቀት ለውጥ አማካኝነት የሚፈጠሩ ቆሻሻዎችን
የማጥራትና የማስወገድ፣ አየርንና ውሃን የማጣራት፣ እንዲሁም በአደጋ
ወይም በቆሻሻ ክምችት የተበከለን የመሬት አካል ወደ ተፈጥሮዋዊ
ይዘቱ የመመለስ ስራዎች የሚያከናወኑበት የምህንድስና ዘርፍ ነው።
በአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ትኩረት ከሚደረግባቸው ዋና ነጥቦች
ውስጥ የመርዝ ወይም የኬሚካል እንቅስቃሴ ወይም ጉዞ (ከመሬት
ላይና ከመሬት በታች)፣ የውሃ ማጣራት፣ የቆሻሻ ፍሳሽ ማጣራት፣
የአየር ብክለት፣ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና የአደገኛ ቆሻሻዎች አያያዝ
ይገኙበታል። የአካባቢ ጥበቃ መሃንዲሶች ብክለትን የመቀነስ፣
የአረንጓዴ ምህንድስና ዘርፍ ስራዎች (የአካባቢ ብክለትን የሚቀንሱ
የግንባታ መንገዶችንና ቁሶችን የኢኮኖሚ አቅምን ባገናዘበ መልኩ
የማጥናት ስራ)፤ እንዲሁም የኢንዱስትሪዎችን የቁሳቁስና የሃይል
አጠቃቀም ፍሰት የማጥናት ስራዎችና (industrial ecology)
የመሳሰሉት ላይ ይሳተፋሉ። ከዚህም በተጨማሪ የአካቢቢ ጥበቃ
መሃንዲሶች ድርጊቶች (ለምሳሌ የአንድ የግንባታ አካል ትግበራ)
በአካባቢው ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተጽእኖ በመገምገም መረጃ
ያዘጋጃሉ።

5,የምርመራ ምህንድስና

የምርመራ ምህንድስና የግንባታ አካላት የሚፈለግባቸውን ጥቅም
ሳይሰጡ ለአገልግሎት ከታቀደላቸው ጊዜ በፊት በመፍረስ አገልግሎት
መስጠት ሲያቆሙ፣ እንዲሁም የመፍረስ አደጋው በሰው ወይም
በንብረት ላይ አደጋ በሚያደርስበት ጊዜ የግንባታ አካሉን አወቃቀር ፣
የተሰራበትን ቁስ ፣ የግንባታውን ጥናት እንዲሁም መሰል ተዛማጅ
ጉዳዮችን በመመርመር ተጠያቂ የሚሆነውን አካል ለማወቅና የፍርድ
ሂደትን ለማገዝ የሚያገለግል የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ከዚህም
በተጨማሪ ይህ የምህንድስና ዘርፍ ከምርመራ ውጤቶች በመነሳት
የግንባታ ቁሶችን ወይም የግንባታ አካላት ጥራትን እንዲሁም የግንባታ
አካላት አወቃቀርን የማሻሻል ስራዎን ለመስራት የሚያስችል የሲቪል
ምህንድስና ዘርፍ ነው። ልዮ የሆነ የባለቤትነት ፍቃድ (patent)
ያላቸውን የግንባታ ቁሶች ፣ አካላት ፣ ወይም የግንባታ ዘዴዎች የፍቃድ
ባለቤቱን ይሁንታ ሳያገኙ በሚፈጸሙ ግንባታዎች ላይ የባለቤትነት
ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚደረጉ ህጋዊ ሂደቶች ላይ ይህ የምህንድስና
ዘርፍ ቁልፍ ቦታ አለው።

6,መሬት ነክ ምህንድስና (ጂኦቴክኒካል ምህንድስና)

መሬት ነክ ምህንድስና የግንባታ አካላትን የሚሸከሙ አለቶችና አፈሮችን
የምህንድስና ጠባይ የሚያጠና የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ
ዘርፍ ከአፈር ሳይንስ፣ ከቁስ ሳይንስ ፣ ከሜካኒክስ እንዲሁም የፍሰት
ሳይንስ (hydraulics) እውቀቶችን በመጠቀም ደህንነታቸው
የተጠበቀና የገንዘብ አቅምን ያገናዘቡ የግንባታ መሰረቶችን፣
የመጠበቂያ ግድግዳዎችን፣ ግድቦችን፣ ዋሻዎችን የመሳሰሉ የግንባታ
አካላትን መንደፍና መገንባት ላይ ትኩረት ያደርጋል ።
የከርሰ ምድር ውሃን በተለያዮ ምክንያቶች ከመበከል የመጠበቅ
እንዲሁም የቆሻሻ ክምችትን በአግባቡ ለመቆለልና ክምችቱ የአፈርና
የከርሰ ምድር ውሃን እንዳይበክል የማድረግ ስራዎችም በዚሁ
የምህንድስና ዘርፍ የሚተገበሩ ናቸው።
የአፈርን የምህንድስና ጸባይ የማወቅ ተግባር ለመሬት ነክ መሃንዲሶች
ፈታኝ ነው። በሌሎች የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች የግንባታ ቁሶች
ጸባይ (ለምሳሌ እንደ ብረት እና ኮንክሪት) በሚገባ የሚታወቅ ሲሆን፤
በግንባታ አካባቢ የሚገኝን የአፈር ጸባይ ማወቅ ግን ከተለዋዋጭነቱና
በናሙና በሚደረጉ ሙከራዎች መፈተሽ የሚቻለው ከጠቅላላውን
የተወሰነውን ብቻ በመሆኑ በጣም አዳጋች ነው።
ከዚህም በተጨማሪ አፈር በጭነት ምክንያት የሚያደርገው የቅርጽ
ለውጥ ከጫናው ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ (nonlinear) ተዛምዶ ስላለው፤
ማለትም አነስተኛ እና ከፍተኛ ለሆኑ ጫናዎች የተለያየ ጥንካሬ
(strength)፤ ጠጣርነት(stiffness)፤ የቅርጽ ለውጥ ስለሚኖረው፤
የአፈርን የምህንድስና ጸባይ በተሟላ ሁኔታ ለማወቅ የዳግታል።
መሬት ነክ መሃንዲሶች አብዛኛውን ጊዜ ከከርሰ ምድር ባለሙያዎችና
የአፈር ሳይንቲስቶች ጋር በትብብር ይሰራሉ።

7,የቁሶች ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና

ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና በሲቪል ምህንድስና ውስጥ
ከፍተኛ የሆነ ሚና ይይዛል። የቁሶች ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና
የቁሶችየቁሶችን ተፈጥሮዋዊ ባህሪ የሚያጠና የሳይንስ ወይም የምህንድስና
ዘርፍ ነው።


ይቀጥላል....

https://t.me/ethioengineers1
3.5K viewsENG Sintayehu Melese, 07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 11:55:59
በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት ሥልጠና ያጠናቀቁ ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ ነው።

በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት የሚያበቃቸውን ሥልጠና ያጠናቀቁ የመጀመሪያውዙር ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ መሆኑን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሲቭል ኢንጂነሪንግ፣ በኮንስትራክሽን ማናጅሜንት ቴክኖሎጂ፣ በአርክቴክቸር እና መሰል ሙያዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ተማሪዎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ነበር ተብሏል።

ሥልጠናው፥ ከዛሬ ሦሥት ዓመት በፊት በቀድሞው ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የጀርመን ኮንስትራክሽን ማኅበራት ፌዴሬሽን በጋራ እንደተጀመረ ነበር።

‘ጎኤቴ’ በመባል በሚታወቀው የጀርመን ባህል እና ቋንቋ ኢንስቲትዩት ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ከ50 በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 11ዱ ሥልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ የጀርመን ኮንስትራክሽን ፌዴሬሽን የሚፈልገውን መስፈርት አሟልተው የመጨረሻውን ፈተና በማለፍ ለጉዞ ዝግጁ ሲሆኑ 6ቱ ጀርመን ከሚገኙ አሠሪዎቻቸው ጋር የሥራ ውል ተፈራርመዋል።

ሥልጠናቸውን አጠናቀው፣ የመጨረሻው ምዘና አልፈው እና አስፈላጊውን የሥራ ትዕዛዝ ተቀብለው ወደ ጀርመን ሀገር ለመጓዝ ዝግጀታቸውን ያጠናቀቁ እንዲሁም በመሠልጠን ላይ የሚገኙትን ምሩቃንን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ማነጋገራቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

      
https://t.me/ethioengineers1
3.8K viewsENG Sintayehu Melese, edited  08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 09:26:32 መያዥያ ገንዘብ (Retention money)

ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ/defect liability period / ሀላፊነት
ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከእያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ
ገንዘብ ነው።

ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል።

ሆኖም ከ አስር ፐርሰንት (10%) የበለጠ መሆን አይችልም።

በሀገራችን አብዛኛውን ግዜ አምስት ፐርሰንት(5%) ብቻ የተለመደ ነው።

ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስራው ላይ ስህተት ቢፈጠር በውሉ ላይ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ ከመጨረሻ ርክክብ ጋር በ
አርባ አምስት (45) ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።

@ethioengineers1
1.8K viewsENG Sintayehu Melese, edited  06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 08:35:03
ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት ማምረቻ በድርጅት እኛውጋ ካሪፍ መስተግዶ


የምንስጣቸው አገልግሎት እደ ንብ ከፈለጉ በናተሀሳ አለያም ከኛ

ፕሌት 1ሚሊም ስከ 50 ሚሊም በአልተበላ ለብይድ በሚመች ላሜራ

ጄቦልት ከ12 ሚሊም እስከ 32 ሚሊም ድረስ

በልሙጥ ቶዲኖ ከ14 እስከ 40 ውፍረት በሚፈልጉት ሳይዝ

ብቻ ማንኛውም በብረት ዙርያ ይጠይቁን ካሪፍ ምክር ጋር

0923764834
0913061530 ፀግሽ ይበሉ

አድራሻ መርካቶ
1.9K viewsbereket AWEK BEREKT, 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:21:59 ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) VS ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)
               
1, ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB)

በኮንስትራክሽን ጉዳይ በአብዛኛው በሀገራችን የሚሰራበት የፕሮጀክት አይነት ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ መንገድ እንዲዘጋጅ ካደረገ በኃላ ግንባታውን በተቋራጭ እንዲከናወን የሚያደርግበት ነው።ይሄውም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) በመባል ይታወቃል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን/ በሌላ አርክቴክት ድርጅት/ እንዲከናወን ያደርጋል፡፡
በመቀጠልም በተዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ ወደመምረጥ ሂደት ይገባል፡፡የግንባታው ባለቤት የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነ እንደሆነ ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ የመምረጡ ስራ የሚከናወነው በግዥ ህግ መሰረት ይሆናል፡፡ይሄ አይነቱ ፕሮጀክት በሀገራችን የተለመደ ነው፡፡
              

2, ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)

በሌላ በኩል ደግሞ ተቋራጩ ዲዛይኑን እና ግንባታውን በራሱ የሚያከናውንበት የፕሮጀክት አይነትም አለ።ይሄውም ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB) ይባላል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት ተቋራጩ የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት ያከናውናል፡፡የአርክቴክት ስራው የሚያስከትለው ሀላፊነት የተቋራጩ ይሆናል፡፡ከዲዛይን ስራው ጋር የተያያዘ ችግር የሚያስከትለው ሀላፊነት አሰሪውን/የግንባታውን ባለቤት አይነካውም፡፡ሆኖም ተቋራጩ ዲዛይኑን ያሰራው በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት የሆነ እንደሆነ ከአርክቴክቸር ስራው ጋር በተያያዘ ተቋራጩ ለአሰሪው የሚኖርበት ሀላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ አርክቴክቱም ለተቋራጩ በፍትሀብሄር ህጉ ስለእውቀት ስራ ውል በተደነገገው አግባብ ሀላፊነት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
በዚህ አይነት ፕሮጀክት የግንባታው ባለቤት/አሰሪው ሙሉ በሙሉ የኮንስትራክሽን ስጋቶችን/risks/ ወደ ተቋራጩ ያስተላልፋል፡፡ይህ ማለት አሰሪው ውጤቱን ማለትም ግንባታውን በመጀመሪያ በቀረበለት ዲዛይን አግባብ በጥራት ተከናውኖለት ከመረከብና በውሉ የተቀመጠውን የግንባታ ዋጋ ከመክፈል ባለፈ ማናቸውም አይነት ሀላፊነት አይኖርበትም ማለት ነው፡፡ለአብነት ለመጥቀስ ያህል የኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን(ERA) ዲዛይን ቢዩልድ የመንገድ ፕሮጀክት ሲኖረው ተወዳዳሪ ተቋራጮች የሰርቨየይንግና ዲዛይን ስራዎችን በራሳቸው ከሰሩ በኋላ በዋጋ ይወዳደራሉ፡፡ተቋራጮቹ ዲዛይኑን ሲሰሩ አሮጌ ድልድዮች ካሉ እና ተጠግነው በአዲስ ድልድይ የጥራት ደረጃ መድረስ የሚችሉ ከሆነ ተቋራጮች እንደየፍላጐታቸውና ሙያዊ ምርመራቸው/ምክንያታቸው ተጠጋኝ ድልድይ እና በአዲስ የሚገነባ ድልድይ እያሉ በዝርዝር በዲዛይን አካተው የሚያቀርቡ ሲሆን ምንም ሆነ ምን በውጤት ደረጃ አሰሪው በሚፈልገው የጥራት ደረጃ/ስታንዳርድ መገንባቱ እና ይሄውም በአማካሪው መረጋገጡ ግን የግድ ነው፡፡ምናልባት ተጠግኖ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ይደርሳል የተባለው አሮጌ ድልድይ በጥገና ወቅት ቢፈርስ እንኳ አሰሪውን ክፍያ የመጨመር ሀላፊነት አያስከትልበትም፡፡ስለዚህ ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ለአሰሪዎች ሪስክ ፍሪ/ከስጋት ነጻ የሆነ የፕሮጀክት አይነት ነው፡፡
           
ሌላው ሁለቱም የፕሮጀክት አይነቶች ለኮንስትራክሽን ውላቸው የሚጠቀሙት ጀኔራል ኮንዲሽን የተለያየ ነው።FIDIC በዚህ ረገድ የግንባታ ውል ዝግጅትን በማቅለል ለአለማችን ትልቅ ስጦታ ነው። አለበለዚያ አሰሪና ተቋራጭ በየአንዳንዱ ውል ዝግጅት ወቅት በሁሉም የውል ሁኔታወች ላይ መደራደርን ይጠይቃቸው ነበር።ዛሬ ላይ ግን ለውሉ ጥቅም ላይ የሚውለውን ጀኔራል ኮንዲሽን አስመልክቶ FIDIC ቨርሽን መረጣ እና በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በሚካተቱ ነጥቦች ላይ ብቻ መወያየት በቂ ነው።

በተጨማሪም በዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት የኮንስትራክሽን ስጋት/ሪስክ ሙሉ በሙሉ ወደ ተቋራጩ የሚተላለፍ በመሆኑ ልዩ የዋስትና ሽፋን ያስፈልገዋል፡፡ስለዚሁም ተቋራጩ በግንባታው ዋጋ ልክ All risk insurance እንዲገባ እና ለዲዛይን ስህተት፣ለስራው ብልሽትና በተቋራጩ ባለሙያወች የስራ ስህተት ለሚከሰት ጉዳትና ኪሳራ ደግሞ professional indemenity insurance እንዲገባ FIDIC ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ኮምፖቴብል የሆነው ተርንኪ ጀኔራል ኮንዲሽን ግዴታ ያስቀምጣል።

በሀገራችን ዲዛይን ቢዩልድ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ብዙም የተለመደ አይደለም።ሆኖም በመንገድ ግንባታ ውሎች የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አልፎ አልፎ ይጠቀምበታል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮንሰትራክሽን ዲዛይኒንግ እና የውል አስተዳደር ረገድ ሰፊ የእውቀት ክፍተት ያለ በመሆኑ እና ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ገንዘብ የማይጠናቀቁበት ሁኔታ በሰፊው የሚስተዋል እንደመሆኑ ሙሉ የኮንስትራክሽን ሪስክ/ስጋት ወደ ተቋራጩ በማስተላለፍ  መንግስታዊ ግንባታዎችን በዲዛይን ቢዩልድ የፕሮጀክት አይነት እንዲከናወኑ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ለመጠቆም እወዳለሁ።
                

@ethioengineers1
2.4K viewsENG Sintayehu Melese, edited  18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 14:35:44 የ ምስራች ዜና ለ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በ ሙሉ

በ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በ ተቋራጭነት፣በ ኢንተርየር ዲዛይን፣በ ሰብ ኮንትራክት፣በ ብረታ ብረት፣በ እንጨት ስራ እና የ ህንፃ ግንባታ ተያያዥ ስራዎች ያላቹ በ ሙሉ

አዳዲስ ጨረታዎች ሲወጡ፣ ዕለታዊ የማተርያል ማሽነሪ Cost ለማወቅ በቀላሉ በ Private ቴሌግራም ቻናል አድራሻቹ አመቱን ሙሉ በ ማይታመን ዋጋ እንዲደርሳቹ ለምትፈልጉ ከታች ባሉት አደራሻዎች አናግሩን።

ለመመዝገብ
https://t.me/ethioengineers1 ወይም @Tenderethio ላይ ያናግሩን።

ለ በለጠ መረጃ በ 0953138434 ይደውሉ

እናመሰግናለን


ethio construction
2.7K viewsENG Sintayehu Melese, edited  11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 08:52:36
ይህ በቤኒን መዲና ፖርት-ኖቮ የሚገኘው መስጅድ የአፍሮ-ብራዚል ሥነ ሕንጻ ማሳያ ጥሩ ምሳሌ ነው። በብራዚል በ17ኛው እና 18ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ከዚህ ሕንጻ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ አብያተክርስቲያናት ተገንብተዋል።

ቢጫ፣ ቡኒ፣ አረንጓዴ እና ሰሚያዊ ደማቅ ቀለማት ከብራዚል ጥንታዊ የሥነ ሕንጻ ግንባታ ጥበብ ጋር ቁርኝት አላቸው።

ይህ በቤኒን መዲና ፖርት-ኖቮ የሚገኘው መስጅድ የአፍሮ-ብራዚል ሥነ ሕንጻ ማሳያ ጥሩ ምሳሌ ነው። በብራዚል በ17ኛው እና 18ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ከዚህ ሕንጻ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ አብያተክርስቲያናት ተገንብተዋል።

ቢጫ፣ ቡኒ፣ አረንጓዴ እና ሰሚያዊ ደማቅ ቀለማት ከብራዚል ጥንታዊ የሥነ ሕንጻ ግንባታ ጥበብ ጋር ቁርኝት አላቸው።

https://t.me/ethioengineers1

ተፈጸመ
2.8K viewsENG Sintayehu Melese, edited  05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ