Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction
የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.69K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-07-06 10:38:40 የግንባታ ሥራዎች ሂደት ደረጃዎች/Stages in Construction/

የግንባታ ሥራዎች የሂደት ደረጃዎች በዋናነት በሶስት የሚከፈሉ ሲሆን እነዚህም:

i. የቅድመ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/Preconstruction Stages/

ii. የግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/construction Stages/

iii. የድህረ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ//Postconstruction Stages/

i. የቅድመ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/Preconstruction Stages/

1.የፕሮጀክት ተፈጻሚነትና አዋጭነት ጥናት/Inception and Physibility study/

ይህ ደረጃ አሰሪው ወይም ኢንቬስተሩ ያለመውን ነገር ወይም ፍላጎቱን ወደእውነታ ለማምጣት የመጀመሪያ ሥራው የታሰበውን ፕሮጀክት የተፈጻሚነትና አዋጭነት ጥናት ውጤት ማወቅ ነው፡፡

በዚህ ጊዜ የተላያዩ ባለሞያዎችን የሚይዝ ቡድን፡-

የታሰበውን ስራ እውን ሊሆን የሚችል መሆኑንና አለመሆኑን በማስረጃ ያረጋግጣል ለፕሮጀክቱ አዋጭነት ወሳኝ የቦታ መረጣ ያካሂዳል ፕሮጀክቱ በታሰበበት አካባቢ ከገንዘብ ሃብት ውጭ ያሉ የፕሮጀክት ሃብቶች አቅርቦት ሁኔታ፣ የዋጋ ሁኔታና እንደታሰበው ፕሮጀክቶች ዓይነት ሌሎች ሁኔታዎችን ያጠናል፡፡
የፕሮጀክቱን አዋጭነት ስሌት ዘገባ ይዘጋጃል፣ የሥራውን አጠቃላይ ሁኔታ ሊያሳይ የሚችል ሀሳባዊ ረቂቅ ንድፍ ያዘጋጃል፡፡ 

2.የአፈር አካላት ሳይንስ ጥናት /Geotechnical Investigations/

የአፈር አካላት ሳይንስ ጥናት፡-

አጠቃላይ የግንባታ ሥራው የሚከናወንበትን ወይም ግንባታው የሚያርፍበትንና በዙሪያው ያለውን አካባቢ ሊያካልል የሚችል ፤የመሬቱ የመሸከም አቅም፣ ችግርሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች የሚጠናበት ነው፡፡

3.የመሬት አቀማመጥ አጠቃላይ ሁኔታ የሰርቬይንግ መረጃ ይሰበሰባል፡፡

4.የዕቅድና የንድፍ ሥራ /Planning and Design stage/

የአፈር ሳይንስ ጥናት መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ቀጣዩ ሥራ የሚሆነው የዕቅድና የዲዛይን ማጠቃለያ ሥራዎች የሚከናወኑበት ነው፡፡በዚህም፡
እንደፕሮጀክቱ ሁኔታ የአርክቴክቸራል፣ስትራክቸራል፣ ኤሌክትሪካል፣የኤሌክሮ ሜካኒካልና የሳኒተሪ የመሳሰሉት የዲዛይንና የንድፍ ሥራዎች ይሰራሉ፡፡

5.የፕሮጀክት ሥራ አመራር መዋቅር ዝግጅትና ዕቅድ

6.የገንዘብ ሀብት ዝግጅት ዕቅድ

7.የታሰበው ፕሮጀክት እንደፕሮጀክቱ ግዝፈትና ሊሰራ ለታሰበበት ደረጃ የሚመጥን፤ ለሥራው ጥራት ደረጃ ዕቅድ
የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት ምርጫና የጥራት ልክ ዕቅድየሥራ ተቋራጭ ብቃት ደረጃ ዕቅድና የመሳሰሉት ይሰራሉ፡፡

8.የጨረታ ሥራዎች /Tendering stage/

በዚህ ደረጃ የሚከተሉት ስራዎች ይከናወናሉ

የጨረታ ሰነድ የማዘጋጃት ሥራ/Bidding Document Preparation/፡-

በጨረታ ሰነድ ዝግጅት የጨረታ ሥራ ባለሞያዎች በጨረታ ሰነዱ ሊያካትቷቸው  የሚገቡ ጉዳዮች እንደሚከተለው ይሆናሉ፡፡

የጨረታ ጥሪ/Bid Invitation /
በቂ ለሆነ ጊዜና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች የጨረታ ጥሪ ይፋ መደረጉ የሚረጋገጥበት ሲሆን የጨረታ ጥሪ አድራጊውን አካል ስምና አድራሻ፣የግነባታ ሥራው ዓይነትና የሚከናወንበትን ቦታ፣ሥራውን ለመስራት የሚፈለገው ተቋራጭ የመወዳደር ችሎታ ዝርዝር መመዘኛዎች፣ሥራው ስለሚፈጀው ጠቅላላ ጊዜ፣የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት አኳሆንና የሚገኝበት ቦታ፣ሰነዱን ለማግኘት ስለሚያስፈልግ ክፍያ መጠን፣የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ሰለሚያበቃበት ቀን፣ የተጫራቾች ዜግነት፣ በጨረታው ለመሳተፍ ቅድሚያ ሊከፈል ወይም ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid security) የሚያዝ ገንዘብ ካለ መጠኑና፣ እነደአስፈላጊነቱ ሌሎች ዝዝር መረጃዎችን የሚይዝ ይሆናል፡፡

የተጫራቾች መመሪያ/instraction to bidders/

በተጫራቾች መመሪያ ዝርዝር፡-
_የጨረታ መገምገሚያ ዘዴዎችና የመገምገሚያ መስፈርቾች/Evaluation Methods and Criteria/
_ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ምን ምን ሊያካትት እንደሚገባው የሚገልጽ ዝርዝር
_ የአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚገባቸው መሆኑን
_ ለዘመኑ የታደሱ የተለያዩ ለመጫረት ብቁ የሚያደርጉ ምዝገባዎች ማቅረብ አስፈላጊ ስለመሆኑ
_ ለመንግስት የሚገባውን ግብር ከፍሎ ማረጋገጫ ያለው ስለመሆኑ (Tax Clearance)
_ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈር እንደሚገባቸው
_ ጨረታው ተከፍቶ ካለቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል እንደማይችሉ የሚያመለክት መግለጫ
_ ጨረታውን ለማዛባት ስለመሞከርና በተጫራቹ ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት
_ ስለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና ሰለየመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና
_ ስለጨረታው ማቅረያ ጊዜ፣የሚያበቃበትንና የሚከፈትበትን ጊዜና ሰዓት እንዲሁም የአቀራረብ ሁኔታና
_ ተጫራቹ ስለማጭበርበርና ሙስና/ጉቦ መስጠትንና መቀበልነ ጭምር በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆኑን በማረጋገጥ ግዴታ በመግባት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘወን ቅጽ መፈረም እንዳለበትና
እንደግዢው ዓይነት ሌሎች ሁኔታዎችን የሚያካትት ይሆናል

-የአገልግሎት ዝርዝር/Survice Description/

-የጨረታ ሃሳብ ማቅረቢያና የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ/BOQ/

-የውል ቃሎችና ሁኔታዎች/Contract terms and Conditions/

በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሌላው ሊካተት የሚገባውና በሰነዱ ውስጥ አንድ ክፍል ሆኖ መቅረብ ያለበት ነገር የውል ቃላትና የውል ሁኔታዎች ዝርዝር ነው፡፡ ይኽውም የስራውን ስፋት፣ መሰጠት የሚገባቸው አገልግሎቶችን፣ የአሰሪውና የሥራ ተቋራጩን መብትና ግዴታዎች ዝርዝር፣ የሥራ ተቆጣጣሪው/አማካሪው መሃንዲስ የስራ ድርሻዎች፣ ባለሞያዎች አሟልቶ ስለመስራት፣ የፕሮጀክት መሪ ባለሞያ  ተግባርና ሃላፊነቶችና የመሳሰሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች የሚይዝ ሲሆን ከውሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች በተጨማሪ ከሚሰጠው አገልግሎት የተለየ ባህሪ ጋር የሚሄዱ ልዩ ሁኔታዎችን እና ሥራው የሚከናወንበትን ቦታ የሚያመለክቱ ዝርዝር መረጃችን መያዝ አለበት፡፡
የውል ቃላት የተለያዩ በሰነዱ ውስጥ አገልግሎት ላይ የዋሉ ቃላትን በውል ሰነዱ አተረጓጎም ወቅት ሊኖራቸው

-ጨረታ ይፋ የማድረግ ፣ የመገምገም ፣ አሸናፊውን የመለየት ሥራዎች

-የጨረታ አሸናፊ ጥሪ ስለማድረግና ውል  ስለመዋዋል /Award of Contract and contracing/

ii. የግንባታ ሥራ ክንዋኔዎች ደረጃ ከጅማሬ እስከ ፍጻሜ/construction Stages/

በዚህ ክፍል ዋና ዋና የክንውን ጊዜያት ሶስት ናቸው።

* የዝግጅት ጊዜ/Period of Mobilization/

* የግንባታ ዋና ሂደት ጊዜ/Period of Main Construction Activities/

* የጥገናና የዕድሳት /Defects liability Period/

iii. የግንባታ ሥራ ፍጻሜና ርክክብ /Commissioning and Acceptance/

ለወደፊት እያንዳንዱን በዝርዝር የምናይ ይሆናል።

Via etconp
https://t.me/ethioengineers1
1.4K viewsENG Sintayehu Melese, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 10:32:23
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ፕሌት any Size & thickness
ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

ስልክ 0994941706 ወይም 0910379303 ደውለው ያግኙን
ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት
ቁ.3 በቅርቡ ቄራ ላይ ይጠብቁን
ከቃላችን ይልቅ ስራችን ይናገራል።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነዉ።
1.6K viewsENG Sintayehu Melese, 07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 11:30:14 2. Primavera P6:

• Project Portfolio Management: Learn how to evaluate, prioritize, and select projects based on strategic objectives and resource availability.
• Project Planning and Control: Understand the process of defining project scope, creating work breakdown structures (WBS), and establishing project baselines.
• Resource Management: Discover techniques for effectively managing and optimizing resources, ensuring their availability and productivity.
• Project Tracking and Reporting: Acquire skills to monitor project progress, analyze variances, create reports, and make data-driven decisions.
• Risk Management: Explore methodologies for identifying, assessing, and responding to project risks, minimizing their impact on project outcomes.
https://t.me/BeGetEngineering
3.2K viewsBelay #1, 08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 11:30:13
Here's a preview of the Major Topics covered in Microsoft project and Primavera P6:

1. Microsoft Project:

•  Project Planning: Learn how to create detailed project plans, set project goals, and define tasks and resources.
• Task Management: Understand the fundamentals of task scheduling, linking tasks, setting dependencies, and managing milestones.
• Resource Allocation: Discover effective techniques for allocating resources, tracking resource usage, and optimizing resource assignments.
• Time and Cost Management: Master time tracking, cost estimation, budgeting, and forecasting to ensure project success.
• Collaboration: Explore ways to share project information, communicate with team members, and facilitate efficient collaboration.
https://t.me/BeGetEngineering
2.9K viewsBelay #1, 08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 09:39:24
Call for Advanced Level Training

1) Building Adv. Structural Design
2) Bridge Design 
3
) Project Planning & Contract Administration .

Weekend Class Starts on July8/2023
0911890392 / 0920933016

Megenagna,Marathon, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
2.5K viewsENG Sintayehu Melese, 06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 09:39:24 የግንባታ ሥራዎች አጠቃላይ ፍረጃ/Major Category of construction projects/

የትራንስፖርትና የመገናኛ ግንባታ ሥራዎች /Transport and Communication /:-

የአውራ ጎዳና ግንባታዎች፣ የገጠር መንገዶች፣ የባቡር ሀዲድ፣የአየር ማረፊያ፣ የስልክ ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታ ሥራና የመሳሰሉት የሚገኙበት ነው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሥራዎች ግንባታ /Water and Energy works /:-

የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታዎች፣ የመስኖ ግንባታ፣ የመጠጥ ውሃ ማጣሪያና የመስመር ዝርጋታዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃና ማጣሪያ፣ የጎርፍ መውረጃ ፣ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ የነዳጅ ማውጣት ሥራ የማሳሰሉትን ያካትታል፡፡

የህንጻ ግንባታ ሥራዎች /Buildings/:-

የጤና ተቋማት ግንባታዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ፋብሪካዎች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ሥራ ህንጻዎች እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

https://t.me/ethioengineers1
2.3K viewsENG Sintayehu Melese, 06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 09:35:45 የግንባታ ሥራ  ውል አፈጻጸም ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑ ዋና ዋና  ባለድርሻ አካላት፡

የስራው ባለቤት/Client/Employer:-

ግለሰብ ወይም ማህበር ወይም ድርጅት ወይም የመንግስት ተቋም ሊሆን የሚችል ሲሆን የሥራው ባለቤት ከመሆኑ አንጻር ሥራውን ለማከናወን የሚችል ሥራ ተቋራጭና አማካሪ መሃንዲስ መቅጠር እና ለግንባታ ሥራው የሚያስፈልገውን የገንዘብ ሀብት የሚያዘጋጅና ዋጋ የመክፈል ሃላፊነት ያለበት አካል ነው፡፡

ሥራ ተቋራጭ:-

ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን ግብዓቶች በሙሉ በሟሟላት የግንባታ ሥራውን  በተባለው ጊዜና በተቀመጠው የጥራት ደረጃ ለመስራት ተዋውሎ የሚሰራ ነው፡፡

መሃንዲስ(አማካሪ):-

ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ውለታውን እንዲያስተዳድር የሚቀጠር ነው፡፡ምንም እንኳን አማካሪ መሃንዲሱን የሚቀጥረውና ክፍያ የሚፈጸምለት በአሰሪው ቢሆንም፤ አማካሪው ውሉን በማስተዳደር ሂደት ውስጥ በቅን ልቡና በፍጹም ፍትሃዊነት ለሁለቱም የሚሰራ ነው፡፡

የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅቶች (Insurance Companies):-

አንድ ሥራ ተቋራጭ በጨረታ ለመሳተፍ፣ ወደውል ለመግባት፣ ክፍያዎች ለማግኘትና በሌሎች አሰሪው ድርጅት ለደህንነቱ መጠበቂያ ከስራ ተቋራጩ እንዲቀርብለት የሚጠይቀውን የመተማመኛ የመድን ዋስትናዎች ለሥራ ተቋራጩ የሚያቀርብ አካል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ ለንብረቱ፣ ለገንዘቡ፣ ለስራውና ለሰራተኞቹ ደህንነት የሚጠይቃቸውን የመድን ዋስትናዎችንም (for Contractor’s all risks) የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ አንድ የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅት አይነቱ ተለይቶ ለታወቀ ጉዳይ ለሥራ ተቋራጩ የመድን ሽፋን ሰጠ ማለት በአሰሪው ድርጅትና በሥራ ተቋራጩ በኩል ሊኖር የሚችለውን የአደጋ ስጋት ለመሸከም ሃላፊነት የሚቀበል ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለወደፊት ስለግንባታ ፕሮጀክቶች የመድን ዋስትናዎች (Construction Insurances) በተብራራ ሁኔታ በምናቀርበው ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡

ባንኮች:-

ለስራ ተቋራጩም ይሁን ለስራው ባለቤት ለፕሮጀክቱ ማከናወኛ የገንዘብ ፍላጎቶችን በማመቻቸት የሚሰሩ ናቸው፡፡ ባንኮች እንደ የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ የባንክ ዋስትናም በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡ 

አቅራቢዎች (Suppliers):-

እነዚህ ባለድርሻ አካላት ለግንባታ ሥራ ከመጀመሪያ እስከ ሥራው ፍጻሜ የሚያስፈልጉ ማናቸውንም ዓይነት የግንባታ ሥራ ግብዓቶችን፣ ማሽነሪዎችን ወይም የግንባታ ሥራ ቁሳቁሶችን በሽያጭና በኪራይ  የሚያቀርቡ ናቸው፡፡

ፈቃድ ሰጪ አካላት (Permitting bodies):-

ለግንባታ ሥራው የግንባታ ቦታ በመፍቀድ፣ የግንባታ ፈቃድ በመስጠት፣ የግብዓት ማውጫ ካባዎችን ፣የማምረቻ የማከማቻና የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ፈቃድ በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡

የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅራቢ ተቋማት (Public):-

ለግንባታ ሥራው እንደ ውሃ፣መብራት፣ስልክ የመሳሰሉ ለግንባታ ሥራዎች የመሰረታዊ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ አካላት ናቸው፡፡


https://t.me/ethioengineers1
3.2K viewsENG Sintayehu Melese, edited  06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 21:02:09 የግንባታ ኢንደስትሪው ሀብቶች

1.የገንዘብ ሀብት/Financial Resource or fund/:-

የግንባታ ሥራው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚጠይቀው የገንዘብ ወጪ ነው፡፡ ይህም ከተቀማጭ በቀጥታ፣  በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ከብድር፣ወይም ከስጦታ ወይም ከሌላ ህጋዊ ከሆነ የገንዘብ ምንጭ የሚገኝ ሊሆን የሚችል ሲሆን የግንባታ ፕሮጀክት ለማከናወን ከሚያስፈልጉ ሀብቶች አንዱ መሰረታዊውና ዋነኛው ነው፡፡

2. የሰው ሃይል ሀብት/Human Resource/Labour or Workmanship/:-

እነዚህም ከዘርፉ ቀጥተኛ የሰለጠኑ ባለሞያዎች/Proffesionals/ ፣ በፕሮጀክት አመራር ውስጥ አጋዥ ወይም ደጋፊ የሥራ ዘርፍ ባለሞያዎችንና እስከታችኛው እርከን የሚወርዱ የሥራው ቀጥታ ተሳታፊ የሆኑ በከፊል የሰለጠኑና/Semi skilled/ ስልጠና የሌላቸው የጉልበት ሰራተኞችን/Unskilled/ ሁሉ ያጠቃለለ ነው፡፡የሰው ሃይል ሀብት ለግንባታ ሥራ ከሚመደበው የገንዘብ ሀብት ወይም ባጀት ከ5-7% የሚሆነውን የሚቋደስ ነው፡፡

3. የመረጃ ሀብት/Information Resource/:-

ይህ ዓይነቱ ሀብት ከፕሮጀክት ጥናት ጀምሮ በዲዛይን ሥራ ብሎም ወደግንባታ ሥራ ለመግባትና፣ በፕሮጀክት ሥራ ክንውን ወቅት በሚደረጉ ጉዞዎች ሁሉ አስፈላጊና ለፕሮጀክቱ ዘላቂ ደህንነት መረጋገጥ የሚጠቅሙ፣ የግንባታ ሥራን  አዋጭና በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚረዱ መረጃዎች ናቸው፡፡
መረጃዎች ሳይሰበሰቡ የሚደረግ የዲዛይንና የግንባታ ሥራ ሁሉ አጠራጣሪ ወይም አስጊነቱ የማይካድ ነው፡፡

4. አካላዊ/ግዘፍ ሀብቶች/Physical Resources/:-

አካላዊ ወይም ግዘፍ ሀብቶች የሚባሉት የግንባታ ግብዓት ዕቃዎችና የግንባታ ሥራ ማሽነሪዎች /Materials and Machinaries/ ናቸው፡፡ እነዚህ ሀብቶች ከፍተኛ ግዢ የሚካሄድባቸውና፣ የአንድ ፕሮጀክት አብዛኛውን የገንዘብ ሀብት ወይም ባጀት የሚቋደሱ ወይም የሚይዙት ናቸው፡፡ለምሳሌ የግንባታ ግብዓቶችን ብቻ አንኳን ብንመለከት ከ50-65% የሚሆነውን የግንባታ ሥራ በጀት የሚይዙ ናቸው፡፡

5. የአገልግሎትና አስተዳደራዊ አቅርቦቶች ሀብቶች/Survices and Management/:-

የመሬት አቅርቦት፣ የውሃ አቅርቦት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የስልክ መገናኛ አገልግሎት አቅርቦቶችና የመሳሰሉትን የሚያካትት ሆኖ የግል ወይም የመንግስት አገልግሎት አቅራቢ ተቋማትን አስተዳደራዊ ፈቃድ የሚጠይቁና የሚቀርቡ፤ የግንባታ ሥራዎች ጥራት፣ ቅልጥፍናና የተሻለ አዋጭነት ባለው መልኩ እንዲከናወንና እንዲጠናቀቅ የሚረዱ ሀብቶች ናቸው፡፡


https://t.me/ethioengineers1
3.3K viewsENG Sintayehu Melese, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 18:20:41 https://t.me/ethioengineers1
3.2K viewsENG Sintayehu Melese, 15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 10:18:58 ከ ክረምት ጋር በተያያዘ የውሃ ስርገትና ርጥበትን እንዴት ልከላከል /Damp Prevention/

የውሃ ስርገትና ርጥበትን የመከላከልያ ሌሎች የተለመዱ መንገዶች/Typical Membrane Damp-proofing Agents/

1ኛ. የኮንክሪት ግግር መደብ/Application thin Concrete layer(s) /

አነስተኛ ርጥበት የሚፈጥር የውሃ ስርገት መኖሩ ሲገመት ማለትም የውሃ ፍሰቱ/እዠት በሚኖርበትና ጊዜ በ1:2:4 የውህድ ምጣኔ የተዘጋጀና ከ4-5cm ውፍረት ያለው የኮንክሪት ግግር መደብ/Mass concrete/ልንጠቀም እንችላለን።

የኮንክሪት ግግር መደቡን የስርገት መከላከል አቅም የበለጠ ከፍ ለማድረግ 2 ዙር/2 coat/ ሙቅ/የቀለጠ ቢቱሚን/hot bitumen/Primer መቀባት ውጤቱን የተሻለ ያደርገዋል።

2ኛ. ሞርታር/Mortar/

ለሌሎች የውሃ ስርገት ስራዎች ደጋፊ/ማረፊያ እንዲሆንና የበለጠ ውጤት ለማግኘት ከስር የሚነጠፍ በሲሚንቶና አሸዋ ቅይጥ የሚዘጋጅ ነው።

እንደ ተደራቢው ክርታሱ/membrane/ዓይነት ከ2-5cm ውፍረት ባለው በፈረካስ/trowel finish/ ወይም በሊሾ /screed finish/ማጠናቀቅ ይቻላል።

ከተደራቢው ክርታስ ጋር በቀላሉ ለማያያዝ 2 ዙር/1 coat/ ሙቅ/የቀለጠ ቢቱሚን/hot bitumen/Primer መቀባት ውጤቱን የተሻለ ያደርገዋል።

3ኛ. ልዩ ጡቦች/Bricks/

ውሃ የመምጠጥ አቅማቸው ከፍተኛ ሆነው በልዩ ሁኔታ የተመረቱ ጡቦችን መጠቀም አንዱ የውሃ ስርገትን መከላከያ መንገድ ሲሆን፣የውሃ ፍሰቱ/እዠት በሚኖርበትና ቦታ ብቻ ነው መጠቀም የሚፈቀደው።

4ኛ.የጥብቅ ድንጋይ ንጣፍ/Stones/
ለምሳሌ: ግራናይት

5ኛ. በወፍራሙ የተጋገረ የቢቱመን ንጣፍ/Hot laid bitumen/

እና ሌሎች እንደ Mastic Asphalt
፣Metal sheets የመሳሰሉት አማራጭ የውሃ ስርገትና ርጥበት የመቀነሻና መከላከያ መንገዶችን በዲዛይን ባለሞያዎች ምክርና እገዛ በመታገዝ ብቻ መጠቀም እንችላለን።


https://t.me/ethioengineers1
3.6K viewsENG Sintayehu Melese, 07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ