Get Mystery Box with random crypto!

የግንባታ ሥራዎች ሂደት ደረጃዎች/Stages in Construction/ የግንባታ ሥራዎች የሂደት | Ethio Construction

የግንባታ ሥራዎች ሂደት ደረጃዎች/Stages in Construction/

የግንባታ ሥራዎች የሂደት ደረጃዎች በዋናነት በሶስት የሚከፈሉ ሲሆን እነዚህም:

i. የቅድመ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/Preconstruction Stages/

ii. የግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/construction Stages/

iii. የድህረ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ//Postconstruction Stages/

i. የቅድመ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/Preconstruction Stages/

1.የፕሮጀክት ተፈጻሚነትና አዋጭነት ጥናት/Inception and Physibility study/

ይህ ደረጃ አሰሪው ወይም ኢንቬስተሩ ያለመውን ነገር ወይም ፍላጎቱን ወደእውነታ ለማምጣት የመጀመሪያ ሥራው የታሰበውን ፕሮጀክት የተፈጻሚነትና አዋጭነት ጥናት ውጤት ማወቅ ነው፡፡

በዚህ ጊዜ የተላያዩ ባለሞያዎችን የሚይዝ ቡድን፡-

የታሰበውን ስራ እውን ሊሆን የሚችል መሆኑንና አለመሆኑን በማስረጃ ያረጋግጣል ለፕሮጀክቱ አዋጭነት ወሳኝ የቦታ መረጣ ያካሂዳል ፕሮጀክቱ በታሰበበት አካባቢ ከገንዘብ ሃብት ውጭ ያሉ የፕሮጀክት ሃብቶች አቅርቦት ሁኔታ፣ የዋጋ ሁኔታና እንደታሰበው ፕሮጀክቶች ዓይነት ሌሎች ሁኔታዎችን ያጠናል፡፡
የፕሮጀክቱን አዋጭነት ስሌት ዘገባ ይዘጋጃል፣ የሥራውን አጠቃላይ ሁኔታ ሊያሳይ የሚችል ሀሳባዊ ረቂቅ ንድፍ ያዘጋጃል፡፡ 

2.የአፈር አካላት ሳይንስ ጥናት /Geotechnical Investigations/

የአፈር አካላት ሳይንስ ጥናት፡-

አጠቃላይ የግንባታ ሥራው የሚከናወንበትን ወይም ግንባታው የሚያርፍበትንና በዙሪያው ያለውን አካባቢ ሊያካልል የሚችል ፤የመሬቱ የመሸከም አቅም፣ ችግርሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች የሚጠናበት ነው፡፡

3.የመሬት አቀማመጥ አጠቃላይ ሁኔታ የሰርቬይንግ መረጃ ይሰበሰባል፡፡

4.የዕቅድና የንድፍ ሥራ /Planning and Design stage/

የአፈር ሳይንስ ጥናት መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ቀጣዩ ሥራ የሚሆነው የዕቅድና የዲዛይን ማጠቃለያ ሥራዎች የሚከናወኑበት ነው፡፡በዚህም፡
እንደፕሮጀክቱ ሁኔታ የአርክቴክቸራል፣ስትራክቸራል፣ ኤሌክትሪካል፣የኤሌክሮ ሜካኒካልና የሳኒተሪ የመሳሰሉት የዲዛይንና የንድፍ ሥራዎች ይሰራሉ፡፡

5.የፕሮጀክት ሥራ አመራር መዋቅር ዝግጅትና ዕቅድ

6.የገንዘብ ሀብት ዝግጅት ዕቅድ

7.የታሰበው ፕሮጀክት እንደፕሮጀክቱ ግዝፈትና ሊሰራ ለታሰበበት ደረጃ የሚመጥን፤ ለሥራው ጥራት ደረጃ ዕቅድ
የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት ምርጫና የጥራት ልክ ዕቅድየሥራ ተቋራጭ ብቃት ደረጃ ዕቅድና የመሳሰሉት ይሰራሉ፡፡

8.የጨረታ ሥራዎች /Tendering stage/

በዚህ ደረጃ የሚከተሉት ስራዎች ይከናወናሉ

የጨረታ ሰነድ የማዘጋጃት ሥራ/Bidding Document Preparation/፡-

በጨረታ ሰነድ ዝግጅት የጨረታ ሥራ ባለሞያዎች በጨረታ ሰነዱ ሊያካትቷቸው  የሚገቡ ጉዳዮች እንደሚከተለው ይሆናሉ፡፡

የጨረታ ጥሪ/Bid Invitation /
በቂ ለሆነ ጊዜና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች የጨረታ ጥሪ ይፋ መደረጉ የሚረጋገጥበት ሲሆን የጨረታ ጥሪ አድራጊውን አካል ስምና አድራሻ፣የግነባታ ሥራው ዓይነትና የሚከናወንበትን ቦታ፣ሥራውን ለመስራት የሚፈለገው ተቋራጭ የመወዳደር ችሎታ ዝርዝር መመዘኛዎች፣ሥራው ስለሚፈጀው ጠቅላላ ጊዜ፣የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት አኳሆንና የሚገኝበት ቦታ፣ሰነዱን ለማግኘት ስለሚያስፈልግ ክፍያ መጠን፣የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ሰለሚያበቃበት ቀን፣ የተጫራቾች ዜግነት፣ በጨረታው ለመሳተፍ ቅድሚያ ሊከፈል ወይም ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid security) የሚያዝ ገንዘብ ካለ መጠኑና፣ እነደአስፈላጊነቱ ሌሎች ዝዝር መረጃዎችን የሚይዝ ይሆናል፡፡

የተጫራቾች መመሪያ/instraction to bidders/

በተጫራቾች መመሪያ ዝርዝር፡-
_የጨረታ መገምገሚያ ዘዴዎችና የመገምገሚያ መስፈርቾች/Evaluation Methods and Criteria/
_ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ምን ምን ሊያካትት እንደሚገባው የሚገልጽ ዝርዝር
_ የአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚገባቸው መሆኑን
_ ለዘመኑ የታደሱ የተለያዩ ለመጫረት ብቁ የሚያደርጉ ምዝገባዎች ማቅረብ አስፈላጊ ስለመሆኑ
_ ለመንግስት የሚገባውን ግብር ከፍሎ ማረጋገጫ ያለው ስለመሆኑ (Tax Clearance)
_ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈር እንደሚገባቸው
_ ጨረታው ተከፍቶ ካለቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል እንደማይችሉ የሚያመለክት መግለጫ
_ ጨረታውን ለማዛባት ስለመሞከርና በተጫራቹ ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት
_ ስለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና ሰለየመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና
_ ስለጨረታው ማቅረያ ጊዜ፣የሚያበቃበትንና የሚከፈትበትን ጊዜና ሰዓት እንዲሁም የአቀራረብ ሁኔታና
_ ተጫራቹ ስለማጭበርበርና ሙስና/ጉቦ መስጠትንና መቀበልነ ጭምር በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆኑን በማረጋገጥ ግዴታ በመግባት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘወን ቅጽ መፈረም እንዳለበትና
እንደግዢው ዓይነት ሌሎች ሁኔታዎችን የሚያካትት ይሆናል

-የአገልግሎት ዝርዝር/Survice Description/

-የጨረታ ሃሳብ ማቅረቢያና የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ/BOQ/

-የውል ቃሎችና ሁኔታዎች/Contract terms and Conditions/

በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሌላው ሊካተት የሚገባውና በሰነዱ ውስጥ አንድ ክፍል ሆኖ መቅረብ ያለበት ነገር የውል ቃላትና የውል ሁኔታዎች ዝርዝር ነው፡፡ ይኽውም የስራውን ስፋት፣ መሰጠት የሚገባቸው አገልግሎቶችን፣ የአሰሪውና የሥራ ተቋራጩን መብትና ግዴታዎች ዝርዝር፣ የሥራ ተቆጣጣሪው/አማካሪው መሃንዲስ የስራ ድርሻዎች፣ ባለሞያዎች አሟልቶ ስለመስራት፣ የፕሮጀክት መሪ ባለሞያ  ተግባርና ሃላፊነቶችና የመሳሰሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች የሚይዝ ሲሆን ከውሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች በተጨማሪ ከሚሰጠው አገልግሎት የተለየ ባህሪ ጋር የሚሄዱ ልዩ ሁኔታዎችን እና ሥራው የሚከናወንበትን ቦታ የሚያመለክቱ ዝርዝር መረጃችን መያዝ አለበት፡፡
የውል ቃላት የተለያዩ በሰነዱ ውስጥ አገልግሎት ላይ የዋሉ ቃላትን በውል ሰነዱ አተረጓጎም ወቅት ሊኖራቸው

-ጨረታ ይፋ የማድረግ ፣ የመገምገም ፣ አሸናፊውን የመለየት ሥራዎች

-የጨረታ አሸናፊ ጥሪ ስለማድረግና ውል  ስለመዋዋል /Award of Contract and contracing/

ii. የግንባታ ሥራ ክንዋኔዎች ደረጃ ከጅማሬ እስከ ፍጻሜ/construction Stages/

በዚህ ክፍል ዋና ዋና የክንውን ጊዜያት ሶስት ናቸው።

* የዝግጅት ጊዜ/Period of Mobilization/

* የግንባታ ዋና ሂደት ጊዜ/Period of Main Construction Activities/

* የጥገናና የዕድሳት /Defects liability Period/

iii. የግንባታ ሥራ ፍጻሜና ርክክብ /Commissioning and Acceptance/

ለወደፊት እያንዳንዱን በዝርዝር የምናይ ይሆናል።

Via etconp
https://t.me/ethioengineers1