ከ ክረምት ጋር በተያያዘ የውሃ ስርገትና ርጥበትን እንዴት ልከላከል /Damp Prevention/ የውሃ ስርገትና ርጥበትን የመከላከልያ ሌሎች የተለመዱ መንገዶች/Typical Membrane Damp-proofing Agents/ 1ኛ. የኮንክሪት ግግር መደብ/Application thin Concrete layer(s) / አነስተኛ ርጥበት የሚፈጥር የውሃ ስርገት መኖሩ ሲገመት ማለትም የውሃ ፍሰቱ/እዠት በሚኖርበትና ጊዜ በ1:2:4 የውህድ ምጣኔ የተዘጋጀና ከ4-5cm ውፍረት ያለው የኮንክሪት ግግር መደብ/Mass concrete/ልንጠቀም እንችላለን። የኮንክሪት ግግር መደቡን የስርገት መከላከል አቅም የበለጠ ከፍ ለማድረግ 2 ዙር/2 coat/ ሙቅ/የቀለጠ ቢቱሚን/hot bitumen/Primer መቀባት ውጤቱን የተሻለ ያደርገዋል። 2ኛ. ሞርታር/Mortar/ ለሌሎች የውሃ ስርገት ስራዎች ደጋፊ/ማረፊያ እንዲሆንና የበለጠ ውጤት ለማግኘት ከስር የሚነጠፍ በሲሚንቶና አሸዋ ቅይጥ የሚዘጋጅ ነው። እንደ ተደራቢው ክርታሱ/membrane/ዓይነት ከ2-5cm ውፍረት ባለው በፈረካስ/trowel finish/ ወይም በሊሾ /screed finish/ማጠናቀቅ ይቻላል። ከተደራቢው ክርታስ ጋር በቀላሉ ለማያያዝ 2 ዙር/1 coat/ ሙቅ/የቀለጠ ቢቱሚን/hot bitumen/Primer መቀባት ውጤቱን የተሻለ ያደርገዋል። 3ኛ. ልዩ ጡቦች/Bricks/ ውሃ የመምጠጥ አቅማቸው ከፍተኛ ሆነው በልዩ ሁኔታ የተመረቱ ጡቦችን መጠቀም አንዱ የውሃ ስርገትን መከላከያ መንገድ ሲሆን፣የውሃ ፍሰቱ/እዠት በሚኖርበትና ቦታ ብቻ ነው መጠቀም የሚፈቀደው። 4ኛ.የጥብቅ ድንጋይ ንጣፍ/Stones/ ለምሳሌ: ግራናይት 5ኛ. በወፍራሙ የተጋገረ የቢቱመን ንጣፍ/Hot laid bitumen/ እና ሌሎች እንደ Mastic Asphalt ፣Metal sheets የመሳሰሉት አማራጭ የውሃ ስርገትና ርጥበት የመቀነሻና መከላከያ መንገዶችን በዲዛይን ባለሞያዎች ምክርና እገዛ በመታገዝ ብቻ መጠቀም እንችላለን። https://t.me/ethioengineers1 3.6K viewsENG Sintayehu Melese, 07:18