Get Mystery Box with random crypto!

SHEAR_WALL Shear wall is a structural member in a reinforced | Ethio Construction

SHEAR_WALL

Shear wall is a structural member in a reinforced concrete framed structure to resist lateral forces such as wind forces.

SHEAR WALL የአግዳሚ ወይም horizontal load ተፅዕኖዎችን የሚቋቋሙልን ግድግዳዎች ናቸው፡፡ ሺር ዎል የተባሉበትም ምክንያት የመሬት መንቀጥቀጥ በጎን አቅጣጫ ስለሚመጣና ዎሎቹ ላይ የሺር ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ነው ( ሺር በ Thickness ትይዩ በሆነ አቅጣጫ እንደሚመጣ ልብ ማለት ይገባል፡፡ Horizontal force የሆኑት Earth Quake እና Wind Load  በዎሎቹ Thickness ትይዩ በሆነ አቅጣጫ ነው የሚመጡት) ፡፡

ሺር ዎሎች በትክክል ዲዛይን ተደርገው ትክክለኛ ቦታቸው ላይ ካልተቀመጡ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ህንጻውን አፍራሽ ግብረ ሃይል ናቸው - ስለዚህ እንዴት ማስቀመጥ እንዳለብን ቀጥለን እንመልከት፡

1) አንድ ህንፃ ላይ የሚፈቀደው ትንሹ  የሺር ዎል ብዛት ሶስት ነው፡፡ ቢያንስ-ሶስት

2) ሶስት ወይም ከዛ በላይ ሺር ዎሎች ካሉን የዎሎቹ አክሲሶች አንድ ነጥብ ላይ መገናኘት የለባቸውም

3) ትይዩ እንዲሆኑ የሚፈቀደው ቢበዛ ለሁለት ዎሎች ነው፡፡

ሺር ዎሎች ከኮለንና ቢም ይልቅ የህንፃውን ጥንካሬ ወይም Stiffness ወደ ራሳቸው የመጎተት ከፍተኛ አቅም አላቸው ፤ እንደሚታወቀው የመሬት መንቀጥቀጥ act የሚያደርገው Center of Mass ላይ ነው ፤ የመሬት መንቀጥቀጥን በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም ደግሞ የህንፃው ጥንካሬ ወይም Center of Stiffness የሚገኝበት ነጥብና የህንጻው Center of Mass የሚገኝበት ነጥብ በተቻለ መጠን መቀራረብ አለበት ፤ እናም ስናጠቃልለው - በትክክል ያልተቀመጡ ሺር ዎሎች የህንጻውን Center of Stiffness ወይም ጥንካሬ ወደራሳቸው ሲጎትቱት ከ Center of Mass እንዲርቅ ያደርጉታል - በመራራቃቸው የተነሳ እሽክርክሪት ፎርስ ወይም  Torsion ይፈጠራል ፡፡ Torsion ህንፃው እንዲፈርስ ያደርገዋል፡፡ የኒውተን ሶስተኛ ህግ ምን ይላል “The forces of action and reaction between interacting bodies are equal in magnitude, opposite in direction and COLLINEAR” – ሁለት ፎርሶች Collinear force የሚባሉት ደግሞ በአንድ መስመር act ሲያደርጉ ነው፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ CM ላይ Act ሲያደርግ CS ደግሞ በሺር ዎሎቹ ስለተጎተተ ሌላ ቦታ React ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ Collinear force አይደሉም ማለት ነው፡፡

ስለዚህ Newton Third Law ውድቅ ሆነ ማለት ነው፡፡
Action እና Reaction በመጠንም ይሁን በአቅጣጫ እኩል ስለማይሆኑ ትርፍ balance ያልተደረገ force ይፈጠራል

Newton First Lawን ታሳቢ በማድረግ ህንፃው Equilibrium ላይ አይሆንም ማለት ነው፡፡

የኒውተን ሁለተኛ ህግስ ማን አለው የሚል ሰው ካለ - በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የሚፈጠረው ፎርስ ማለት የህንፃው ክብደት ሲባዛ በእንቅጥቃጤው የሚፈጠር Acceleration ነው - ይህም Newton Second Law ነው::

ስናጠቃልለው ከጥፋት ለመዳን ሺር ዎልን ስናስቀምጥ ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ተግባራዊ ማድረግ አለብን፡፡

@ethioengineers1