Get Mystery Box with random crypto!

የግንባታ ኢንደስትሪው ሀብቶች 1.የገንዘብ ሀብት/Financial Resource or fund/:- | Ethio Construction

የግንባታ ኢንደስትሪው ሀብቶች

1.የገንዘብ ሀብት/Financial Resource or fund/:-

የግንባታ ሥራው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚጠይቀው የገንዘብ ወጪ ነው፡፡ ይህም ከተቀማጭ በቀጥታ፣  በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ከብድር፣ወይም ከስጦታ ወይም ከሌላ ህጋዊ ከሆነ የገንዘብ ምንጭ የሚገኝ ሊሆን የሚችል ሲሆን የግንባታ ፕሮጀክት ለማከናወን ከሚያስፈልጉ ሀብቶች አንዱ መሰረታዊውና ዋነኛው ነው፡፡

2. የሰው ሃይል ሀብት/Human Resource/Labour or Workmanship/:-

እነዚህም ከዘርፉ ቀጥተኛ የሰለጠኑ ባለሞያዎች/Proffesionals/ ፣ በፕሮጀክት አመራር ውስጥ አጋዥ ወይም ደጋፊ የሥራ ዘርፍ ባለሞያዎችንና እስከታችኛው እርከን የሚወርዱ የሥራው ቀጥታ ተሳታፊ የሆኑ በከፊል የሰለጠኑና/Semi skilled/ ስልጠና የሌላቸው የጉልበት ሰራተኞችን/Unskilled/ ሁሉ ያጠቃለለ ነው፡፡የሰው ሃይል ሀብት ለግንባታ ሥራ ከሚመደበው የገንዘብ ሀብት ወይም ባጀት ከ5-7% የሚሆነውን የሚቋደስ ነው፡፡

3. የመረጃ ሀብት/Information Resource/:-

ይህ ዓይነቱ ሀብት ከፕሮጀክት ጥናት ጀምሮ በዲዛይን ሥራ ብሎም ወደግንባታ ሥራ ለመግባትና፣ በፕሮጀክት ሥራ ክንውን ወቅት በሚደረጉ ጉዞዎች ሁሉ አስፈላጊና ለፕሮጀክቱ ዘላቂ ደህንነት መረጋገጥ የሚጠቅሙ፣ የግንባታ ሥራን  አዋጭና በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚረዱ መረጃዎች ናቸው፡፡
መረጃዎች ሳይሰበሰቡ የሚደረግ የዲዛይንና የግንባታ ሥራ ሁሉ አጠራጣሪ ወይም አስጊነቱ የማይካድ ነው፡፡

4. አካላዊ/ግዘፍ ሀብቶች/Physical Resources/:-

አካላዊ ወይም ግዘፍ ሀብቶች የሚባሉት የግንባታ ግብዓት ዕቃዎችና የግንባታ ሥራ ማሽነሪዎች /Materials and Machinaries/ ናቸው፡፡ እነዚህ ሀብቶች ከፍተኛ ግዢ የሚካሄድባቸውና፣ የአንድ ፕሮጀክት አብዛኛውን የገንዘብ ሀብት ወይም ባጀት የሚቋደሱ ወይም የሚይዙት ናቸው፡፡ለምሳሌ የግንባታ ግብዓቶችን ብቻ አንኳን ብንመለከት ከ50-65% የሚሆነውን የግንባታ ሥራ በጀት የሚይዙ ናቸው፡፡

5. የአገልግሎትና አስተዳደራዊ አቅርቦቶች ሀብቶች/Survices and Management/:-

የመሬት አቅርቦት፣ የውሃ አቅርቦት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የስልክ መገናኛ አገልግሎት አቅርቦቶችና የመሳሰሉትን የሚያካትት ሆኖ የግል ወይም የመንግስት አገልግሎት አቅራቢ ተቋማትን አስተዳደራዊ ፈቃድ የሚጠይቁና የሚቀርቡ፤ የግንባታ ሥራዎች ጥራት፣ ቅልጥፍናና የተሻለ አዋጭነት ባለው መልኩ እንዲከናወንና እንዲጠናቀቅ የሚረዱ ሀብቶች ናቸው፡፡


https://t.me/ethioengineers1