Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioengineers1 — Ethio Construction
የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.69K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-07-02 20:32:38 SHEAR_WALL

Shear wall is a structural member in a reinforced concrete framed structure to resist lateral forces such as wind forces.

SHEAR WALL የአግዳሚ ወይም horizontal load ተፅዕኖዎችን የሚቋቋሙልን ግድግዳዎች ናቸው፡፡ ሺር ዎል የተባሉበትም ምክንያት የመሬት መንቀጥቀጥ በጎን አቅጣጫ ስለሚመጣና ዎሎቹ ላይ የሺር ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ነው ( ሺር በ Thickness ትይዩ በሆነ አቅጣጫ እንደሚመጣ ልብ ማለት ይገባል፡፡ Horizontal force የሆኑት Earth Quake እና Wind Load  በዎሎቹ Thickness ትይዩ በሆነ አቅጣጫ ነው የሚመጡት) ፡፡

ሺር ዎሎች በትክክል ዲዛይን ተደርገው ትክክለኛ ቦታቸው ላይ ካልተቀመጡ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ህንጻውን አፍራሽ ግብረ ሃይል ናቸው - ስለዚህ እንዴት ማስቀመጥ እንዳለብን ቀጥለን እንመልከት፡

1) አንድ ህንፃ ላይ የሚፈቀደው ትንሹ  የሺር ዎል ብዛት ሶስት ነው፡፡ ቢያንስ-ሶስት

2) ሶስት ወይም ከዛ በላይ ሺር ዎሎች ካሉን የዎሎቹ አክሲሶች አንድ ነጥብ ላይ መገናኘት የለባቸውም

3) ትይዩ እንዲሆኑ የሚፈቀደው ቢበዛ ለሁለት ዎሎች ነው፡፡

ሺር ዎሎች ከኮለንና ቢም ይልቅ የህንፃውን ጥንካሬ ወይም Stiffness ወደ ራሳቸው የመጎተት ከፍተኛ አቅም አላቸው ፤ እንደሚታወቀው የመሬት መንቀጥቀጥ act የሚያደርገው Center of Mass ላይ ነው ፤ የመሬት መንቀጥቀጥን በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም ደግሞ የህንፃው ጥንካሬ ወይም Center of Stiffness የሚገኝበት ነጥብና የህንጻው Center of Mass የሚገኝበት ነጥብ በተቻለ መጠን መቀራረብ አለበት ፤ እናም ስናጠቃልለው - በትክክል ያልተቀመጡ ሺር ዎሎች የህንጻውን Center of Stiffness ወይም ጥንካሬ ወደራሳቸው ሲጎትቱት ከ Center of Mass እንዲርቅ ያደርጉታል - በመራራቃቸው የተነሳ እሽክርክሪት ፎርስ ወይም  Torsion ይፈጠራል ፡፡ Torsion ህንፃው እንዲፈርስ ያደርገዋል፡፡ የኒውተን ሶስተኛ ህግ ምን ይላል “The forces of action and reaction between interacting bodies are equal in magnitude, opposite in direction and COLLINEAR” – ሁለት ፎርሶች Collinear force የሚባሉት ደግሞ በአንድ መስመር act ሲያደርጉ ነው፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ CM ላይ Act ሲያደርግ CS ደግሞ በሺር ዎሎቹ ስለተጎተተ ሌላ ቦታ React ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ Collinear force አይደሉም ማለት ነው፡፡

ስለዚህ Newton Third Law ውድቅ ሆነ ማለት ነው፡፡
Action እና Reaction በመጠንም ይሁን በአቅጣጫ እኩል ስለማይሆኑ ትርፍ balance ያልተደረገ force ይፈጠራል

Newton First Lawን ታሳቢ በማድረግ ህንፃው Equilibrium ላይ አይሆንም ማለት ነው፡፡

የኒውተን ሁለተኛ ህግስ ማን አለው የሚል ሰው ካለ - በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የሚፈጠረው ፎርስ ማለት የህንፃው ክብደት ሲባዛ በእንቅጥቃጤው የሚፈጠር Acceleration ነው - ይህም Newton Second Law ነው::

ስናጠቃልለው ከጥፋት ለመዳን ሺር ዎልን ስናስቀምጥ ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ተግባራዊ ማድረግ አለብን፡፡

@ethioengineers1
3.7K viewsENG Sintayehu Melese, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 09:47:31 How is a reinforcement bar in hardened concrete structure exposed to corrosion??

ሙሉ በሙሉ ጥንካሬውን ያገኘ የ ኮንክሪት ስትራክቸር ውስጥ ያለ ወይም የተሰራበት reinforcement bar እንዴት ሊዝግ ይችላል? በምን ምክንያቶችስ ሊሆን ይችላል?


ሦስት መሰረታዊ የሆኑ ሁኔታዎች reinforcement ባራችንን በበቂ ሁኔታ ጥንካሬውን ባገኝ የ አርማታ ስትራክቸር ውስጥ ባለበት ሊያዝጉት ይችላሉ (corrosion እንዲፈጠር ሊያደርጉት ይችላሉ)

1,የመጀመሪያው carbonation ይባላል

:- እንደሚታወቀው concrete strongly alkaline nature አለው። ይህም የሆነበት ምክንያት Ca(OH)2 ስላለው። pH value ደግሞ about 13 ነው። 
:- due to this high alkalinity nature ኮንክሪቱ reinforcement ባሩን ከ corrosion ለመከላከል a thin passivating layer በባሩ ዙሪያ በመፍጠር ብረቱን ከዝገት ይከላከላል። ይህም process passivation በመባል ይታወቃል።
:- as we know CO2 በራሱ reactive አይደለም። ግን in the pressence of moisture( እርጥበት) ወደ dilute carbonic acid ይቀየራል። ከዛም concrete form ያደረገውን passivating layer መብላት ወይም ማፈራረስ ይጀምራል። በመጨረሻም PH value ን  ወደ 8.3 - 9 ያደርሰዋል። ልክ PH value ከ 11 ማነስ ሲጀምር ብረቱ በቀላሉ መዛግ ይጀምራል።

2,ሁለተኛው ደግሞ chloride attack ነው

:- በተመሳሳይ መንገድ ልክ carbonation passivating layer ን ማፈራረስ እንደሚችል chloride attack ም ያንን በበለጠ ማድረግ ይችላል።
:- chloride attack is more serious reason than any other
:- in the presence of water and oxygen, chloride can destroy the passivating layer and leads to corrosion.
:- chloride በቀላሉ ወደ ኮንክሪቱ ሊገባ ይችላል። ለምሳሌ በ cement,water,aggregate and sometimes from admixtures or from environment by diffusion.

3,ሶስተኛው በ electrochemical process ነው

:- ይሄኛው ደግሞ when there is a difference in electrical potential along the steel reinforcement in concrete.
:- ብረቱ ውስጥ አንደኛው part anode ሌላኛው part ደግሞ cathode ሲሆን ነው።

★ በስተመጨረሻም corrosion of reinforcement ለመከላከል ምን አይነት measurement መውሰድ እንዳለብን እንድትወያዩበት እጋብዛለው።

https://t.me/ethioengineers1
3.5K viewsENG Sintayehu Melese, 06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 20:04:49
Concrete Cover is also known as Spacers which is used to provide spacing at Slab, Column, Beam & foundation.

Application is very simple as place between Rebar (Reinforcement bar) and ground/wall.

There are four types of cover block or Spacers!

1. Slab Cover
2. Column & Beam Cover
3. Foundation Cover
4. Piling Cover

Why  need covering


1. to protect the steel  reinforcement bars ( rebars) from env't  effect to prevent their corrosion .

2. To provide thermal insulation ,whiche protect the reinforcement bars from fire.

3. To give reinforcing bars sufficient embedding to enable them to be stressed with out slipping



https://t.me/ethioengineers1
3.8K viewsENG Sintayehu Melese, edited  17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 06:45:26
  Here is detail for the new class schedule.

Option 1 is for detail package( 8 separate packages available , each for 2 months)

Option 2 is for separate software need( each for 3 weeks)


Class Starts on June 19/2023

Registration is active

0911890392 / 0920933016

Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
1.1K viewsENG Sintayehu Melese, 03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 22:16:57 Advance Security vs
Performance Security.

1. Advance security

ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው የቅድም ክፍያ ገንዘብ በሚከፈለው የገንዘብ መጠን ልክ የሚያሲዘው የባንክ ዋስትና ቦንድ ነው። እውነተኛነቱ በተረጋገጠ ቼክ፣ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ወይም ከህጋዊ ጥቃቅን ማይክሮ ፋይናንስ የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርበታል።
ስራ ተቋራጩ የወሰደውን ቅድመ ክፍያ ከፍሎ እስኪጨርስ ያስያዘው ዋስትና ግዜው ማለቅ(Expire) አይችልም። ከአንድ ወር ቀደም ብሎ የዋስትና ቀነ ገደቡ ከማለፉ በፊት ከአማካሪ በሚፃፍለት ደብዳቤ መሰረት ሊታደስ ይገባል። ነገር ግን ስራ ተቋራጩ ያስያዘውን ዋስትና ቀነ ገደቡ አልፎ ሳያሳድስ ቢቀር ቀሪ ያልተከፈለ ቅድመ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ከሚቀጥለው ክፍያ ቅፅ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
ስራ ተቋራጩ ያስያዘውን ዋስትና ቅድመ ክፍያ ገንዘብ ከፍሎ እንደጨረሰ ተመላሽ ይደረግለታል።
የተለየ የቅድመ ክፍያ እና የዋስትና አከፋፈል አካሔድ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/ ይችላል።

2. Performance Security

ስራ ተቋራጩ ውል ተቀብሎ ተፈፃሚ ማድረግ የሚችልበትን ለብቃት ማረጋገጫ የሚያሲዘው ዋስትና ነው። ውል በተፈራረመ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ (15) ውሉ የሚያዘውን መጠን ዋስትና ያቀርባል ።
ዋስትናው ስራ ተቋራጩ በተገቢው መንገድ ውሉን ተፈፃሚ ሳያደርግ ቢቀር ለውል ሰጪ (ባለቤት) እንደ ካሳ ክፍያ ይሆናል።
እውነተኛነቱ በተረጋገጠ ቼክ፣ የባንክ ዋስትና ወይም ከህጋዊ ጥቃቅን ማይክሮ ፋይናንስ የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ውሉ ላይ በተቀመጠው ፎርማት መሰረት ማስያዝ ይኖርበታል።
ይህ ዋስትና ሳይቀርብ ምንም አይነት ክፍይ ተፈፃሚ ሊደረግ አይገባም። ስራው ተጠናቆ እስኪያልቅ


https://t.me/ethioengineers1
1.5K viewsENG Sintayehu Melese, edited  19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 19:53:31
ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት ማምረቻ ጅምላ እና ችርቻሮ መሸጫ

በበቂ ሁኔታ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች እደ ምርጫቹ ታገኛላቹ ከበቂ ሀሳብ ጋር

1 ፕሌት በሚፈልጉት ሳይዝ ቆርጠን ቀዳዳ አበጅተን እንሰጦታለን

2 ጄቦልት በሚፈልጉት የጥርስ መጠን እናም የቁመት መጠን ጥርስ አውጥተን አጥፈን እሰጦታለን

3 እንዲሁም ላሜራ 1ሚሊም እስከ 12 ሚሊም ለማስቆረጥ ካሰቡ እኛው ቆርጠን እናስረክባለን

4 ማንኛውም ላሜራ እንዲሁም ሌላ ብረት ቀዳዳ ሚበሳ ካሎት እበሳለን

እደው ምን አለፋውት ላሜራ መቁረጫ ቶርኖ ምን ለሁሉም ይጠይቁን ከብቁ ባለሞያ ጋር ሁሉም አለ

ሌላው ብቻ ሚፈልጉት ይዘዙን በታማኝነት በተባለው ቀን ያገኛሉ

መልካም ስራ ለራስ ነው
በዚህ ይደውሉ 0913061530
0923764834 ፀግሽ ፕሌት
1.7K viewsENG Sintayehu Melese, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 19:53:31 የውሃ ጋኖች (water supply Reservoir)
.
የውሃ ጋኖች ከጥቅማቸው አንፃር ለ ሶስት ይከፈላሉ
.
1-Collector reservoir
2-Service reservoir
3-Supply reservoir
.
እያንዳንዱ ጥቅማቸው ምንድነው……
.
[Collector reservoir ]
.
ይህ የጋን አይነት ዋና ስራው ውሃው ከሚመነጭበት (የገጸ ምድር ወይም የከርሰ ምድር ውሃ) ቦታ ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚቀመጥበት ጋን ነው፡፡ ጥቅሙ የተሰበሰበውን ውሃ ወደተለያዩ ጋኖች እስኪሰራጭ በጊዜያዊነት እንዲቀመጥና ውሃው ለጋኖቹ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጉልበት እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡ ብዙን ጊዜ ውሃው ከሚመነጭበት ቦታ አቅራቢያ ይተከላል፡፡ ውሃ ፈሳሽ እንደመሆኑ ብዙን ግዜ ሚፈልቀው ከፍታቸው ካነሱ ቦታዎች ስለሆነ ከሌሎች ጋኖች ይልቅ የዚህ ጋን ከፍታ (elevation) ያንሳል፡፡
.
[Service reservoir]
.
ይህ የጋን አይነት በቋሚነት ከcollecter reservoir የተቀበለውን ውሃ የሚያርፍበት ነው፡፡ አሰራሩም ከሌሎቹ ጋኖች ለየት ይላል ፡፡ ውሃው የሚያደርስበትን ግፊት ለመቋቋም የሚያስቸለውን መካች ጉልበት(reaction force) በበቂ ሁኔታ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ በቁመትም በመጠንም ትልቅ ነው፡፡ ወጪ ለመቀነስ ከፍ ካለ ቦታ ይተከላል (ውሃ በ3 አይነት መንገድ ይከፋፈላል
.
1-የሞተር ሀይልን በመጠቀም

2-የመሬት የመሳብ ሃይልን (gravity force) በመጠቀም።

3-የሞተር ሃይልንና የመሬት የስበት ሃይልን በማጣመር በመጠቀም እንዲሰራጭ ይደረጋል ፡፡

በአሁን ጊዜ ሶስተኛው አማራጭ በስፋታ አገልግሎት ላይ ይውላል ይህ አማራጭ ከወጪም አንፃር በጣም ተመራጭ ነው ለዚህ ዘዴ ተመራጩ ደግሞ የservice reservoir ከፍ ካለ ቦታላይ መተከል ወሳኝነት አለው፡፡)
ከዚህ ጋን ቀጥታ ለስርጭት ቧንቧ አይገጠምም ምክንያቱም ከጋኑ የሚወጣው ውሃ ከፍተኛ ጉልበት ስላለው የማሰራጫ ቱቦዎችን ሊያፈነዳ ይችላል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ቀጣዩን የጋን አይነት መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
.
[Supply  reservoir]
.

የዚህ ጋን ዋና ጥቅም ውሃውን ለስርጭት ወደ ስርጭት ቱቦዎች እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከሰርቪስ ጋን ቀጥታ ወደ ስርጭት ቧንቧ ውሃ አይገባም ምክንያቱም ከፍተኛ ሀይል ስላለው የቧንቧዎቹን የመቆየት አቅም ያሳጥራል ብሎም እስከ ማፈንዳት ያደርሳል፡፡ ይህ እንዳይከሰት የሳፕላይ ጋኖች ይገነባሉ፡፡ ይህ ጋን በቱቦዎቹ የሚያልፈውን ውሃ ግፊት በመቀነስና ፈጥነቱን (velocity) ከ 0.5-2 m/s በማድረግ እና ወደ ቱቦዎቹ የሚገባን ሃይል በመቀነስ (Energy dissipate ) ቱቦዎቹ  ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ያስወግዳል፡፡ ይህ ጋን ከፍ ባለ ቦታ ይተከላል ነገር ግን ከፍታው ከService reservoir ያነሰ ነው።

#Hydraulics
1.5K viewsENG Sintayehu Melese, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 15:29:50
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ፕሌት any Size & thickness
ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

ስልክ 0994941706 ወይም 0910379303 ደውለው ያግኙን
ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት
                 ቁ.3 በቅርቡ ቄራ ላይ ይጠብቁን
ከቃላችን ይልቅ ስራችን ይናገራል።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነዉ።
2.0K viewsENG Sintayehu Melese, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 12:20:53
ጥቁር ምንጣፍ ወይስ አስፋልት ያስባለው አነጋጋሪው የህንድ አስፋልት

በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ጃልና የተሰኘው ወረዳ ነዋሪዎች ለአመታት የመንገድ ይገንባልን ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ አግኝቷል።  ነገር ግን ደስታቸውን የቅጽበት ሆኖ እንዲቀር የሚያደርግ ክስተት ገጥሟቸዋል ይላል የአልዐይን ዘገባ።

የጠጠር መንገዳቸው የለበሰው አስፋልት በቀላሉ እንደምንጣፍ ሊነሳ የሚችል በሌላ ቋንቋም ጥቁር ምንጣፍ ሆኖ አግኝተውታል።

በእጃቸው ሲያነሱትም ከስሩ ጨርቅ ነገር ለብሶ ከላዩ ላይ በስሱ አሽዋና ሬንጂ ተደርጎበት የተሰራ መሆኑንም ያረጋግጣሉ። መንገዱን የሰራውን ተቋራጭ ሲጠይቁት አዲስ የጀርመን ቴክኖሎጂ ተጠቅሜያለሁ ሲል ተሳልቋል።


https://t.me/ethioengineers1
2.9K viewsENG Sintayehu Melese, 09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 10:38:59
  Here is detail for the new class schedule.

Option 1 is for detail package( 8 separate packages available , each for 2 months)

Option 2 is for separate software need( each for 3 weeks)


Class Starts on June 19/2023

Registration is active

0911890392 / 0920933016

Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
4.4K viewsENG Sintayehu Melese, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ