Get Mystery Box with random crypto!

የውሃ ጋኖች (water supply Reservoir) . የውሃ ጋኖች ከጥቅማቸው አንፃር ለ ሶስት ይ | Ethio Construction

የውሃ ጋኖች (water supply Reservoir)
.
የውሃ ጋኖች ከጥቅማቸው አንፃር ለ ሶስት ይከፈላሉ
.
1-Collector reservoir
2-Service reservoir
3-Supply reservoir
.
እያንዳንዱ ጥቅማቸው ምንድነው……
.
[Collector reservoir ]
.
ይህ የጋን አይነት ዋና ስራው ውሃው ከሚመነጭበት (የገጸ ምድር ወይም የከርሰ ምድር ውሃ) ቦታ ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚቀመጥበት ጋን ነው፡፡ ጥቅሙ የተሰበሰበውን ውሃ ወደተለያዩ ጋኖች እስኪሰራጭ በጊዜያዊነት እንዲቀመጥና ውሃው ለጋኖቹ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጉልበት እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡ ብዙን ጊዜ ውሃው ከሚመነጭበት ቦታ አቅራቢያ ይተከላል፡፡ ውሃ ፈሳሽ እንደመሆኑ ብዙን ግዜ ሚፈልቀው ከፍታቸው ካነሱ ቦታዎች ስለሆነ ከሌሎች ጋኖች ይልቅ የዚህ ጋን ከፍታ (elevation) ያንሳል፡፡
.
[Service reservoir]
.
ይህ የጋን አይነት በቋሚነት ከcollecter reservoir የተቀበለውን ውሃ የሚያርፍበት ነው፡፡ አሰራሩም ከሌሎቹ ጋኖች ለየት ይላል ፡፡ ውሃው የሚያደርስበትን ግፊት ለመቋቋም የሚያስቸለውን መካች ጉልበት(reaction force) በበቂ ሁኔታ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ በቁመትም በመጠንም ትልቅ ነው፡፡ ወጪ ለመቀነስ ከፍ ካለ ቦታ ይተከላል (ውሃ በ3 አይነት መንገድ ይከፋፈላል
.
1-የሞተር ሀይልን በመጠቀም

2-የመሬት የመሳብ ሃይልን (gravity force) በመጠቀም።

3-የሞተር ሃይልንና የመሬት የስበት ሃይልን በማጣመር በመጠቀም እንዲሰራጭ ይደረጋል ፡፡

በአሁን ጊዜ ሶስተኛው አማራጭ በስፋታ አገልግሎት ላይ ይውላል ይህ አማራጭ ከወጪም አንፃር በጣም ተመራጭ ነው ለዚህ ዘዴ ተመራጩ ደግሞ የservice reservoir ከፍ ካለ ቦታላይ መተከል ወሳኝነት አለው፡፡)
ከዚህ ጋን ቀጥታ ለስርጭት ቧንቧ አይገጠምም ምክንያቱም ከጋኑ የሚወጣው ውሃ ከፍተኛ ጉልበት ስላለው የማሰራጫ ቱቦዎችን ሊያፈነዳ ይችላል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ቀጣዩን የጋን አይነት መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
.
[Supply  reservoir]
.

የዚህ ጋን ዋና ጥቅም ውሃውን ለስርጭት ወደ ስርጭት ቱቦዎች እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከሰርቪስ ጋን ቀጥታ ወደ ስርጭት ቧንቧ ውሃ አይገባም ምክንያቱም ከፍተኛ ሀይል ስላለው የቧንቧዎቹን የመቆየት አቅም ያሳጥራል ብሎም እስከ ማፈንዳት ያደርሳል፡፡ ይህ እንዳይከሰት የሳፕላይ ጋኖች ይገነባሉ፡፡ ይህ ጋን በቱቦዎቹ የሚያልፈውን ውሃ ግፊት በመቀነስና ፈጥነቱን (velocity) ከ 0.5-2 m/s በማድረግ እና ወደ ቱቦዎቹ የሚገባን ሃይል በመቀነስ (Energy dissipate ) ቱቦዎቹ  ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ያስወግዳል፡፡ ይህ ጋን ከፍ ባለ ቦታ ይተከላል ነገር ግን ከፍታው ከService reservoir ያነሰ ነው።

#Hydraulics