Get Mystery Box with random crypto!

Advance Security vs Performance Security. 1. Advance security | Ethio Construction

Advance Security vs
Performance Security.

1. Advance security

ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው የቅድም ክፍያ ገንዘብ በሚከፈለው የገንዘብ መጠን ልክ የሚያሲዘው የባንክ ዋስትና ቦንድ ነው። እውነተኛነቱ በተረጋገጠ ቼክ፣ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ወይም ከህጋዊ ጥቃቅን ማይክሮ ፋይናንስ የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርበታል።
ስራ ተቋራጩ የወሰደውን ቅድመ ክፍያ ከፍሎ እስኪጨርስ ያስያዘው ዋስትና ግዜው ማለቅ(Expire) አይችልም። ከአንድ ወር ቀደም ብሎ የዋስትና ቀነ ገደቡ ከማለፉ በፊት ከአማካሪ በሚፃፍለት ደብዳቤ መሰረት ሊታደስ ይገባል። ነገር ግን ስራ ተቋራጩ ያስያዘውን ዋስትና ቀነ ገደቡ አልፎ ሳያሳድስ ቢቀር ቀሪ ያልተከፈለ ቅድመ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ከሚቀጥለው ክፍያ ቅፅ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
ስራ ተቋራጩ ያስያዘውን ዋስትና ቅድመ ክፍያ ገንዘብ ከፍሎ እንደጨረሰ ተመላሽ ይደረግለታል።
የተለየ የቅድመ ክፍያ እና የዋስትና አከፋፈል አካሔድ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/ ይችላል።

2. Performance Security

ስራ ተቋራጩ ውል ተቀብሎ ተፈፃሚ ማድረግ የሚችልበትን ለብቃት ማረጋገጫ የሚያሲዘው ዋስትና ነው። ውል በተፈራረመ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ (15) ውሉ የሚያዘውን መጠን ዋስትና ያቀርባል ።
ዋስትናው ስራ ተቋራጩ በተገቢው መንገድ ውሉን ተፈፃሚ ሳያደርግ ቢቀር ለውል ሰጪ (ባለቤት) እንደ ካሳ ክፍያ ይሆናል።
እውነተኛነቱ በተረጋገጠ ቼክ፣ የባንክ ዋስትና ወይም ከህጋዊ ጥቃቅን ማይክሮ ፋይናንስ የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ውሉ ላይ በተቀመጠው ፎርማት መሰረት ማስያዝ ይኖርበታል።
ይህ ዋስትና ሳይቀርብ ምንም አይነት ክፍይ ተፈፃሚ ሊደረግ አይገባም። ስራው ተጠናቆ እስኪያልቅ


https://t.me/ethioengineers1