Get Mystery Box with random crypto!

በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት ሥልጠና ያጠናቀቁ ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ ነው። በኮንስትራ | Ethio Construction

በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት ሥልጠና ያጠናቀቁ ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ ነው።

በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት የሚያበቃቸውን ሥልጠና ያጠናቀቁ የመጀመሪያውዙር ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ መሆኑን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሲቭል ኢንጂነሪንግ፣ በኮንስትራክሽን ማናጅሜንት ቴክኖሎጂ፣ በአርክቴክቸር እና መሰል ሙያዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ተማሪዎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ነበር ተብሏል።

ሥልጠናው፥ ከዛሬ ሦሥት ዓመት በፊት በቀድሞው ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የጀርመን ኮንስትራክሽን ማኅበራት ፌዴሬሽን በጋራ እንደተጀመረ ነበር።

‘ጎኤቴ’ በመባል በሚታወቀው የጀርመን ባህል እና ቋንቋ ኢንስቲትዩት ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ከ50 በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 11ዱ ሥልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ የጀርመን ኮንስትራክሽን ፌዴሬሽን የሚፈልገውን መስፈርት አሟልተው የመጨረሻውን ፈተና በማለፍ ለጉዞ ዝግጁ ሲሆኑ 6ቱ ጀርመን ከሚገኙ አሠሪዎቻቸው ጋር የሥራ ውል ተፈራርመዋል።

ሥልጠናቸውን አጠናቀው፣ የመጨረሻው ምዘና አልፈው እና አስፈላጊውን የሥራ ትዕዛዝ ተቀብለው ወደ ጀርመን ሀገር ለመጓዝ ዝግጀታቸውን ያጠናቀቁ እንዲሁም በመሠልጠን ላይ የሚገኙትን ምሩቃንን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ማነጋገራቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

      
https://t.me/ethioengineers1