Get Mystery Box with random crypto!

መያዥያ ገንዘብ (Retention money) ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማ | Ethio Construction

መያዥያ ገንዘብ (Retention money)

ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ/defect liability period / ሀላፊነት
ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከእያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ
ገንዘብ ነው።

ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል።

ሆኖም ከ አስር ፐርሰንት (10%) የበለጠ መሆን አይችልም።

በሀገራችን አብዛኛውን ግዜ አምስት ፐርሰንት(5%) ብቻ የተለመደ ነው።

ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስራው ላይ ስህተት ቢፈጠር በውሉ ላይ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ ከመጨረሻ ርክክብ ጋር በ
አርባ አምስት (45) ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።

@ethioengineers1