Get Mystery Box with random crypto!

Ethio telecom

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_telecom
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 347.09K
የሰርጥ መግለጫ

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 62

2023-05-21 11:01:02
በደግነት የምታሳልፉት መልካም እለተ ሰንበት ተመኘን!

#happyweekend #sharingiscaring
21.3K views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 16:55:39
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሁለቱ ተቋማት የሥራ ጉብኝት አደረጉ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማረ አሰፋ እና በኩባንያችን ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር ኢንጂነር ታሪኩ ደምሴ የተመራ የከፍተኛ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ቡድን በሁለቱ ተቋማት በመገኘት የቴክኒካል ሳይቶችን የጎበኘ ሲሆን በጋራ እየሰሯቸው ባሉ ስራዎች ዙሪያ ገንቢ ውይይት አድርገዋል።

የጋራ ቡድኑ አባላትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኔትወርክ እና የሴኪውሪቲ መቆጣጠሪያ ማዕከላትን እንዲሁም የኩባንያችንን የኔትወርክ መቆጣጠሪያ ማዕከል እና ሞጁላር ዳታ ሴንተር በጋራ ጎብኝተዋል።

በሃገራችን ቀደምት አገልግሎት ሰጪ የሆኑት ሁለቱ ተቋማት በትብብር በመስራት ረጅም ዓመታትን አብረው የዘለቁ እንደመሆኑ በቀጣይም ይህንኑ አጠናክረው በመቀጠል በበርካታ መስኮች አብረው ለመስራት ቁርጠኛነታቸውን ኃላፊዎቹ አረጋግጠዋል፡፡
29.8K views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 09:01:20
በእረፍት ቀንዎ በአይነቱ የመጀመሪያው የሆነውንና የሃገራችንን ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፉ የግብርና ውጤቶች የሚያሳየውን ኤግዚቢሽን በሳይንስ ሙዚየም ተገኝተው በነጻ እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል
28.6K views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 17:00:28
ከመቼውም በተሻለ ለድርጅትዎ የሚበጅ ወጪ ቆጣቢ አስተማማኝ መላ፣ ሞባይል ሼር ፕላን!

በድምፅ ላይ እስከ 97%፣ ዳታ ላይ እስከ 286% እንዲሁም መልዕክት ላይ እስከ 136% ጭማሪ አገልግሎት ታክሎበት የቀረበውን ሞባይል ሼር ፕላን ለድርጅትዎ ሠራተኞች እንደ አስፈላጊነቱ ማከፋፈል እንዲሁም ማስተዳደር ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ bit.ly/38lAkuu ይጎብኙ

አገልግሎቱን በአቅራቢያዎ በሚገኝ የድርጅት የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ያግኙ
30.9K viewsedited  14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 09:00:03
ፍቅርዎን ይግለጹ አብሮነትዎን ያጠንክሩ!

በጥቅል ያጋሩ አገልግሎት ያለዎትን የሞባይል ጥቅል ለሚወዷቸው በማጋራት ደስታን ይጋሩ!

በማይኢትዮቴል መተግበሪያ ወይም
*999# ደውለው 8 (የኔ አገልግሎቶች) - 2 ጥቅል ለማስተላለፍን መርጠው ሂደቱን ይከተሉ።
የአገልግሎት ክፍያ 12 ሳንቲም ብቻ!
31.5K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 17:32:19
የቦታ ርቀት ሳይገድብዎ ባሉበት ሆነው በጋራ ያውጉ፣ ይወያዩ፣ ይጨዋወቱ!

በኮንፈረንስ ጥሪ አገልግሎታችን  ስልክ ሳይዘጉ እስከ አምስት ሰው ድረስ በአንድ ጊዜ መደወል እና በጋራ ለመወያየት:
የመጀመሪያውን ስልክ ደውለው ስልኩ ከተነሳ በኋላ ደንበኛውን መስመር ላይ እንዲጠብቅ በማድረግ ተጨማሪ ስልክ ማስደወያውን በመጫን(Add call) ለሌላኛው ደንበኛ ይደውሉ --›  በመቀጠል ሁለተኛው ደንበኛ ስልኩን እንዳነሳ ያገናኙ(Merge) የሚለውን በመጫን የስልክ ጥሪዎቹን ወደ አንድ ማምጣት ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ ሰዎችን ወደ ውይይቱ ለማካተት ተመሳሳይ ሂደትን ይከተሉ፡፡
14.2K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 12:07:23
ከቀደምት የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት መካከል አንዱ
#throwbackThursday #ትውስታ
20.9K viewsedited  09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 09:05:23
በርካታ አማራጮች  ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ገንዘብ ለማስገባት

ለነዳጅ፣ ለመብራት እንዲሁም ለሌሎች ክፍያዎች፤ ለትራንስፖርት ወይም ለግብይት ክፍያ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ገንዘብ ገቢ ለማድረግ

በአቅራቢያዎ በሚገኙ የቴሌብር ወኪሎች
ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 20 ባንኮች የሞባይል ባንኪንግ
በተጨማሪም በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከሎችን ይጠቀሙ።
23.1K viewsedited  06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 17:22:34
ጊዜ ዋጋዋ እጅግ ንሯል፤ በዚህ ዘመን በወረፋ ጊዜ እና ውድ ጉልበትዎ እንዳይባክን የዘመነው ቴሌብር አለልዎ!
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያዎን ካሉበት ሳይንቀሳቀሱ በቀላሉ በቴሌብር ለመክፈል ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ http://onelink.to/fpgu4m ያውርዱ ወይም *127# ይደውሉ

ቴሌብር - ፈጣን፣ ቀላል፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
28.8K views14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 12:43:13
በጥሪ ማሣመሪያ እየተዝናኑ እና ደዋዮችዎን እያዝናኑ ይሸለሙ!

አሁን የመሸለም ተራው የእርስዎ ነው!
4 ላፕቶፖች፣ 4 ታብሌቶች፣ 4 ስማርት ስልኮች፣ 4 ስማርት ሰዓቶች እንዲሁም የድምፅ እና የኢንተርኔት ጥቅል ሽልማቶች እርስዎን እየጠበቁ ነው።

ደዋዮችዎን ዘና ለማድረግ ወደ 822 A ብለው በመላክ ይመዝገቡ
ወደ ሌሎች ሲደውሉ ራስዎ ለሚሰሙት ደግሞ A1 ብለው ወደ 822 ይላኩ
በተጨማሪም ወደ 822 ወይም *822# በመደወል ወይም በ www.crbt.et በቀላሉ ይመዝገቡ፣ ደጋግመው ሙዚቃ ይቀይሩ፤ የመሸለም እድልዎን ያስፉ!
30.2K views09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ