Get Mystery Box with random crypto!

የቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ዋና ኃላፊ አምባሳደር ሁ ቻንግቹን የተመራ ልኡክ | Ethio telecom

የቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ዋና ኃላፊ አምባሳደር ሁ ቻንግቹን የተመራ ልኡክ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኩባንያችንን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም የሀገራችንን የቴሌኮም ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስከደረሰበት የእድገት ደረጃ የሚያመላክቱ ቴክኖሎጂዎችን የተመለከቱ ሲሆን ስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ማዕድን ልማት፣ ስማርት ቱሪዝም የመሳሰሉት የዲጂታል ሶሉሽኖች ለሀገራችን ዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት የሚያበረክቱት ሚና ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ አምባሳደሩ ኩባንያችን ለዲጂታል ሶሉሽኖች የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እና የገነባው ግዙፍ መሰረተ ልማት በእጅጉ አድንቀው ኩባንያው በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ወደላቀ የከፍታ ምዕራፍ እንደሚሸጋገር አመላካች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia