Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja — ETHIO-MEREJA®
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.05K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 279

2022-05-30 15:58:45
ቴሌግራም https://telegram.me/onlineshoppingce
አድራሻችን:- ቦሌ መድሐኔዓለም ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ፊትለፊት አለምነሽ ፕላዛ ሱቅ ቁጥር 05

+251941661030
12.9K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 13:02:05 በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ፍቅረኛዋ ከድር ሀሰን ፍርድ ቤት ቀረበ!

የአ/አ ፖሊስ መርማሪ ከ15 ቀን በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በሞሴ ሆቴል ከ8ኛ ፎቅ ህይወቷ አልፎ ስለተገኘችው በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል ፍቅረኛዋ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ ሰፊ የምርመራ ስራ እያከናወነ መሆኑን ለችሎቱ አስታውቋል።

የሟች የአሟሟት ሁኔታን ለማጣራት ለአስከሬን ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆ ውጤት እየተጠባበቀ መሆኑን የገለጸው መርማራ ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማቅረብ እንዲያስችለው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪ ከድር ሀሰን በበኩሉ ከጂማ መተው በሆቴል እንደነበሩ ገልጾ ሟች ሀናን መሐመድ የሚወዳት ፍቅረኛው መሆኗንና ህይወቷ እስካለፈበት ሰዓት በመካከላቸው ምንም አይነት ጸብም ሆነ ጭቅጭቅ እንደሌለ ለፍርድ ቤት አብራርቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰውን ወሬ በተሰማ ቁጥር በየጊዜው እየተጠራሁ እጠየቃለው እውነቱ ግን ሀናን የማፈቅራት ሚስቴ ናት እሷ ነጋዴ ናት ዕቃ ገዝቼ እንድመጣ አዛኝ በሰላም ተነጋግረን ፊቴን ታጥቤ ከሆቴሉ በደረጃ በኩል ነው የወረድኩት ስወጣ ባለቤቴ ደህና ነበረች ወጥቼ ሄጄ 2:00 ሰዓት ላይ በስልክ ደውላ በአስቸኳይ ተመለስ አለቺኝ ከዛ ስልኩን ዘጋች እኔም ለሆቴሉ ማናጀር ደውዬ ምን እንደሆነች እንዲጠይቅለኝ ነገርኩት በኋላ ላይ የሆቴሉ ማናጀር ደውሎ ለኔ መንገር ፈርቶ ደህናት ፈጥነህ ና አለኝ ከዛ እሷን ወደ ቤተዛታ ወስደዋት ነበር ቤተዛታ ስደርስ ህይወቷ አልፎ አገኘኋት ወዲያው ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ እንዲያጣሩልኝ አመለከትኩ ሲል ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ እራሴን አጠፋለው እያለች ትናገር እንደነበር የገለጸው ተጠርጣሪ በማላታይን እራሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ ሞክራ እንደነበር ቤተሰቦቿ እንደሚያውቁ ለችሎቱ አስረድቷል።

በዕለቱ ሆቴል ውስጥ የተፈጠረውን ሁኔታ ከሆቴሉ ካሜራ ላይ የተቀሳቃሽ ምስል አይተው ማጣራት እየተቻለ እኔ ታስሬ የምወዳትን የሚስቴን አስከሬን ተቀብዬ መቅበር አልቻልኩም ሲል ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

በፖሊስ በኩል የተቀሳቃሽ ካሜራ ማስረጃ እንደተቀበለና እንዳልተቀበለ ከፍርድ ቤቱ ለተነሳ ጥያቄ አለመቀበሉንየገለጸው መርማሪው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚቀበል ገልጿል።

ጉዳዩን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተጠርጣሪ የወንጀል ተሳትፎ ተለይቶ እንዲቀርብ ትዛዝ በመስጠት ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ የ 11 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።

የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

Via Tarik Adugna
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.7K viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 13:01:21 ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ ዛሬ ረፋዱን ከእስር ተለቃለች!!

የ"ፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ " የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ ዛሬ ረፋዱን ከእስር መለቀቋን የጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ለሚ ታዬ ተናግረዋል።

ጋዜጠኛ ሶቦንቱ በፖሊስ ቁጥጥር የዋለችው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 18/2014 አመሻሽ ላይ ከስራ ቦታዋ ስትወጣ መሆኑን በወቅቱ ተገልጾ ነበር። ጋዜጠኛዋ ከእስር ከተለቀቀች በኋላ በስልክ እንዳነጋገሯት የገለጹት የቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ፖሊስ " ስንፈልግሽ ትመጫለሽ " በሚል መፈታቷን እንደነገረቻቸው አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
14.2K viewsedited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 12:00:31
የሳምንታዊው "ፍትህ" መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ባለቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ረፋዱ ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ፣ ለግንቦት 29 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ተለዋጩ ቀጠሮ ካለፈው ቀጠሮ ጀምሮ የሚቆጠር የ10 ቀን ቀጠሮ እንደሆነ ችሎቱ ተናግሯል። ችሎቱ ዛሬ የተሰየመው የተጠርጥጣሪው ጉዳይ መታየት ያለበት በመገናኛ ብዙኀን አዋጁ ነው ወይስ አይደለም? በሚለው ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር። ሆኖም ችሎቱ መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ማስረጃ ሰብስቦ ሳይጨርስ፣ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ መስጠት እንደማይችል በመግለጽ ተለዋጩን ቀጠሮ ሊሰጥ ችሏል።

በዛሬው ችሎት የተጠርጣሪው ጠበቆች፣ ተጠርጣሪው በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰረበት ክፍል እጅግ የተጣበበ እና የመጸዳጃ ችግር ያለበት መሆኑን በመጥቀስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታቸውን ለችሎቱ አቅርበዋል። ለ30 እስረኛ በተዘጋጀ ክፍል ውስጥ 400 እስረኞች ታስረው እንደሚገኙ የተመስገን ጠበቃ ኄኖክ አክሊሉ ለችሎቱ ተናግረዋል።

ችሎቱም ፖሊስ በአቤቱታው ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቆ፣ ፖሊስ ችግሩ የሁሉም እስረኞች ችግር እንጅ ባንድ እስረኛ ላይ የተፈጸመ አይደለም በማለት ምላሽ ሰጥቷል።

የፖሊስን ማብራሪያ ያደመጡት ዳኛ፣ ተጠርጣሪው ንጽህናው ወደተጠበቀ እና በቂ መጸዳጃና መታጠቢያ ወዳለው ክፍል እንዲዛወር ያዘዙ ሲሆን፣ ትዕዛዙ እስከ ነገ ድረስ ተፈጻሚ እንዲሆንም አሳስበዋል። የችሎቱ ትዕዛዝ እስከ ነገ ተፈጻሚ ካልሆነ፣ የተጠርጣሪው ጠበቃ ሌላ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ችሎቱ ገልጧል። [ዋዜማ ራዲዮ]
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
14.9K viewsedited  09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 10:30:45
መልካም ዜና!
በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመረቀ።

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራ የሚገኝው የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ ብቁ የጤና ተቋማት በመገንባት ተመጣጣኝና ፍትሀዊ የጤና አገልግሎትን ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው በአሁን ሰአት ለምርቃት የበቃው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የተሰራው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ቀድሞ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው ተገልጿል።

በአጠቃላይ በሳምንት ለ240 ዜጎች አገልግሎት የመስጠት አቅም እንዳለው ተነግሯል። በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ዜጎች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል የተባለለት ማዕከሉ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች በነፃ አገልግሎቱን በመስጠት ተስፋ እንደሚሆንም ተጠቁሟል። ማዕከሉ አለም አቀፍ ደረጃውን ያሟላ የህንጻ ግንባታን ይዞ ተገንብቷል።

T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.1K viewsedited  07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 21:09:51
‹‹ከኢትዮጵያዊነት የሚቀዳ ጀግንነት ከእያንዳንዱ መኮንን ይጠበቃል›› - ጠቅለይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለ69ኛው ጊዜ በምክትል መቶ አለቃነት ያሰለጠናቸውን የጥቁር አንበሳ ኮርስ መኮንንኖችን አስመርቋል፡፡

በምርቃት ስነስርዐቱ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ ጠቅለይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ መስመራዊ መኮንንኖች የኢትዮጵያ መኮንን መሆን ስታስቡ ጀግንነት፣ አላማና የማይነጥፍ እወቀት ሊኖራችሁ ይገባል ብለዋል፡፡

"ጀግንነት ከኢትዮጵያዊ ማንነት የተወረሰ ነው፤ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ኢትዮጵያዊነት የሚባለው ማንነትና ሕዝብ ከጀግንነት ጋር ተነጣጥሎ የሚታይ ባለመሆኑ ከኢትዮጵያዊነት የሚቀዳ ጀግንነት ከእያንዳንዱ መኮንን ይጠበቃል" ብለዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ዛሬ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ለመሆን የወሰናችሁበት፣ የተሰጣችሁን ስልጠና በበቂ ሁኔታ ተቀብላችሁ የተመረቃችሁና ምክትል መቶ አለቃ የምትባሉ፣ በውስጣችሁ ብዙ ጀነራሎች፣ ብዙ የሀገር መሪዎች፣ የሀገር ኩራቶች የሚፈጠሩበት ታሪካዊ እለት ነው ሲሉም ለተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በሚቀጥለው የሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ የማይረሳ ታሪካዊ ቀን ስለሆነ የዛሬ ምክትል መቶ አለቃዎች የነገ ጀነራሎች እንኳን ደስ አላችሁም ብለዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
8.1K viewsedited  18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 20:58:58
ቴሌግራም https://telegram.me/onlineshoppingce
አድራሻችን:- ቦሌ መድሐኔዓለም ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ፊትለፊት አለምነሽ ፕላዛ ሱቅ ቁጥር 05

+251941661030
7.7K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 20:58:41
Double A፣ ከአጓጊ ሽልማቶች ጋር ተመልሷል

የ“Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ፡-
 የተለያዩ ስጦታዎችን ለምሳሌ፦ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣የውሃ ማጣሪያ፣ ማይክሮዌቭ/የምግብ ማሞቂያ ማሽን፣ የጁስ መፍጫ እና የመሳሰሉትን ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

የ QR ነጥብ መሰብሰቢያ ፕሮግራማችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ! ደጋግመው QR ስካን ሲያርጉ ፤ ተጨማሪ ሽልማቶችን ያገኛሉ፡፡

መተግበርያውን ለማውረድ እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or

https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
7.8K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 19:03:17
22 ሰዎችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው የኔፓል አውሮፕላን ጠፋ!!

ንብረትነቱ የግል አየርመንገድ የሆነ አነስተኛ የመንገደኞች አውሮፕላን 22 ሰዎችን አሳፍሮ በመብረር ላይ ሳላ በተራራማዋ የኔፓል ቦታ የደረሰበት ጠፍቷል፡፡

ባለስልጣናት እንደተናገሩት የአካባቢው ሰዎች እሳት ማየታቸውን ወደገለጹበት ቦታ የፍለጋ ቡድን መሰማራቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የኔፓል ቴሌቪዥን በልያንኩ ኮህል አካባቢ ያሉ ሰዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው ቲቤትን በሚያዋስነው የሂማሊያ ተራራ ስር አርክራፍቷ በእሳት ስትያያዝ አይተዋል፡፡

ዲ ሃቪላንድ ካናዳ ዲኤች ሲ-6-300 ጠዊነ ኦተር ለ20 ደቂቃ በራራ የተነሳ ቢሆን ለማረፍ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ከመቆጣጠሪያ ጣቢያው ያለው ግንኙነት ተቋርጧል፡፡ ቁጥጥሩ የሚያደርገው የታራ ኤየር ኩባንያ ነበር፡፡

የታራ አየር ቃል አቀባይ የፍለጋ ቡድን ወደ ስፍራው መሰማራቱን ለሮይተርስ ገልጿል፡፡ የኔፓል ሲቪል አቬሽን ማለስልጣንም የፍለጋ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን አስታውቋል፡፡ አራት ህንዳውያን፤ሁለት ጀርመናውያንን እና 16 የኔፓል ዜጎችን አሳፍሮ ነበር ያለው አየርመንገዱ በረራው ከኔፓል ዋና ከተማ ከታማንዱ ዋና ከተማ በምስራቅ በኩል 125 ኪሜ ርቀት ወደምትገኘው የቱሪስት መዳረሻዋ ፖክሃራ ከተማ ነበር፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.7K viewsedited  16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 15:26:05
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ለእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት የሚሆኑ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረከበ።

በመርሀ ግብሩ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፤ የብልጽግና ፓርቲ አማራ ክልል ቅርንጫፍ ሀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ፤ የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሀይለማርያም ከፊያለው እና ሌሎች ከፍተኛ የክልል፣የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረክቧል።

በክልላችን ከነበረብን የህልውና ትግል ጎን ለጎን በብዙ ጥረት ከ4.8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ በምርት ለመሸፈን ዝግጅት እንደተደረገ በመግለጽ በዚህ አመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ዛሬ ከ324 የሜካናይዜሽን ትራክተር ለአርሶአደሮች መስጠቱን የገለጹት የክልሉ የግብርና ቢሮ ሀላፊው ዶ/ር ሀይለማርያም ከፍያለው ናቸው። ሀላፊው አክለውም ግብርናውን በማዘመን በቀጣይ የ2014 መጨረሻዎች 700 ትራክተሮችን እንደሚያቀርቡ በመግለጽ በቀጣይ አምስት አመታት ከ26,000 ትራክተሮች በላይ ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ አቅዶ እየሰራ እንደሆ ገልጸዋል።

T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.8K viewsedited  12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ