Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.33K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 278

2022-05-29 19:03:17
22 ሰዎችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው የኔፓል አውሮፕላን ጠፋ!!

ንብረትነቱ የግል አየርመንገድ የሆነ አነስተኛ የመንገደኞች አውሮፕላን 22 ሰዎችን አሳፍሮ በመብረር ላይ ሳላ በተራራማዋ የኔፓል ቦታ የደረሰበት ጠፍቷል፡፡

ባለስልጣናት እንደተናገሩት የአካባቢው ሰዎች እሳት ማየታቸውን ወደገለጹበት ቦታ የፍለጋ ቡድን መሰማራቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የኔፓል ቴሌቪዥን በልያንኩ ኮህል አካባቢ ያሉ ሰዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው ቲቤትን በሚያዋስነው የሂማሊያ ተራራ ስር አርክራፍቷ በእሳት ስትያያዝ አይተዋል፡፡

ዲ ሃቪላንድ ካናዳ ዲኤች ሲ-6-300 ጠዊነ ኦተር ለ20 ደቂቃ በራራ የተነሳ ቢሆን ለማረፍ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ከመቆጣጠሪያ ጣቢያው ያለው ግንኙነት ተቋርጧል፡፡ ቁጥጥሩ የሚያደርገው የታራ ኤየር ኩባንያ ነበር፡፡

የታራ አየር ቃል አቀባይ የፍለጋ ቡድን ወደ ስፍራው መሰማራቱን ለሮይተርስ ገልጿል፡፡ የኔፓል ሲቪል አቬሽን ማለስልጣንም የፍለጋ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን አስታውቋል፡፡ አራት ህንዳውያን፤ሁለት ጀርመናውያንን እና 16 የኔፓል ዜጎችን አሳፍሮ ነበር ያለው አየርመንገዱ በረራው ከኔፓል ዋና ከተማ ከታማንዱ ዋና ከተማ በምስራቅ በኩል 125 ኪሜ ርቀት ወደምትገኘው የቱሪስት መዳረሻዋ ፖክሃራ ከተማ ነበር፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.7K viewsedited  16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 15:26:05
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ለእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት የሚሆኑ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረከበ።

በመርሀ ግብሩ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፤ የብልጽግና ፓርቲ አማራ ክልል ቅርንጫፍ ሀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ፤ የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሀይለማርያም ከፊያለው እና ሌሎች ከፍተኛ የክልል፣የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረክቧል።

በክልላችን ከነበረብን የህልውና ትግል ጎን ለጎን በብዙ ጥረት ከ4.8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ በምርት ለመሸፈን ዝግጅት እንደተደረገ በመግለጽ በዚህ አመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ዛሬ ከ324 የሜካናይዜሽን ትራክተር ለአርሶአደሮች መስጠቱን የገለጹት የክልሉ የግብርና ቢሮ ሀላፊው ዶ/ር ሀይለማርያም ከፍያለው ናቸው። ሀላፊው አክለውም ግብርናውን በማዘመን በቀጣይ የ2014 መጨረሻዎች 700 ትራክተሮችን እንደሚያቀርቡ በመግለጽ በቀጣይ አምስት አመታት ከ26,000 ትራክተሮች በላይ ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ አቅዶ እየሰራ እንደሆ ገልጸዋል።

T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.8K viewsedited  12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 11:59:15
ዩክሬን በአሜሪካ የተሰሩ የረጅም ርቀት ሮኬቶች እንደሚያስፈልጓት ገለጸች!!

የሩሲያ ኃይሎች እስካሁን በሲቪዬሮዶኔትስክ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውን የሊማን የባቡር ማእከል የያዙ ሲሆን በምስራቅ ዩክሬን ተጨማሪ ወታደራዊ ይዞታዎች ለመቆጣጠር መጠነ ሰፊ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው ተብሏል፡፡

ጥቃቶቹ መቋቋም የከበዳት የምትመስለው ዩክሬን በበኩሏ ተጨማሪና ረዥም ርቀት የሚምዘገዘጉ የጦር መሳሪያዎች ያስፈልገኛል ስትል ምዕራባውያንን ጠይቃለች፡፡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ እና የሰላም ተደራዳሪ ማይካሂሎ ፖዶሊያክ “በአሜሪካ የተሰሩ የረዥም ርቀት ባለብዙ ሮኬት ማስወንጨፊያዎችን ያስፈልጉናል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
16.3K viewsedited  08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 11:33:16
በነጻ ተጨማሪ የሕክምና ምክርን ከእኛ ያግኙ

አቺባደም ሆስፒታል

ትክክለኛውን ምርመራ ለማድረግ ወይም ተገቢውን የሕክምና አማራጮችን ለመለየት ከፈለጉ ተጨማሪ የሐኪሞች አስተያየትና ምክርን ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በቱርክ የሚገኘው አቺባደም የጤና ክብካቤ ቡድን ይህንን አገልግሎት በነጻ ይሰጣል። የህክምና መረጃዎን በማቅረብ ከአለማችንን የታወቁ የህክምና ባለሙያዎችን አስተያየትና ምክር ማግኘት ይችላሉ።

ለተከታታይ ጠቃሚ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/acibadem_ethiopia ይቀላቀሉ፡፡
15.4K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 11:23:40
Double A፣ ከአጓጊ ሽልማቶች ጋር ተመልሷል

የ“Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ፡-
 የተለያዩ ስጦታዎችን ለምሳሌ፦ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣የውሃ ማጣሪያ፣ ማይክሮዌቭ/የምግብ ማሞቂያ ማሽን፣ የጁስ መፍጫ እና የመሳሰሉትን ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

የ QR ነጥብ መሰብሰቢያ ፕሮግራማችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ! ደጋግመው QR ስካን ሲያርጉ ፤ ተጨማሪ ሽልማቶችን ያገኛሉ፡፡

መተግበርያውን ለማውረድ እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or

https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
14.8K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 01:02:59
#ጤናመረጃ

10 አስገራሚ የአቮካዶ የጤና ጥቅሞች!!

አቮካዶን መመገብ ከሚያስገኛቸው ብዙ ጥቅሞች ዋነኞቹን እናያለን።

1) አቮካዶ የደም ግፊትንና የደም ዝውውርን የሚያስተካክለውን ፖታሲየም የተሰኝውን ንጥረ ነገር በብዛት ይዟል፡፡ ይህ ፖታሲየምም ሙዝ ውስጥ ከሚገኝው በ10% ይበልጣል።

2) አቮካዶ ፎሌት የተባለ ንጥረ ነገር ያለው ሲሆን ለእርጉዝ ሴቶች በጣም ጠቃሚና ለህፃኑ የአእምሮና አካላት እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት የሚመጣውን ማቅለሽለሽ የሚከላከል ቫይታሚን ቢ6 ይዟል።

3) በአቮካዶ ውስጥ ያለው ሞኖሳቹሬትድ ፋት ለልብ ህመም የሚያጋልጠንን ኮሌስትሮል በመቀነስ ጤናን ያስተካክላል።በተጨማሪም ለስኳር በሸተኞች በደም ውስጥ ያለውን ትራይግላይሴራይድ በመቀነስ ይጠቅማል።

4) አቮካዶ ኦሊይክ አሲድ በውስጡ ይዟል። ይህ አሲድ የጡት ካንሰርን ይከላከልልናል።

5) አቮካዶ ሊየቲን የተባለ ቫይታሚን ሲኖረው ይህ ቫይታሚን የካሮቲን ቫይታሚን ከሆነው ቫይታሚን ኤ ዝርያ የሚመደብ ሲሆን ለአይን ጤንነት በጣም ጠቃሚ ነው።

6) አቮካዶ ከፕሮስቴት ካንሰር የሚከላከሉና የተጐድ ሴሎችን የሚጠግኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ይዟል።

7) አቮካዶ የአፍ ካንሰርን ከመከላከሉ ባሻገር ለመጥፎ የአፍ ጠረን አይነተኛ መፍትሄ ነው።

8) በአቮካዶ ውስጥ ያሉት ኢንዛይምና የምግብ ንጥረ ነገሮች የተጐዳ የጨጓራና የትንሽ አንጀት ግድግዳዎችን በማለስለስ ወደር አይገኝላቸውም።

9) በአንቲ ኦክሲዳንት የበለፀገ ስለሆነ ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡ ምልክቶችን ይከላከላል።ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅምን ይጨምራል የነርቭ ስርዓት ጤናማ እንዲሆን ያደርል።

10) በቫይታሚን የበለፀገ ሲሆን ቆዳችንን ከፍሪራዲካልስ ይከላከላል።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
@ethio_mereja
1.8K viewsedited  22:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 00:36:26
ተጠናቀቀ

ሪያል ማድሪድ ሻምፒዮን ሆኗል !

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በፈረንሳይ ርዕሰ መዲና ፓሪስ በሚገኘው ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም ሲካሄድ ሪያል ማድሪድ ከ ሊቨርፑል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 - 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግብ ቪኒሰስ ጁኒየር አስቆጥሯል። ሪያል ማድሪድ ለአስራ አራተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ።

ቪኒሰስ ጁኒየር በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ግብ ያስቆጠረ አምስተኛው በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ሆኗል። ቪኒሰስ ጁኒየር በዘንድሮ የውድድር አመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በአስር ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን አድርጓል ።

ሊቨርፑል 0 - 1 ሪያል ማድሪድ
ቪኒስየስ ጁኒየር 59'

T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
2.9K viewsedited  21:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 21:40:52
ሩሲያ በታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ከነዳጅ እንደምታገኝ ገለጸች!!

የሩሲያ ፋይናንስ ሚኒስትር እንዳሉት በተያዘው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት ተጨማሪ 14 ቢሊዮን ዶላር ነዳጅ እንደምታገኝ ይጠበቃል። ሚኒስትሩ አንተን ሲሉአኖቭ እንደተናገሩት ባለፈው ዓመት ሩሲያ ከነዳጅ ገበያ ያገኘችው ዓመታዊ ገቢ 9 ቢሊየን ዶላር ነበር።

በተያዘው ዓመት ተጨማሪ 14 ቢሊየን ዶላር ነዳጅ እንደምታገኝ የገለጸችው ሩሲያ፤ ገቢውን የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚዋን ለማረጋጋት እንደምታውለውም ሚኒስትሩ አክለዋል።ከዚህ በተጨማሪም ከዩክሬን ጋር ለጀመረችው ጦርነት ወጪ እንደምታውለውም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከጀመረች ሶስት ወራት አልፎታል።

ጦርነቱን ተከትሎም በአሜሪካ አስተባባሪነት ከ6 ሺህ በላይ ማዕቀቦችን የተለያዩ ሀገራት በሩሲያ ላይ ጥለዋል።

ሩሲያም ወዳጅ አይደሉም ያለቻቸውን ሀገራት ነዳጇን በሩብል እንዲከፍሉ ትዕዛዝ ማስተላለፏን ተከትሎ የአውሮፓ ኩባንያዎች ነዳጅ በሩብል መግዛት ጀምረዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
8.9K viewsedited  18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 20:14:38
የ20 21/22 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ዛሬ ምሽት በፓርክ ደ ፍራንስ ፓሪስ ፍፃሜውን ያገኛል።

የዓመቱ አውሮጳ እግር ኳስ ሻምፒና የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ይካሄዳል። ፓሪስ የተቀናቃኞቹን የስፔኑን ሪያል ማድሪድ እና የእንግሊዙን ሊቨርፑል ክለቦች ደጋፊዎች ተቀብላ የጫወታው መጀመር እየተጠበቀ ነው።

-የመድረኩ ልዕለ ሃያል የ13 ጊዜ የመድረኩ ሻምፒዮን የሆነው የጋላክቲኮ ስብስብ ሪያል ማድሪድ ከሌላኛው በመድረኩ የ6 ጊዜ ባለ ድል የእንግሊዙ ሃያል ክለብ ሊቨርፑል ጋር ይፋለማሉ።

ዘንድሮ ሪያል ማድሪድ በካሪም ቤንዜማ፣ በወጣቶቹ ቭንሽየስ ጁኒየርና ሮድሪጎ፤ በመሃል ሜዳ ተክኒሻን ሉካ ሞድሪች ጥምረት፤ ከአንድም ሁለቴ ሞቶ እየተነሳ ፒ ኤስ ጂ፣ ቼልሲንና ማን ሲቲን አሰናብቶ ለአሥራ አራተኛ ድል ፓሪስ ይገኛል።

ቀያዮቹ ዘንድሮ በቆፍጣናው የታክቲክ ሊቅ የርገን ክሎፕ እየተመራ በቫይዳይክ ድንበሩን አስከብሮ፤ በሞሳላህና በሳይዶ ማኔ ድንቅ ብቃት ታግዞ ለዋታው ይቀርባል። ከወትሮው በተለየ መልኩ ቀድመው የካራባኦና የኤፍ ኤ ዋንጫ በማንሳት በተሻለ ጥንካሬ ላይ የሚገኙ ሲሆን ይህን ዋንጫ በቀላሉ ለማድሪድ ይሰጣሉ ተብሎ አይገመትም ።

ጨዋታው ዛሬ ምሽት 4:00 ይደረጋል ።

ማን ያሸንፋል ? ይገምቱ!

T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.4K viewsedited  17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 19:45:57
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መንግሥት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ!!

ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀረበው መንግሥት የሚያስራቸው ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ በሔደበት ወቅት ነው።

የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ጄይላን አብዲ በሥራው ምክንያት የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ የለም ሲሉ ለጋዜጠኞች መብት ለሚሟገተው ሲፒጄ ተናግረዋል። ኃላፊው ትላንት አርብ ከሲፒጄ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የታሰሩት ፖሊስ ወንጀል ለመፈጸማቸው ማስረጃ በማግኘቱ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ተፈጽመዋል ለሚባሉ ወንጀሎች የቅድመ-ዳኝነት እስርን እንደሚከለክል የጠቀሱት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ" የታሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች ሁሉ ሊፈቱ ይገባል" የሚል ጥሪ ዛሬ ቅዳሜ አቅርበዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
10.6K viewsedited  16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ