2022-05-22 01:25:19
#ጤናመረጃሙዝ ለጤናችን የሚሰጠን 12 አስደናቂ ጥቅሞች!
ሙዝ በንጥረ ነገር ይዘታቸው ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች አንድ ሲሆን በውስጡ በርከት ያሉ እንደ ማግኒዚየም ፣ ፓታሲየም ፣አይረን፣ ዚንክ፣ አዮዲንና ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኢ፣ኤፍን ይዛል።
1- የሀይል ምንጭ ነው:- ሙዝ በውስጡ ቫይታሚን፣ሚኒራል እና ካርቦሀይድሬት በመያዙ ሀይል ለማግኘት ይጠቅማል፡፡
2- ለምግብ መንሸራሸር ይጠቅማል:- ይህም የሚሆነው ሙዝ በውስጡ የቃጫ ባህሪ(ፋይበርነት) ስላለው ነው፡፡
3- የጨጓራ ህመምን ያስታግሳል:- ጨጓራ ጠንካራ ግድግዳ እንዲኖረው እና በጨጓራ ውስጥ ያለውን አሲድነት በመቀነስ ህመምን ያስታግሳል፡፡
4- የልብን ጤንነትን ይጠብቃል:- ሙዝ በፖታሲየም የበለፀገ ስለሆነ ይህም ለልብ ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡
5- ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ አነስተኛ ቅባት እንደዚሁም ብዙ ፋይበር ሰለያዘ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
6- አኔሚያን ለማከም ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ በዛ ያለ የብረት ማእድን ስለያዘ ይህም የቀይ የደም ሴልን ማነስ ይከላከላል፡፡
7- ነብሰጡሮችን ከህመም ይታደጋል:- ነብሰጡር ሴቶችን የሚያጠቃ የጠዋት ህመም የሚባለውን ለማከም ይረዳል፡፡
8- የአይንን ጤና ያሻሽላል:- ሙዝ ቫይታሚን ኤን ስለያዘ የአይን በሽታን ይከላከላል፡፡
9- በወባ ትንኝ የተነደፈን ይፈውሳል:- የተነደፈበት ቦታ በሙዝ ልጣጭ በማሸት ከህመሙ ይፈውሳል፡፡
10. ጥርስን ያነጣል፦ በሙዝ ልጣጭ ጥርስዎን ሁልጊዜ ጥርስዎን ሲፍቁ ለአስደናቂ ፈገግታ ይኖርዎታል።
11. የተጎድ የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል፣ የፊት መሸብሸብ እና የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል።
12. ክንታሮትን ያድናል:- ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ስለሆነ ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው።
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
@ethio_mereja
987 views22:25