Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja — ETHIO-MEREJA®
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.05K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 277

2022-06-01 11:06:56
የዓለም ባንክ ግሩፕ ለኢትዮጵያ የ200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ ነው!!

የዓለም ባንክ ግሩፕ ኢትዮጵያ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር የነደፈቻቸውን ስትራቴጂካዊ ሀሳቦች ለማገዝ የ200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ከዓለም ባንክ ግሩፕ ዋሽንግተን ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የመንግሥት ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን አቅም በመገንባት፤ የሥራ ገበያው የሚፈልገውን በክህሎት የዳበረ የሰው ኃይል በማፍራት ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተነደፈው ስትራቴጂካዊ ሐሳቦች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በማኅበራዊ ትሥሥር ገጸቸው ባሰፈሩት መልእክት ገልጸዋል።

በዚህም “ባንኩ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ ተስማምተናል” ብለዋል።

ሚኒስትሯ የዓለም ባንክ በተለያዩ ዘርፎች እያደረገ ላለው እገዛ በተለይም የፕሮግራሙን ሐሳብ አዋጭነት ገምግመው ለተግባራዊነቱ እገዛ ላደረጉት ሳፋ ኤሊ ኮጋሊ፣ ሁማ አሊ ዋሂድ እና ባልደረቦቻቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.2K viewsedited  08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 11:06:40
ቴሌግራም https://telegram.me/onlineshoppingce
አድራሻችን:- ቦሌ መድሐኔዓለም ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ፊትለፊት አለምነሽ ፕላዛ ሱቅ ቁጥር 05

+251941661030
13.6K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 11:06:34
በነጻ ተጨማሪ የሕክምና ምክርን ከእኛ ያግኙ

አቺባደም ሆስፒታል

ትክክለኛውን ምርመራ ለማድረግ ወይም ተገቢውን የሕክምና አማራጮችን ለመለየት ከፈለጉ ተጨማሪ የሐኪሞች አስተያየትና ምክርን ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በቱርክ የሚገኘው አቺባደም የጤና ክብካቤ ቡድን ይህንን አገልግሎት በነጻ ይሰጣል። የህክምና መረጃዎን በማቅረብ ከአለማችንን የታወቁ የህክምና ባለሙያዎችን አስተያየትና ምክር ማግኘት ይችላሉ።

ለተከታታይ ጠቃሚ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/acibadem_ethiopia ይቀላቀሉ፡፡
14.5K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 23:21:56
የኑሮ ወድነቱ ወዴት እየሄደ ነው?

"ሰሚ የሌለው ህዝብ - ጠያቂ ያጣው የኑሮ ውድነት "

በእውነቱ ህዝቡ ጠያቂም፣ ሰሚም ነው ያጣው። በዚህ ከባድ በማይገልፀው የኑሮ ውድነት ምክንያት የኢትዮጵያ ህዝብ ከማማረርም አልፎ በሁሉም ነገር ተስፋ እየቆረጠ እንደሆነ ግልፅ ነው። በእውነቱ አብዛኛው ህዝብ ኑሮውን በፈጣሪ ቸርነት(በፀጋው) እየገፋ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። መሰረታዊ ከሚባሉት (ልብስ፣ መኖሪያ ቤትና ምግብን) ጨምሮ ሁሉም አገልግሎቶች እና እቃዎች በከባድ ሁኔታ ከመወደዳቸው የተነሳ ህዝቡ ስጋት ውስጥ ገብቷል። ምን ውስጥ ኖሬ፣ ምን በልቼ አድራለሁ የሚለው የብዙዎች ጭንቀት እየሆነ መምጣቱን ካለው ሁኔታ ለመረዳት አይከብድም።

በተለይ የመንግስት ሰራተኞች፣ በቀንስራ የሚተዳደሩ፣ እንዲሁም ገና በስራ ፍለጋ ያሉትም ጨምሮ አብዛኛው ህዝብ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ችግር ውስጥ ገብቷል።የሚገኘው ገቢ ለቤት ኪራይና ለቀለብ በማይችልበት ሁኔታ ላይ ይገኛል። የእቃዎቹ መወደድ፣ የዘይትና ምግብ ነክ ነገሮች መናር፣ የታሪፍ መጨመር፣ የኪራይ ዋጋ መጨመርና ወዘተ...ህዝቡን ተስፋ እያሰቆረጠ ሲሆን ቀጣዩ ጊዜ ደግሞ በጣም ያስፈራል።

በጦርነቱ፣ በድርቁ፣ በውጪ ተፅእኖው፣ በተለያዩ ሀገረዊ ችግሮችና መንግስት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ባለመስጠቱ የኑሮው ውድነቱ ቅጥ ያጣ፣ መቆሚያ የሌለውና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

በይበልጥ የዚህ ገፈት ቀማሽ ደግሞ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ናቸው። ይህ ጠያቂ የሌለውና ሰሚ ያጣ ህዝብ ምንም ቢያደርግ አይፈረድበትም፣ መንግስት ይህንን አንገብጋቢና መልስ የሚያሻው ጥያቄ እያለ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት በሜጋ ፕሮጀክትና በአዲስ ፓላስ ግንባታ መወጠሩ ምን ቢታሰብ ነው ያሰኛል።

እናንተስ ምን ትላላችሁ? ፃፉልን።

ህዝብ ሰሚም፣ጠያቂም ይፈልጋል።( አንተነህ)
@ethio_mereja
3.0K viewsedited  20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 19:59:05
የ«ሀገር ጉዳይ ያሳስበናል» ያሉ ሦስት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ሥርዓት አልበኘነት የሕጋዊነት ያህል ነግሷል በማለት የጋራ መግለጫ አወጡ።

መግለጫውን ያወጡት፦ እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ናቸው።

ፓርቲዎቹ «አገር በሕግና በሥርዓት እንጂ በእፈና አትመራም» በሚል ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ የችግሮች ሁሉ ምንጭ የሆነው የጎሳና ማንነት አደረጃጀት አለመስተካከሉ እና ጥያቄው መልስ አለማግኘቱ አገር የጥቂት ቡድኖች ሀብት ወደ መምሰል እንድትጓዝ እያደረገ ነው ብለዋል። ፓርቲዎቹ ኢትዮጵያ በምጣኔ ሀብት በኩል የገጠማት ምስልቅል በፖለቲካውና በፀጥታው ዘርፍ ከገጠማት የባሰ እንጂ የተሻለ አይደለም ሲሉ የዋጋ ግሽበትን ለአብነት በመጥቀስ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የፓርቲዎቹ የጋራ መግልጫ «አዲስ አበባ ላይ እየተሠራ ያለው ደባ እና ከልክ ያለፈ ጠቅላይነት ተው ባይ አጥቶና መረን ለቆ የነገ አገር ተረካቢ ተማሪዎች ላይ አዲስ ማንነት ለመጫን በሚደረግ መፍጨርጨር ትምህርት ቤቶች ተረጋግተው የሚጠበቅባቸውን የመማር ማስተማር ሂደት መተግበር ወደማይችሉበት ኹኔታ እየገፋ ይገኛል» ብለዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ጦርነት አማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎችን አውድሟል ያሉት ሦስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢትዮጵያንም አክስሯል ሲሉ ገልፀዋል።

ፓርቲዎቹ «መንግሥት ማኅበረሰብን በሃይማኖት፣ በወንዝና በቡድን እየከፋፈለ ለመምታትና ለማፈን የሚያደርገውን ጥረት እንዲያቆም» በማለትም ክስና አቤቱታን በአንድ አሰምተዋል። ሕግ በማስከበር ሰበብ የታፈኑ ያሏቸው ንፁሃን ጋዜጠኞች፣ ማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የፀጥታ ተቋማት አባላት፣ የፓርቲ አመራሮች እና ሌሎችም እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።    

@ethio_mereja
10.8K viewsedited  16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 18:30:09
"አሜሪካ መምህራንን መሳሪያ ታስታጥቅ" ዶናልድ ትራምፕ


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሃገራቸው መምህራንን እንድታስታጥቅ ጠየቁ፡፡

ትራምፕ በቴክሳስ የተፈጸመውን ሰሞነኛ ግድያ በተመለከተ ብሔራዊ የጦር መሳሪያዎች ማህበር (NRA) ባካሄደው ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸው ከቤተሰብ ጋር የተያያዙ ችግሮች እና የአእምሮ ሕመምን ተደጋግመው በትምህርት ቤቶች ለተፈጸሙ ድንገተኛ ለግድያዎች ምክንያት አድርገው አስቀምጠዋል፡፡

በእርሳቸው የፕሬዝዳንትነት ዘመን እንዲህ ዐይነቱን ችግር ለመቅረፍ ብዙ መስራታቸውን በመጠቆምም የተካቸውን አዲሱን የባይደን አስተዳደር ወቅሰዋል፡፡ አስተዳደሩ እንዲህ ዐይነቶቹን መሰል ችግሮች ለማስቆም መምህራንን እንዲያስታጥቅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

"ለዩክሬን የምንሰጠው 40 ቢሊዮን ዶላር ካለን በቤታችን የራሳችንን ዜጎች ደህንነት ለመጠበቅ ከዚህም በላይ ማውጣት አለብን"ም ነው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ያሉት። "የታጠቀን መጥፎ ሰው ማስቆም የሚችለው የታጠቀ ጥሩ ሰው ብቻ ነው" ሲሉም ተናግረዋል የ79 ዓመቱ አዛውንት፡፡

ትምህርት ቤቶች ዒላማ ውስጥ ሊገቡ በማይችሉበት ሁኔታ መገንባት እንዳለባቸውም በማሳሰብም ጦር መሳሪያዎች ከትምህርት ቤቶች እንዲርቁ ጠይቀዋል፡፡ከሰሞኑ በቴክሳስ ኡቫልዴ ከተማ በሚገኝ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ሁለት መምህራንን ጨምሮ 20 ገደማ ህጻናት ተማሪዎች መገደላቸው ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎቻችንን በፌስቡክ ይመልከቱ Open
T.me/ethio_mereja
12.4K viewsedited  15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 18:10:27
ኦባሳንጆ በመቀሌ ከህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ጋር እንደተወያዩ ተሰምቷል!!

የአፍሪካ ህብረት ተወካዩ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ መቀሌ እንደነበሩ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ አስታውቀዋል።

ቃል አቀባዩ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ኦባሳንጆን ተቀብለው ማነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡“በቀጠናዊ ጉዳዮች” ላይ መምከራቸውንም ገልጸዋል ቃል አቀባዩ፡፡

ሆኖም ”ቀጣናዊ” የተባለው ጉዳይ ምን እንደሆነ አቶ ጌታቸው በግልጽ አላስቀመጡም። የተወያዩባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች እንዳሉም አልገለጹም፡፡ የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት የመቀሌ ጉዞ በተመለከተ የፌዴራል መንግስቱ የሰጠው መግለጫም ሆነ ያለው ነገር የለም፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.8K viewsedited  15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 18:10:21
ቴሌግራም https://telegram.me/onlineshoppingce
አድራሻችን:- ቦሌ መድሐኔዓለም ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ፊትለፊት አለምነሽ ፕላዛ ሱቅ ቁጥር 05

+251941661030
11.2K views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 16:17:32
በወላይታ ዞን በገሱባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሁለት ጥርስ ያበቀለ ሕፃን መወለዱን ሆስፒታሉ አስታውቋል፡፡

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ፀጋዬ እንድሪያስ እንደገለጹት  ÷ ትናንት ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ የተወለደ  ሲሆን  ይህ ክስተትም ከሚወለዱ 2 ሺህ ወይም 3 ሺህ ሕፃናት  በአንዱ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

ይህም ክስተት በህክምና አጠራሩ የሕፃናት የወሊድ ጊዜ ጥርስ (Natal teeth) ተብሎ እንደሚጠራም የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ መናገራቸውን ከገሱባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዶክተሩ አያይዘውም  ሁለት ጥርስ በማብቀል የተወለደው ሕፃን ምንም ሳይቸገር ጡት እየጠባ መሆኑን እና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
13.4K viewsedited  13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 15:53:28
ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል!
የሃገሪቱ ትልቁ ሪፈራል ሆስፒታል የሆነው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ህንፃ ግንባታ ከ4 ና 5 አመት በፊት በከፍተኛ ፍጥነት ሲሰራ ቆይቶ መገባደጃው ሲደርስ ስራው ከቆመ አመታት ተቆጠሩ።

ከሁለት ወር በፊት "ለአዲስ ኮንትራክተር ተሰጥቷል" ተብሎ ነበር። የሚንቀሳቀስ ነገር ግን የለም። ህዝቡ መሬት ላይ፣ ወንበር ላይና አስቀያሚ "ግዜያዊ" አዳራሽ ውስጥ "እየታከመ" ነው።አሁን ያለው ድንገተኛ ክፍል እንኳን ለሰው ልጅ ለአራዊት እንኳን የማይመጥን የሚያሳፍር ቦታ ነው!

ህክምና ለመስጠት የሚችል በቂ ባለሙያ እያለ፣ ሊያልቅ የደረሰ ህንፃ ባዶውን ነጭ ለብሶ ተገትሮ እያለ እንዴት የሚጨርስ የመንግስት ኃላፊ ይጠፋል?

የመንግስት የፓርክና መሰል "ሜጋ ፕሮጀክቶች" አፈፃፀም "A" የሚሰጠው ሲሆን የሆስፒታልና ተያያዥ ፕሮጀክቶች አፈፃፀሙ ደግሞ "F" እንኳ የሚበዛበት ነው

ዶ/ር ፈርዖን ጌታቸዉ ፤ የቀዶ ህክምና ሐኪም
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
13.3K viewsedited  12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ