Get Mystery Box with random crypto!

የኑሮ ወድነቱ ወዴት እየሄደ ነው? 'ሰሚ የሌለው ህዝብ - ጠያቂ ያጣው የኑሮ ውድነት ' በእውነ | ETHIO-MEREJA®

የኑሮ ወድነቱ ወዴት እየሄደ ነው?

"ሰሚ የሌለው ህዝብ - ጠያቂ ያጣው የኑሮ ውድነት "

በእውነቱ ህዝቡ ጠያቂም፣ ሰሚም ነው ያጣው። በዚህ ከባድ በማይገልፀው የኑሮ ውድነት ምክንያት የኢትዮጵያ ህዝብ ከማማረርም አልፎ በሁሉም ነገር ተስፋ እየቆረጠ እንደሆነ ግልፅ ነው። በእውነቱ አብዛኛው ህዝብ ኑሮውን በፈጣሪ ቸርነት(በፀጋው) እየገፋ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። መሰረታዊ ከሚባሉት (ልብስ፣ መኖሪያ ቤትና ምግብን) ጨምሮ ሁሉም አገልግሎቶች እና እቃዎች በከባድ ሁኔታ ከመወደዳቸው የተነሳ ህዝቡ ስጋት ውስጥ ገብቷል። ምን ውስጥ ኖሬ፣ ምን በልቼ አድራለሁ የሚለው የብዙዎች ጭንቀት እየሆነ መምጣቱን ካለው ሁኔታ ለመረዳት አይከብድም።

በተለይ የመንግስት ሰራተኞች፣ በቀንስራ የሚተዳደሩ፣ እንዲሁም ገና በስራ ፍለጋ ያሉትም ጨምሮ አብዛኛው ህዝብ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ችግር ውስጥ ገብቷል።የሚገኘው ገቢ ለቤት ኪራይና ለቀለብ በማይችልበት ሁኔታ ላይ ይገኛል። የእቃዎቹ መወደድ፣ የዘይትና ምግብ ነክ ነገሮች መናር፣ የታሪፍ መጨመር፣ የኪራይ ዋጋ መጨመርና ወዘተ...ህዝቡን ተስፋ እያሰቆረጠ ሲሆን ቀጣዩ ጊዜ ደግሞ በጣም ያስፈራል።

በጦርነቱ፣ በድርቁ፣ በውጪ ተፅእኖው፣ በተለያዩ ሀገረዊ ችግሮችና መንግስት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ባለመስጠቱ የኑሮው ውድነቱ ቅጥ ያጣ፣ መቆሚያ የሌለውና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

በይበልጥ የዚህ ገፈት ቀማሽ ደግሞ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ናቸው። ይህ ጠያቂ የሌለውና ሰሚ ያጣ ህዝብ ምንም ቢያደርግ አይፈረድበትም፣ መንግስት ይህንን አንገብጋቢና መልስ የሚያሻው ጥያቄ እያለ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት በሜጋ ፕሮጀክትና በአዲስ ፓላስ ግንባታ መወጠሩ ምን ቢታሰብ ነው ያሰኛል።

እናንተስ ምን ትላላችሁ? ፃፉልን።

ህዝብ ሰሚም፣ጠያቂም ይፈልጋል።( አንተነህ)
@ethio_mereja