Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja — ETHIO-MEREJA®
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.05K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 276

2022-06-02 10:25:36
ቴሌግራም https://telegram.me/onlineshoppingce
አድራሻችን:- ቦሌ መድሐኔዓለም ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ፊትለፊት አለምነሽ ፕላዛ ሱቅ ቁጥር 05

+251941661030
14.9K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 10:25:27
በነጻ ተጨማሪ የሕክምና ምክርን ከእኛ ያግኙ

አቺባደም ሆስፒታል

ትክክለኛውን ምርመራ ለማድረግ ወይም ተገቢውን የሕክምና አማራጮችን ለመለየት ከፈለጉ ተጨማሪ የሐኪሞች አስተያየትና ምክርን ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በቱርክ የሚገኘው አቺባደም የጤና ክብካቤ ቡድን ይህንን አገልግሎት በነጻ ይሰጣል። የህክምና መረጃዎን በማቅረብ ከአለማችንን የታወቁ የህክምና ባለሙያዎችን አስተያየትና ምክር ማግኘት ይችላሉ።

ለተከታታይ ጠቃሚ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/acibadem_ethiopia ይቀላቀሉ፡፡
15.4K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 22:46:22
ዩክሬን በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ወታደሮቿን እያጣች መሆኑን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አስታወቁ!!

ዩክሬን በየቀኑ ከ60 እስከ 100 የሚደርሱ ወታደሮቿን እያጣች መሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ አስታወቁ። በምስራቅ ዩክሬን ያለው ሁኔታ “በጣም አደገኛ ነው” ሲሉ የገለጹት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ፤ በየቀኑ ቁጥራቸው 500 የሚደርሱ ሰዎች እቆሰሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ ኒውስ ማክስ ከተባለ የመገናኛ ብዙሃን ጋር በኪቭ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በዩክሬን ያለው አጠቃላይ ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ነው ብለዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
4.7K viewsedited  19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 20:11:34
ከዛሬ ጀምሮ የሲሚንቶ ግብዓትና ምርት ስርጭትን በሚያስተጓጉሉ ህገ-ወጦች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዱና የመዓድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ታከለ ኡማ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዱ በመግለጫቸው፤ በክልሉ በሲሚንቶ ምርት ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የሚያስችል እርምጃ ክልሉ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚወስድ አስታውቀዋል።

በተለይም በአንዳንድ አካባቢዎች በሚገኙ ያልተገባ ክፍያ በመጠየቅ የግብዓትና ምርት ስርጭት ላይ እንቅፋት የሆኑ ኬላዎችን በማንሳት ግብዓቱ በቀጥታ ወደ ፋብሪካዎች የሚደርስበት አሰራር ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

አክለውም ምርቱ ከፋብሪካዎች በ400 ብር እና በ500 ብር የሚወጣ ቢሆንም በርካታ ደላሎች በመሀል የምርቱን ዋጋ እስከ 1 ሺሕ ብር ከፍ እንዲል ማድረጋቸው በመግለጫው ተነስቷል። በመሆኑም ክፍተቶችን በመፈተሽ ህጋዊ ማኅበራትን በማደራጀት የምርት ስርጭቱ በቀጥታ ወደ ተጠቃሚው የሚደርስበትን አሰራር ተዘርግቷል ብለዋል።

ከአምራች እንደስትሪዎች ጋር በተገናኘ የሚነሱ የፀጥታና የግብዓት ችግሮች ለመቅረፍ ክልሉ ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑና ችግሩንም ለመቅረፍ ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.4K viewsedited  17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 19:57:44
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+P7ctetopPExiY2Rk
10.8K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 19:29:05 በሰባት የአፍሪካ አገራት ከ1 ሺህ 400 በላይ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

በቫይረሰ መያዛቸው ሙሉ በሙሉ የተረጋገጡት ግን 44ቱ ብቻ ናቸው። ቫይረሱ ካሁን ቀደምም የተለመደባቸው እና አሁንም የተገኘባቸው አገሮች፣ ካሚሮን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ፣ ላይቤሪያ፣ ናይጀሪያ፣ ኮንጎ እና ሴራሊዮን ናቸው። ሆኖም ከእነዚህ አገራት ውጭ እስካሁን ቫይረሱን ሪፖርት ያደረገ የአፍሪካ አገር እንደሌለ ድርጅቱ አመልክቷል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.3K viewsedited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 18:26:34 ፌደራል ፖሊስ ህገ-ወጥ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ!!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ህገ-ወጥ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የፌደራል ፖሊስ በመግለጫው እንዳስታወቀው፡- ፖሊስ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ እንዲሁም በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 (አንድ መቶ አስራ አንድ) ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል ብሏል።

የፌደራል ፖሊስ ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ህገ-ወጥ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃንን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ፡-

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/ 2013 መሰረት ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ እንዲሁም በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 (አንድ መቶ አስራ አንድ) ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል።

ከዚህ ውስጥ በጣም ወጣ ያሉ ብሄርን ከብሄር ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱትን ለይቶ 10 (አስር) ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው ይገኛል።

እነዚህ ግለሰቦች የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን በመቅረጽ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት እንዳይረጋጋ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት በብሄር እና በሀይማኖት መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ሲያደርጉ የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል።

ተቋሙ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ክትትል ግለሰቦቹ ምንም አይነት ህጋዊ ፍቃድ የሌላቸውና በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ያልተመዘገቡ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ባሰባሰበው መረጃ ማረጋገጥ ችሏል። ግለሰቦቹ የሚዲያ ተከታዮቻቸውን በመጠቀም ሐሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን የሚያሰራጩት በክፍያ እንደሆነም በምርመራ ደርሶበታል።

በየትኛውም ሚዲያ ተጠቅመው መረጃን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉ ግለሰቦች የሀገሪቱን ህግና ሥርዓት አክብረው መንቀሳቀስ እና ህጋዊ መስመር በመከተል በተጠያቂነት መንፈስ መስራት ይኖርባቸዋል። ፖሊስም ህግን አክብረው በማይሰሩት ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማሳሰብ ይወዳል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ያገኛውን መረጃ ሁሉ ከመጠቀም በመቆጠብ በጥንቃቄ መርምሮ ማየትና ማገናዘብ እንዳለበት እያሳሰበ በህግ-ወጥ መንገድ በበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት አጀንዳ ቀርፀው በሀይማኖት፣ በብሄር ህብረተሰቡን ለማጋጨት የሚሰሩ አከላትን በማጋለጥና ለህግ አሳልፎ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ለህዝብ ሲገለጽ እንደነበረው ከሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመረውን የህግ ማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
12.2K viewsedited  15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 17:58:04
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው እለት ባካሔደው ምርጫ፦
*ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
*ብፁዕ አቡነ ጴጦሮስን የቅዱስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ ሾሟል።

በዛሬው ዕለት ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓም በተካሄደው ምርጫ አርባ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ከተወዳደሩት፦

፩ኛ. ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፳፮ ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
፪ኛ. ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦንስ ፲፪
፫ኛ. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፯
ድምጽ አግኝተዋል፡፡

ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በእጩነት ከቀረቡት መካከል
፩ኛ. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፳ ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
፪ኛ. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ፲፯
፫ኛ. ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ፰ ድምጽ ማግኘታቸውን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ለEotc tv ገልጸዋል። ለሁለቱም ብፁዐን አባቶች መልካም የሥራ ጊዜ እንመኛለን።

ምንጭ ፣ EOTC TV
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.9K viewsedited  14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 17:52:56
አሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ለአፍሪካ ቀንድ አገራት አዲሱ ልዩ መልዕክተኛዋ አድርጎ መሾሟን አስታውቃለች።

ይህንን ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ይፋ ያደረጉት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ናቸው። ማይክ ሐመር ላለፉት ስድስት ወራት በቀጠናው የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድን ይተካሉ። አሜሪካ ከዓመት በፊት ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሾመች ወዲህ አምባሳደር ማይክ ከአምባሳደር ፉልትማን እና ከአምባሳደር ሳተርፊልድ ቀጥለው ሦስተኛው ልዩ መልዕክተኛ ይሆናሉ። ተሰናባቹ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በአሜሪካው ራይስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የቤከር ፐብሊክ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.8K viewsedited  14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 11:54:03
በአማራ ክልል ተያዙ ከተባሉት ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ውስጥ የተወሰኑት እገታና አግባብ የሌለው እስር መሆኑን ኢሰመጉ ገለፀ!!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በአማራ ክልል በህግ ማስከበር ስም ከታሰሩት ከ4 ሺህ 500 በላይ ተጠርጣሪዎች ውስጥ የተወሰኑት በህግ አግባብ ያልተያዙ ናቸው አለ።

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከግንቦት 2014 ዓ.ም ጀምሮ መንግስት ህግ ማስከበር ዘመቻ በሚል ከ4 ሺህ 500 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን መግለጹ የሚታወስ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ኢሰመጉ ባሰባሰባቸው መረጃዎች በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉ እስሮች ተገቢውን የህግ ስነስርአት ያልተከተሉ እና እገታም የታከለባቸው መሆናቸውን መረዳቱን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በዚህ ሂደት በተፈጠሩ ግጭቶች እና በተወሰዱ እርምጃዎች በክልሉ በሚገኙ አካባቢዎች የ13 አመት ታዳጊን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመት፣ እስራት እና እገታ መፈጸሙን ኢሰመጉ ከአካባቢዎቹ ባሰባሰባቸው መረጃዎች መረዳቱንም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ በጋዜጠኞች፣በተፎካካሪ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እና በማህበረሰብ አንቂዎች ላይ ህገወጥ እስር እና እገታ እየተፈጸመ በመሆኑ መንግስት የእርምት እርምጃዎችን እንዲወስድ ሲጠይቅ መቆየቱን በማስታወስ አሁንም ሕገወጥ እርምጃው በመንግስት በኩል እንደቀጠለ ነው ብሏል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
16.7K viewsedited  08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ