Get Mystery Box with random crypto!

ሟችን የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተፈረደበት | ETHIO-MEREJA®

ሟችን የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተፈረደበት

ከሟች መኖሪያ ቤት በመግባት አፏን በጨርቅ ጠቅጥቆ፣ አንገቷን አንቆ በመያዝ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተፈረደበት

አላዩ ሞገስ ደሳለኝ የተባለ ተከሳሽ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 1፡30 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሽሮ ሜዳ አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት አካባቢ የ14 ዓመት የሆነችውን የግል ተበዳይ የምትኖርበት መኖሪያ ቤት በመግባት በጥፊ በመምታት፣ እንዳትጮህ አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቅ እና አንገቷን በሁለት እጁ አንቆ በመያዝ በኃይል የግብረ-ስጋ ግንኙነት የፈጸመባትና አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቁ እና አንገቷን በማነቁ ምክንያት ትንፋሽ አጥሯት ሕይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ/620/2/ሀ/ እና /3/ መሰረት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

(ፍትህ ሚኒስቴር)

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ