Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ለአፍሪካ ቀንድ አገራት አዲሱ ልዩ መልዕክተኛዋ አድርጎ መሾሟን አ | ETHIO-MEREJA®

አሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ለአፍሪካ ቀንድ አገራት አዲሱ ልዩ መልዕክተኛዋ አድርጎ መሾሟን አስታውቃለች።

ይህንን ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ይፋ ያደረጉት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ናቸው። ማይክ ሐመር ላለፉት ስድስት ወራት በቀጠናው የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድን ይተካሉ። አሜሪካ ከዓመት በፊት ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሾመች ወዲህ አምባሳደር ማይክ ከአምባሳደር ፉልትማን እና ከአምባሳደር ሳተርፊልድ ቀጥለው ሦስተኛው ልዩ መልዕክተኛ ይሆናሉ። ተሰናባቹ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በአሜሪካው ራይስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የቤከር ፐብሊክ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja