Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja — ETHIO-MEREJA®
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.05K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 275

2022-06-03 11:06:43
ቴሌግራም https://telegram.me/onlineshoppingce
አድራሻችን:- ቦሌ መድሐኔዓለም ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ፊትለፊት አለምነሽ ፕላዛ ሱቅ ቁጥር 05

+251941661030 / +251943190237
14.3K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 00:24:26
#ጤናመረጃ

ፓፓያ ለጤናችን የሚሰጠን 10 አስደናቂ ጥቅሞች!

1) ፓፓያ በሆድ ውስጥ የሚገኙ ትላትሎችን ለማጥፋት እና የጨጓራን አሲድነት ይቀንሳል፡፡

2) የፓፓያ ጁስ መጠጣትን ልምድ ማድረግ በአንጀት ውስጥ የሚፈጠርን ኢንፌክሽን እና ጎጂ ፈሳሽ ጠርጎ ያወጣል፡፡ የምግብ መፈጨት ሂደትን በማገዝ ብሎም የአንጀት ካንሰር የመከሰት እድልን ይቀንሳል፡፡

3) ዝቅተኛ የካሎሪ እና ከፍተኛ የጠቃሚ ምግብ ይዘት ስላለው በውፍረት መቀነስ ሂደት ውስጥ ላሉ ሰዎች አስተዋጽዖው የላቀ ነው፡፡

4) የጸረ ካንሰርና የሰውነት መቆጣትን የሚቀንስ ባህሪ አለው፡፡ ይህ የሰውነት መቆጣትን የሚቀንስ ባህሪ በማንኛውም የሰውነታችን መገጣጠሚያ ላይ ለሚደርስ ህመምና የአጥንት መሳሳት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

5) ፎረፎርን በመከላከል ጤናማ ጸጉር እንዲኖረን ስለሚያግዝ በተጨማሪ ከፓፓያ የተሰሩ የጸጉር ማስዋቢያ ምርቶችን መጠቀም ይመረጣል፡፡

6) ካለ እድሜ የሚመጣን የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል፡፡ ፓፓያን በቀጥታ ቆዳዎን በመቀባት ወይም በመመገብ የሚያምር ለስላሳ ቆዳን መጎናፀፍ ይቻላሉ፡፡ የተፈጨ ፓፓያ የተሰነጣጠቀ ተረከዝን ለማከም ይጠቅማል፡፡

7) የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል፣ የቆዳ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ ጥሬ ፓፓያ ፊትዎን ለ25 ደቂቃ በመቀባት ፊት ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ያበጡ ነጠብጣቦችን በቀላሉ ማስወገድ ይችላሉ፡፡

8) ፓፓያ አርጀኒን የተባለን ንጥረ ነገር ሲኖረው ይህም የወንድ ልጅን መሀንነት ይከላከላል፡፡

9) በቫይታሚን ኤ’ ሲ እና ኢ የበለጸገ በመሆኑ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ በተጨማሪም የልብ ህመምን ይከላከላል፡፡

10) ራሰ በራነትን ይከላከላል፣ የፀጉር እድገትንና ጥንካሬን ይጨምራል፡፡

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja
1.9K viewsedited  21:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 22:36:29
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጦርነት የገቡ አካላትን ለማስታረቅ ጠየቀች!!

ቤተ ክርስቲያኒቷ ከግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታካሂድ የነበረውን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማህበራዊና መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቃለች፡፡ የጉባኤውን መጠናቀቅ ተከትሎም ቤተክርስቲያኒቷ ውሳኔዎቿን የተመለከተ መግለጫን አውጥታለች፡፡

በመግለጫው በኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ ያሉ ወገኖች ወደ ሰላምና እርቅ እንዲመጡ ማስታረቅ እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡

ምልዓተ ጉባኤው በቀጣይ ጦርነትና የእርስ በርስ ግጭት ተወግዶ አጠቃላይ ሰላም በሚሰፍንበት መልኩ ተነጋግሮ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት እንዲቻል፣ የአስታራቂነት ሚናዋን መጫወት እንድትችል ለማድረግ ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ አቅርቤያለሁ ብላለች፡፡

እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናንና በኢትዮጵያ እንደ ሀገር የተከሰተውን የሰላም እጦት ተከትሎ የደረሰው ሕልፈተ ሕይወት፣ የካህናትና የምእመናን ሞትና የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል ላይ ጉባኤው መክሮ ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እንዲቀርብ ተደርጓል፣ ቤተክርስቲያኒቷ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም ጥሪ አቅርባለች፡፡

በበዓል ማክበሪያ ቦታዎች መነጠቅ ዙሪያ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ፣ በቀጣይም በመንግሥት በኩል አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላት ቤተክርስቲያኒቱ መጠየቋንም ነው የገለጸችው፡፡

በተጨማሪም እስካሁን በቤተክርስቲያን ላይ ደረሰ የተባለው ችግር በአይነትና በቁጥር ተለይቶ ለሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል መንግሥት አካላት ቀርቧልም ተብሏል፡፡እንዲሁም ቤተክርስቲያኗ በምልዓተ ጉባኤው ላይ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት የሚሰጥ የሕክምና ማዕከል እንዲቋቋም ስለመወሰኗ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡(ሼር)

@ethio_mereja
4.8K viewsedited  19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 20:58:01
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እየተበራከተ የመጣው የጋዜጠኞች እስራት እና እንግልት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ረቡዕ ግንቦት 24 ቀን፣ መግለጫ አውጥተዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 18 ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። መንግስት በቁጥጥር ስር ያረደጋቸው ጋዜጠኞች አንዳንዶቹ  ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም አሁንም ፍርድ ቤት ያልቀረቡና የታሰሩበት ቦታ የማይታወቁ ጋዜጠኞች ስለመኖራቸው ምክር ቤቱን አሳስቦታል ብለዋል ጋዜጠኞች  ከሕግ ውጭ  ከመያዛቸው፤ ባሻገር  ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ክስ ሳይመሰረትባቸ ታስረው መቆየታቸው፣ ያሉበትን መደበቅ እና በቤተሰብና የሕግ ባለሞያ እንዳያገኙ  መከልክል የመገናኛ ብዙኀን አዋጁን የሚፃረር ተግባር ነው ተብሎዋል።  

ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከመገናኛ ብዙኃን ሥራቸው ጋር በተያያዘ ከሆነ ክሱም ሊቀርብባቸው የሚገባው በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ መሠረት መሆን ይኖርበታል ብለዋል አቶ ታምራት ኃይሉ። የኢትዪጵያ መገናኛ  ብዙኃን ሥራ አስፈፃሚ በየግዜው የሚታየው የጋዜጠኞች እስራት እና እንግልት የሕግ ከለላ አለማግኘት በሀገራችን ሀሳብን በነፃነት የመገፅ መብትን ጥያቂ ውስጥ ከመክተቱም ባሻገር  በሞያው ላይ ያሳደረውን ተፀኖ ክረፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።    
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja
8.8K viewsedited  17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 20:45:07
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+P7ctetopPExiY2Rk
8.8K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 16:59:28
በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ያለውን እምቅ አቅም እና በመከናወን ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት መገምገማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

በጉብኝቱ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ናቸው።
T.me/ethio_mereja
13.9K viewsedited  13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 15:05:27
የቀድሞ የሜቴክ 4 አመራሮች ከተከሱሰበት የሙስና ወንጀል ክስ ከእስር እንዲፈቱ ታዘዘ።

አራቱ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ከተወሰነባቸው የእስራት ቅጣት በላይ በእስር በመቆየታቸውና የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ነው እንዲፈቱ የታዘዘው።

የቀድሞ የብረታብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ሀላፊዎች ሌ/ኮ ሰጠኝ ካሳይ፣ ኮነሬል ፍጹም አብርሃ፣ ሻለቃ ዋልታንጉስ ተስፋው እና ሻለቃ ክንድያ ግርማይ ሲሆኑ፤ የኃይል ትራንስፎርመር እና ባለ 3 ፌዝ ተርሚናል ኮኔክተር ለኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ለማቅረብ የተገባ ውል ላይ ያለጨረታ ግዢ ፈጽመዋል ተብለው በዓቃቢህግ በቀረበባቸው የሙስና ክስ በወንጀል ህግ 32 /1 ሀ እና የሙስና ወንጀል አዋጅ. ቁ 881/2007 አንቀጽ 91 ሀና ለ ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት በየደረጃው እንዲከላከሉ ብይን መሰጠቱ ይታወሳል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በዓቃቢህግ ያቀረበውን ማስረጃ በተገቢው አልተከላከላችሁም ሲል የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸው ነበር።

ተከሳሾቹ የቀረቡትን የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን ለአገር ያበረከቱት ሙያዊ አስተዋጾ እና የበጎ አድራጎት ሥራ በቅጣት ማቅለያ አስተያየት ተይዞላቸዋል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ ሻለቃ ክንድያ ግርማይን 2 ዓመት ከ9 ወር እስራትና 400 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ የወሰነ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ሦስት ተከሳሾች ደግሞ በ3 ዓመት እስራትና 500 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል። ይሁንና ተከሳሾቹ ከተወሰነባቸው የእስራት ጊዜ በላይ ከጥቅምት 30 ቀን 2011 ጀምሮ በእስር በማሳለፋቸውና የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ከእስር እንዲፈቱ ታዟል።( ታሪክ-አዱኛ)
T.me/ethio_mereja
14.6K viewsedited  12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 14:47:08
የፍትሕ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ዕለት ታስሮ በሚገኝበት ፖሊስ ጣቢያ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተሰምቷል!!

ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለዶቼ ቬለ እንደገለጸው የእስረኛ ቤተሰቦች ዛሬ ጠዋት ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በተገኙበት ተመስገንን ለመጠየቅ ሄዶ ሲደበደብ ተመልክቷል። «ተመስገን ከዚህ በፊት እስር ቤት በነበረው ቆይታ ጆሮው ላይ ጉዳት እንደደረሰበ ይታወቃል፤ በጠያቂዎች እና በእስረኞች መካከል ያለው 10 ሜትር ገደማ የሚሆነው ርቀት ከሰዎች ጫጫታ ጋር ተዳምሮ መደማመጥ ስላላስቻለው «ትንሽ ቀረብ ቢል ቢያዋራኝ» ብሎ በትህትና ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ሁለት ፖሊሶች ሌሎች እስረኞች እና ጠያቂዎች ባሉበት በቦክስ እና በእርግጫ መማታት ጀመሩ።» ሲልም ሁኔታው አስረድቷል።

ጋዜጠኛ ተመስገንን ደብዳቢዎቹ ፖሊሶች ይዘውት ወደ ሌላ ክፍል እንደወሰዱት እና እነሱንም ከአካባቢው እንዳባረሯቸውም ተናግሯል። ቆይቶም ቢሮ ውስጥ በቅርብ ርቀት ወንድሙን ገብቶ ማየት እንደቻለ የተናገረው ታሪኩ በዚህ ጊዜም ጋዜጠኛ ተመስገን ግራ ዓይኑ ስር አብጦ እና የለበሰው ቲሸርትም ተቀድዶ መመልከቱንም አክሎ ገልጿል። ጉዳዩን ለፖሊስ ጣቢያው ኃላፊዎች ለማስረዳት ሞክሮ እንደሁ የተጠየቀው ታሪኩ ፤ መሞከራቸውን አረጋግጦ ሆኖም የተደበደበ ወንድሙን ከማሳየበት በቀር አቤቱታቸውን ለማዳመጥ ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ተናግሯል።

ድብደባውንም ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ለጠበቃው ማሳወቃቸውንም አመልክቷል። ጋዜጠኛ ተመስገን ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓም አድ ዋ ድልድይ አጠገብ ከሚገኘው ቢሮው ድንገት ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል። ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ምርመራው ተጣርቶ እስኪያልቅ በሚል ለግንቦት 29 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።(ዶቼ-ቬለ)

T.me/ethio_mereja
13.6K views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 11:43:59
የግብጽ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ የአውሮፓ ህብረትን ድጋፍ ጠየቁ፡፡

ግብጽ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ትብብርን ስለማሳደግ ከህብረቱ ከፍተኛ ሃላፊ ጋር የተወያዩት ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ህብረቱ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ የሀገራቸውን አቋም እንዲደግፍ ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሲሲ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለግብጻውያን የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ለከፍተኛ ኮሚሽነሩ የተናገሩ ሲሆን፤ ሀገራቸው የአውሮፓ ህብረትን ድጋፍ እንደምትሻ ጠቁመዋል፡፡

ግብጽ ከዚህ ቀደም በነበሩ የሶስትዮሽ ድርድሮች ላይ ስታነሳው የነበረውን የአሳሪ ስምምነት አቋም እንዳዲስ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ኢትዮጵያ የሶስተኛውን ዙር ውሃ ሙሌት ከማከናወኗ በፊት ህጋዊ ያሉትን ስምምነት እንዲደረስ የአውሮፓ ህብረትን ድጋፍ መጠየቃቸውን አሻርቅ አላውሳት ዘግቧል፡፡

ከሰሞኑ የህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮን ጠቅሶ አል አረቢያ ባወጣው ዘገባ፤ ኢትዮጵያ የሶስተኛውን ዙር ውሃ ሙሌት በመጪዎቹ ነሃሴና መስከረም ወራት እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡በቅርቡ በፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ የሰጡት ም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የግድቡን የሶስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ህብረት ስር ለመቀጠል ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.8K viewsedited  08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 10:25:42
ጠ/ሚ አቢይ አህመድ፣ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የቀድሞ ጠሚ ሃይለማርያም ደሳለኝና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ኦሊሴጎል አባሳንጆ ባሌ ሮቤ ናቸው::

በጉብኝቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ናቸው። የልዑካን ቡድኑ በባሌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ሥራዎችን ተዘዋውሮ ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.8K viewsedited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ