Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጦርነት የገቡ አካላትን ለማስታረቅ ጠየቀች!! | ETHIO-MEREJA®

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጦርነት የገቡ አካላትን ለማስታረቅ ጠየቀች!!

ቤተ ክርስቲያኒቷ ከግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታካሂድ የነበረውን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማህበራዊና መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቃለች፡፡ የጉባኤውን መጠናቀቅ ተከትሎም ቤተክርስቲያኒቷ ውሳኔዎቿን የተመለከተ መግለጫን አውጥታለች፡፡

በመግለጫው በኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ ያሉ ወገኖች ወደ ሰላምና እርቅ እንዲመጡ ማስታረቅ እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡

ምልዓተ ጉባኤው በቀጣይ ጦርነትና የእርስ በርስ ግጭት ተወግዶ አጠቃላይ ሰላም በሚሰፍንበት መልኩ ተነጋግሮ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት እንዲቻል፣ የአስታራቂነት ሚናዋን መጫወት እንድትችል ለማድረግ ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ አቅርቤያለሁ ብላለች፡፡

እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናንና በኢትዮጵያ እንደ ሀገር የተከሰተውን የሰላም እጦት ተከትሎ የደረሰው ሕልፈተ ሕይወት፣ የካህናትና የምእመናን ሞትና የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል ላይ ጉባኤው መክሮ ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እንዲቀርብ ተደርጓል፣ ቤተክርስቲያኒቷ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም ጥሪ አቅርባለች፡፡

በበዓል ማክበሪያ ቦታዎች መነጠቅ ዙሪያ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ፣ በቀጣይም በመንግሥት በኩል አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላት ቤተክርስቲያኒቱ መጠየቋንም ነው የገለጸችው፡፡

በተጨማሪም እስካሁን በቤተክርስቲያን ላይ ደረሰ የተባለው ችግር በአይነትና በቁጥር ተለይቶ ለሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል መንግሥት አካላት ቀርቧልም ተብሏል፡፡እንዲሁም ቤተክርስቲያኗ በምልዓተ ጉባኤው ላይ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት የሚሰጥ የሕክምና ማዕከል እንዲቋቋም ስለመወሰኗ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡(ሼር)

@ethio_mereja