Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እየተበራከተ የመጣው የጋዜጠኞች እስራት እና እንግልት አሳሳ | ETHIO-MEREJA®

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እየተበራከተ የመጣው የጋዜጠኞች እስራት እና እንግልት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ረቡዕ ግንቦት 24 ቀን፣ መግለጫ አውጥተዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 18 ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። መንግስት በቁጥጥር ስር ያረደጋቸው ጋዜጠኞች አንዳንዶቹ  ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም አሁንም ፍርድ ቤት ያልቀረቡና የታሰሩበት ቦታ የማይታወቁ ጋዜጠኞች ስለመኖራቸው ምክር ቤቱን አሳስቦታል ብለዋል ጋዜጠኞች  ከሕግ ውጭ  ከመያዛቸው፤ ባሻገር  ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ክስ ሳይመሰረትባቸ ታስረው መቆየታቸው፣ ያሉበትን መደበቅ እና በቤተሰብና የሕግ ባለሞያ እንዳያገኙ  መከልክል የመገናኛ ብዙኀን አዋጁን የሚፃረር ተግባር ነው ተብሎዋል።  

ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከመገናኛ ብዙኃን ሥራቸው ጋር በተያያዘ ከሆነ ክሱም ሊቀርብባቸው የሚገባው በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ መሠረት መሆን ይኖርበታል ብለዋል አቶ ታምራት ኃይሉ። የኢትዪጵያ መገናኛ  ብዙኃን ሥራ አስፈፃሚ በየግዜው የሚታየው የጋዜጠኞች እስራት እና እንግልት የሕግ ከለላ አለማግኘት በሀገራችን ሀሳብን በነፃነት የመገፅ መብትን ጥያቂ ውስጥ ከመክተቱም ባሻገር  በሞያው ላይ ያሳደረውን ተፀኖ ክረፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።    
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja