Get Mystery Box with random crypto!

#ጤናመረጃ ፓፓያ ለጤናችን የሚሰጠን 10 አስደናቂ ጥቅሞች! 1) ፓፓያ በሆድ ውስጥ የሚገኙ ትላ | ETHIO-MEREJA®

#ጤናመረጃ

ፓፓያ ለጤናችን የሚሰጠን 10 አስደናቂ ጥቅሞች!

1) ፓፓያ በሆድ ውስጥ የሚገኙ ትላትሎችን ለማጥፋት እና የጨጓራን አሲድነት ይቀንሳል፡፡

2) የፓፓያ ጁስ መጠጣትን ልምድ ማድረግ በአንጀት ውስጥ የሚፈጠርን ኢንፌክሽን እና ጎጂ ፈሳሽ ጠርጎ ያወጣል፡፡ የምግብ መፈጨት ሂደትን በማገዝ ብሎም የአንጀት ካንሰር የመከሰት እድልን ይቀንሳል፡፡

3) ዝቅተኛ የካሎሪ እና ከፍተኛ የጠቃሚ ምግብ ይዘት ስላለው በውፍረት መቀነስ ሂደት ውስጥ ላሉ ሰዎች አስተዋጽዖው የላቀ ነው፡፡

4) የጸረ ካንሰርና የሰውነት መቆጣትን የሚቀንስ ባህሪ አለው፡፡ ይህ የሰውነት መቆጣትን የሚቀንስ ባህሪ በማንኛውም የሰውነታችን መገጣጠሚያ ላይ ለሚደርስ ህመምና የአጥንት መሳሳት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

5) ፎረፎርን በመከላከል ጤናማ ጸጉር እንዲኖረን ስለሚያግዝ በተጨማሪ ከፓፓያ የተሰሩ የጸጉር ማስዋቢያ ምርቶችን መጠቀም ይመረጣል፡፡

6) ካለ እድሜ የሚመጣን የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል፡፡ ፓፓያን በቀጥታ ቆዳዎን በመቀባት ወይም በመመገብ የሚያምር ለስላሳ ቆዳን መጎናፀፍ ይቻላሉ፡፡ የተፈጨ ፓፓያ የተሰነጣጠቀ ተረከዝን ለማከም ይጠቅማል፡፡

7) የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል፣ የቆዳ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ ጥሬ ፓፓያ ፊትዎን ለ25 ደቂቃ በመቀባት ፊት ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ያበጡ ነጠብጣቦችን በቀላሉ ማስወገድ ይችላሉ፡፡

8) ፓፓያ አርጀኒን የተባለን ንጥረ ነገር ሲኖረው ይህም የወንድ ልጅን መሀንነት ይከላከላል፡፡

9) በቫይታሚን ኤ’ ሲ እና ኢ የበለጸገ በመሆኑ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ በተጨማሪም የልብ ህመምን ይከላከላል፡፡

10) ራሰ በራነትን ይከላከላል፣ የፀጉር እድገትንና ጥንካሬን ይጨምራል፡፡

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja