Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ 963 የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴ | ETHIO-MEREJA®

ሩሲያ 963 የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ይፋ ባደረገው እና «ሙሉ» ባለው ስም ዝርዝር ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን እና የማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (CIA) ኃላፊ ዊልያም በርንስ ይገኙበታል።

ሩሲያ በአሜሪካዊያኑ ላይ ይህንን ርምጃ የወሰደችው የአሜሪካ መንግሥት ባህሪውን እንዲለውጥ እና "አዲስ የጂኦፖለቲካዊ እውነታዎችን" እንዲቀበል ግፊት ለማድረግ ነው ብላለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ አዲሱን የ40 ቢሊዮን ዶላር የዕርዳታ ድጋፍ ለዩክሬይን ፈርመዋል። የአሜሪካ ኮንግረስ ርዳታውን ካፀደቀ በኋላ የሚቀረው የፕሬዚዳንቱ ፊርማ ብቻ ነበር ።

ከድጋፉ ስድስት ቢሊዮኑ ዶላር የሚውለው ጥይት ለማይበሳቸው ተሽከርካሪዎች እና ለዩክሬን ጦር ኃይሎች የአየር መከላከያ ዘዴዎች ሲሆን ዘጠን ቢሊዮን ዶላር ደግሞ አስቀድሞ ወደ ዩክሬይን የጦር መሣሪያ ለላከው የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይል የተመደበ ነው ተብሏል። ከጦር መሣሪያ ድጋር ባሻገር ዩናይትድ ስቴትስ ለሰብአዊ ዕርዳታ የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ ለዩክሬን መመደባ ተገልጿል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ