Get Mystery Box with random crypto!

መንግስት፤ ህወሓት “ምርኮኞች”ን ለቅቄያለሁ የሚለው አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት ነው አለ!! | ETHIO-MEREJA®

መንግስት፤ ህወሓት “ምርኮኞች”ን ለቅቄያለሁ የሚለው አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት ነው አለ!!

የኢትዮጵያ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህወሓት ምርኮኛ ወታደሮችን ለቋል የሚለው ሀሰት ነው ሲል አስተባብሏል፡፡

ሰሞኑን ህወሓት በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ማርኬያቸዋለሁ ያላቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለቅቄያለሁ ማለቱን ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ይህ የህወሃት ድርጊት አለምአቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ የተደረገ “ሀሰተኛ ፕሮፖገንዳ” ነው ብሏል፡፡

“መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ እያደረገ ባለው ማጣራት በሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ናቸው ተብለው የተለቀቁት አብዛኞቹ ዜጎች የመከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ክልል ለቆ በወጣበት ወቅት በሽብር ቡድኑ ታግተው የቀሩ የሰራዊቱ ቤተሰብ አባላት መሆናቸው ታውቋል።” ከሰራዊት ቤተሰቦች በተጨማሪም ህወሃት በአፋር እና በአማራ ክልል በቆየባቸው ወቅት በግዳጅ ይዞ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽምባቸው የነበሩትን ሰዎች እና “ከልዩ ልዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ለስራ ትግራይ ክልል ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሲቪል ነዋሪዎችን” ምርኮኛ ማስመሰሉን መንግስት ገልጿል፡፡

መንግስት ህወሓት ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ “የተለያዩ ጸጥታ ሃይሎችን መለዮ በማልበስ በምርኮኛ ስም አሰልፏቸዋል” ብላል፡፡የህወሃት ድጋሚ ጦርነት ለመጀመር ያለውን ፍላጎት የሚሳይ ነው ያለው መግለጫው “በምርኮኛ ስም” ሰርጎ ገቦችን ለእኩይ አላማ ማደራጀቱን ደርሰንበታል ብሏል መንግስት፡፡(የመንግስት-ኮሙኒኬሽን)
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ