2022-05-21 00:40:44
#ጤናመረጃየልብ ድካም ምክንያቶችና መፍትሔዎቹ! ልብ ድካም ማለት ልብ ሙሉ በሙሉ ስራዋን ማቆም ሳይሆን በውጤታማነት በጤነኛ መንገድ ተግባሯን ማከናወን አለመቻል ማለት ነው፡፡
......
የልብ ድካም ሊያደርሱ የሚችሉ ምክንያቶች!1.የልብ ደም ቧንቧ መጥበብ፡- ስብ/ኮለስትሮል በደም ስር ውስጥ እየተከማቸ ሲመጣ የሚከሰት ነው።
2.የደም ግፊት፡- የልብ ጡንቻ በመወፈር በሂደት የልብ ግራ ክፍል እንዲሰፋ በማድረግ ልባችን ተግባሩን እንዳያከናውን ያደርገዋል፡፡
3.የልብ በር ችግር፡- ለአካላችን ደም ለማሰራጨት የሚረዳው የልብ በር ሲጎዳ ልብ ተግባሩን እንዳያከናውን ያደርጋል።
4.የልብ ጡንቻ ችግር፡- የልብ ጡንቻ በተለያዩ ኢንፌክሽኖች፤ አልኮል አብዝቶ በመጠጣትና የተለያዩ መድሀኒቶችን በመውሰድ ሊታመም ይችላል፡፡
5. በአፈጣጠር የልብ አካላት ትክክል ባለመሆኑ፡- የልብ አካላት አፈጣጠር ማለትም የልብ በር፣ የደም ቧንቧ፣ የጡንቻውና ሌሎችም
6. ሌሎች በሽታዎች እንደ የስኳር በሽታ፤ የታይሮይድን እጢ የሚያመርቱ ሆርሞኖች ብዛት፤
....
የልባችንን ጤና እንዴት እንጠብቅ?
• ትምባሆ/ሲጋራ አለማጨስ
• የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ፤ በተለይ በፍጥነት መራመድ፤ ዋና፤ ሩጫና ሌሎችንም ማድረግ፡፡
• ቁመታችንና ክብደታችን ካልተመጣጠነ በተገቢው መልኩ ለማመጣጠን ክብደትን መቀነስ፤
• አትክልትና ፍራፍሬን ማዘወተርን የምግብ ምርጫችን ማድረግ!
• የምንጠቀመውን የጨው መጠን መቀነስ፤ ጥሬ ስጋ፤ ጮማ፤ እንቁላልና ቅቤን በሚገባ መቀነስ፡፡
• የደም ግፊትና ስኳር በሽታ ካለብን በመከታተል መቆጣጠር መቻል የልብ ድካምን ለመከላከል ዋናዎቹ ናቸው፡፡
እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለሁሉም እንዲደርስ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ
1.3K viewsedited 21:40