Get Mystery Box with random crypto!

የከተማ አስተዳደሩ ሕንጻዎች ሊቀቡ የሚገባቸውን 13 የቀለም ዓይነቶች መለየቱን ይፋ አደረገ!! የ | ETHIO-MEREJA®

የከተማ አስተዳደሩ ሕንጻዎች ሊቀቡ የሚገባቸውን 13 የቀለም ዓይነቶች መለየቱን ይፋ አደረገ!!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋ ህንጻዎች ሊቀቡ ይገባቸውል ያላቸውን 13 የቀለም አይነቶችን መለየቱን ገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩ የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ ባወጣው ማብራሪያ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እንድትሆን እና ዓለም ዐቀፍ ደረጃን የሚመጥን ገፅታ እንዲኖራት ለማስቻል ከሚሠሩ ሥራዎች አንዱ የሕንጻዎችን ቀለምና ቁመት የሚወስን አሠራርን መተግባር መሆኑን አስታውቋል።

እስካሁን ባለው ሂደት የከተማዋ ሕንጻዎች ያለምንም ቁጥጥር ወጥነት በጎደለው መልኩ ሕንጻዎች ቀለም የሚቀቡ ሲሆን እየተቀቡ ያሉ ቀለማት የከተማዋን መልክ ዥንጉርጉር ከማድረጋቸውም በላይ የሚገነቡ ሕንጻዎች ንድፍ በዘፈቀደ በመሠራቱ የተነሳ የከተማዋ ገፅታ በእጅጉ ተጎድቶ እንደሚገኝ አስተዳደሩ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

ይህን ችግር መልክ ለማስያዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከብዙ ዓለም ዐቀፍ ከተሞች ተሞክሮ በመውሰድ ለከተማዋ የሚስማማ የሕንጻ ቀለማት ደረጃን አጥንቶ ለውይይት አቅርቧል፡፡

በውይይቱ የተሳተፉ በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች ሁኔታውን በተመለከተ ዝርዝር ጥናት በማድረግ ለከተማዋ የሚስማሙ 13 ዓይነት ቀለማት መለየታቸውን አስተዳደሩ ገልጿል።

በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ሁሉ ለከተማዋ በመለያነት ከተመረጡ 13 ቀለማት መካከል የሕንጻ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን ይህ አሠራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ መገባቱንም ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

የተመረጡት ቀለሞች የሚከተሉት ናቸው ከላይ በምስል መልኩ ከዜናው ጋር ተያይዞ ቀርቧል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ