Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ!! | ETHIO-MEREJA®

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ!!

በዞኑ በሚገኙ በአቦቴ እና በወረጃርሶ ወረዳዎች በስፋት በመንቀሳቀስ ህበረተሰቡን ሲዘርፉ እና ሲያሰቃዩ በነበሩት የሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ በመወሠዱ በአሁኑ ወቅት በአካባቢዎቹ አስተማማኝ ሰላም መስፈኑ ተገልጿል።

በዞኑ ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማስፈን በአካባቢው የተሰማሩት የጥምር ፀጥታ አካላት በሽብር ቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን የገለፁት የጥምር ፀጥታ አካላት አስተባበሪ እና በኮማንዶ ክፍለ ጦር የሬጅመንት ዋና አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ታሄል ሬድ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በተደረገው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ በርካታ አመርቂ ድሎች እየተመዘገቡ ይገኛሉ ብለዋል።

ዋና አዛዡ እንደገለጹት፥ እስከ አሁን በተደረጉ ዘመቻዎች እርምጃ የተወሰደባቸው 44፣ የተማረኩ 05፣ ሲሆን 18 የተለያዩ መሳሪያዎች ተማርከዋል፣ የሽብር ቡድኑ ሲጠቀምበት የነበረም 19 ኩንታል እህል በቁጥጥር ስር ውሏል።

በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን የሰጡት ደግሞ 233 መሆናቸውን የጥምር ፀጥታ አካላት አስተባበሪ እና በኮማንዶ ክፍለ ጦር የሬጅመንት ዋና አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ታሄል ሬድ ገልፀዋል።

ከአካባቢው ህብረተሰብ፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከአባገዳዎች ጋር በመሆን በተሰራው የተቀናጀ ትብብር የተገኘው ድል አበረታች ነው ያሉት ደግሞ የወረጃርሶ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አየለ መንግስቱ ናቸው።

ከህብረተሰቡ የተወከሉ የአካባቢው ሽማግሌዎች እና አባገዳዎችን ወደ ጫካ በመላክ ከታጣቂዎቹ ጋር በተደረገው ድርድር እና ውይይቶች በርካታ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች በየቀኑ በሰለማዊ መንገድ እጃቸውን በአካባቢው ለተሰማራው ለፀጥታ አካላት እየሰጡ እንደሚገኙ የገለፁት ዋና አስተዳደሪው በአሁኑ ወቅት በአከባቢው አንፃራዊ ሰላም መስፈን መቻሉን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ