Get Mystery Box with random crypto!

#ጤናመረጃ ጥቁር አዝሙድ ለጤናችን የሚሰጠን አስደናቂ ጥቅሞች በጥቁር አዝሙድ ውስጥ ለሰው ልጅ | ETHIO-MEREJA®

#ጤናመረጃ

ጥቁር አዝሙድ ለጤናችን የሚሰጠን አስደናቂ ጥቅሞች


በጥቁር አዝሙድ ውስጥ ለሰው ልጅ ጠቃሚ የሆኑ ከ100 በላይ የተለያዩ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች አሉ። እንደ ካልሲየም፣ ፖታሲየም፣ ብረት፣ ዚንክ፣ ማግኒዥየም፣ ሲኒየም፣ ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ቢ፣ ቫይታሚን ቢ2 ና ሲ የመሳሰሉት ፕሮቲኖች መገኛ ነው።

የአለርጂ በሽተኞች አሉታዊ ምልክቶችን ለመቀነስ የሚረዳ እንደ ፀረ-ሂስታሚን በውስጡ ይዟል።መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት ለማፅዳት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።

ለስኳር በሽታ የኢንሱሊን መጠንን ለመቆጣጠር፣ ኮሌስትሮልን፣ የሰውነት ዝውውርን ያሻሽላል እንዲሁም ጤናማ የጉበት ሥራን ያበረታታሉ።

ደረቅ ሳልን ለማስታገስ ከቡና ጋር ቀላቅሎ መጠጣት ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለው፣ የፊት መሸብሸብንና ቴታነስን ለመከላከል ጥቁር አዝሙድን ከሞቀ ውሃ ጋር ቀላቅሎ መጠቀም ይመከራል።

እንደ ሣል፣ ትኩሳት፣ አስም፣ የቆዳ ሽፍታ፣ እብጠትና የሆድ ድርቀትን ለማከም አገልግሎት ላይ ይውላል።

የፀጉር መሳሳት እና መላጣነትን ይከላከላል፣ የአይን ኢንፌክሽን፣ ህመም እና ደካማ እይታን ለመከላከል ዘይቱ ይጠቅማል።

በተበከለ ምግብ አማካኝነት የሚከሰትን ድንገተኛ ትውከትን ለማስቆም ይረዳል፣ የጥርስ ህመምን ለማስታገስ ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከሙቅ ውሃ ጋር ቀላቅሎ በተጎዳው ጥርስ ላይ በማፍሰስ ህመምን ማስታገስ ይቻላል።

የደም ግፊትን በጣም ይቀንሳል። ዘይቱ ጸረ-አልባሳት ባህሪዎች የደም ግፊትን እና ሌሎች የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎችን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል።

በማንኛውም የሰውነት ክፍል ላይ አደገኛ የሆኑ ዕጢዎች መፈጠርን ይከላከላል፣ የወር አበባ ፍሰት እና እንቅስቃሴን ያበረታታል።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
@ethio_mereja ኢትዮመረጃ