Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት የሚል ክስ ቀረበባት. የሮሃ ሚድያ መስራች የሆነች | ETHIO-MEREJA®

ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት የሚል ክስ ቀረበባት.

የሮሃ ሚድያ መስራች የሆነችው ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ላይ ፖሊስ ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት የሚል ክስ አቀረበባት። ሮሃ ሚድያ እንደዘገበው ጋዜጠኛዋ ዛሬ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርባለች። ፖሊስ ባቀረበባት ክስ ላይ መረጃ ለማሰባሰብ የ14 ቀን ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ጠበቃዎች በበኩላቸው ሰራች የተባለው ወንጀል ተፈፅሞ ቢሆን እንኳን ጉዳዩ ሊታይ የሚገባው በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ነው። በእስር እንድትቆይ ህጉ አይፈቅድም ሲሉ ተከራክረዋል። በተጨማሪም ጋዜጠኛዋ ከወራት በፊት ታስራ ማስረጃ ሊቀርብባት ባለመቻሉ ነፃ መደረጓን ገልፀው አሁንም “ሞጋች ጋዜጠኛ መሆኗ እንጂ የሰራችው ወንጀል የለም” በማለት አስረድተዋል።

ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ካደመጠ በኋላ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja