Get Mystery Box with random crypto!

22 ሰዎችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው የኔፓል አውሮፕላን ጠፋ!! ንብረትነቱ የግል አየርመንገድ የሆ | ETHIO-MEREJA®

22 ሰዎችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው የኔፓል አውሮፕላን ጠፋ!!

ንብረትነቱ የግል አየርመንገድ የሆነ አነስተኛ የመንገደኞች አውሮፕላን 22 ሰዎችን አሳፍሮ በመብረር ላይ ሳላ በተራራማዋ የኔፓል ቦታ የደረሰበት ጠፍቷል፡፡

ባለስልጣናት እንደተናገሩት የአካባቢው ሰዎች እሳት ማየታቸውን ወደገለጹበት ቦታ የፍለጋ ቡድን መሰማራቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የኔፓል ቴሌቪዥን በልያንኩ ኮህል አካባቢ ያሉ ሰዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው ቲቤትን በሚያዋስነው የሂማሊያ ተራራ ስር አርክራፍቷ በእሳት ስትያያዝ አይተዋል፡፡

ዲ ሃቪላንድ ካናዳ ዲኤች ሲ-6-300 ጠዊነ ኦተር ለ20 ደቂቃ በራራ የተነሳ ቢሆን ለማረፍ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ከመቆጣጠሪያ ጣቢያው ያለው ግንኙነት ተቋርጧል፡፡ ቁጥጥሩ የሚያደርገው የታራ ኤየር ኩባንያ ነበር፡፡

የታራ አየር ቃል አቀባይ የፍለጋ ቡድን ወደ ስፍራው መሰማራቱን ለሮይተርስ ገልጿል፡፡ የኔፓል ሲቪል አቬሽን ማለስልጣንም የፍለጋ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን አስታውቋል፡፡ አራት ህንዳውያን፤ሁለት ጀርመናውያንን እና 16 የኔፓል ዜጎችን አሳፍሮ ነበር ያለው አየርመንገዱ በረራው ከኔፓል ዋና ከተማ ከታማንዱ ዋና ከተማ በምስራቅ በኩል 125 ኪሜ ርቀት ወደምትገኘው የቱሪስት መዳረሻዋ ፖክሃራ ከተማ ነበር፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja