Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ለእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት የሚሆኑ ትራክተሮችን | ETHIO-MEREJA®

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ለእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት የሚሆኑ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረከበ።

በመርሀ ግብሩ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፤ የብልጽግና ፓርቲ አማራ ክልል ቅርንጫፍ ሀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ፤ የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሀይለማርያም ከፊያለው እና ሌሎች ከፍተኛ የክልል፣የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረክቧል።

በክልላችን ከነበረብን የህልውና ትግል ጎን ለጎን በብዙ ጥረት ከ4.8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ በምርት ለመሸፈን ዝግጅት እንደተደረገ በመግለጽ በዚህ አመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ዛሬ ከ324 የሜካናይዜሽን ትራክተር ለአርሶአደሮች መስጠቱን የገለጹት የክልሉ የግብርና ቢሮ ሀላፊው ዶ/ር ሀይለማርያም ከፍያለው ናቸው። ሀላፊው አክለውም ግብርናውን በማዘመን በቀጣይ የ2014 መጨረሻዎች 700 ትራክተሮችን እንደሚያቀርቡ በመግለጽ በቀጣይ አምስት አመታት ከ26,000 ትራክተሮች በላይ ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ አቅዶ እየሰራ እንደሆ ገልጸዋል።

T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja