Get Mystery Box with random crypto!

በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ፍቅረኛዋ ከድር ሀሰን ፍርድ ቤት ቀረበ! የአ/አ ፖሊ | ETHIO-MEREJA®

በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ፍቅረኛዋ ከድር ሀሰን ፍርድ ቤት ቀረበ!

የአ/አ ፖሊስ መርማሪ ከ15 ቀን በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በሞሴ ሆቴል ከ8ኛ ፎቅ ህይወቷ አልፎ ስለተገኘችው በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል ፍቅረኛዋ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ ሰፊ የምርመራ ስራ እያከናወነ መሆኑን ለችሎቱ አስታውቋል።

የሟች የአሟሟት ሁኔታን ለማጣራት ለአስከሬን ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆ ውጤት እየተጠባበቀ መሆኑን የገለጸው መርማራ ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማቅረብ እንዲያስችለው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪ ከድር ሀሰን በበኩሉ ከጂማ መተው በሆቴል እንደነበሩ ገልጾ ሟች ሀናን መሐመድ የሚወዳት ፍቅረኛው መሆኗንና ህይወቷ እስካለፈበት ሰዓት በመካከላቸው ምንም አይነት ጸብም ሆነ ጭቅጭቅ እንደሌለ ለፍርድ ቤት አብራርቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰውን ወሬ በተሰማ ቁጥር በየጊዜው እየተጠራሁ እጠየቃለው እውነቱ ግን ሀናን የማፈቅራት ሚስቴ ናት እሷ ነጋዴ ናት ዕቃ ገዝቼ እንድመጣ አዛኝ በሰላም ተነጋግረን ፊቴን ታጥቤ ከሆቴሉ በደረጃ በኩል ነው የወረድኩት ስወጣ ባለቤቴ ደህና ነበረች ወጥቼ ሄጄ 2:00 ሰዓት ላይ በስልክ ደውላ በአስቸኳይ ተመለስ አለቺኝ ከዛ ስልኩን ዘጋች እኔም ለሆቴሉ ማናጀር ደውዬ ምን እንደሆነች እንዲጠይቅለኝ ነገርኩት በኋላ ላይ የሆቴሉ ማናጀር ደውሎ ለኔ መንገር ፈርቶ ደህናት ፈጥነህ ና አለኝ ከዛ እሷን ወደ ቤተዛታ ወስደዋት ነበር ቤተዛታ ስደርስ ህይወቷ አልፎ አገኘኋት ወዲያው ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ እንዲያጣሩልኝ አመለከትኩ ሲል ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ እራሴን አጠፋለው እያለች ትናገር እንደነበር የገለጸው ተጠርጣሪ በማላታይን እራሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ ሞክራ እንደነበር ቤተሰቦቿ እንደሚያውቁ ለችሎቱ አስረድቷል።

በዕለቱ ሆቴል ውስጥ የተፈጠረውን ሁኔታ ከሆቴሉ ካሜራ ላይ የተቀሳቃሽ ምስል አይተው ማጣራት እየተቻለ እኔ ታስሬ የምወዳትን የሚስቴን አስከሬን ተቀብዬ መቅበር አልቻልኩም ሲል ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

በፖሊስ በኩል የተቀሳቃሽ ካሜራ ማስረጃ እንደተቀበለና እንዳልተቀበለ ከፍርድ ቤቱ ለተነሳ ጥያቄ አለመቀበሉንየገለጸው መርማሪው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚቀበል ገልጿል።

ጉዳዩን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተጠርጣሪ የወንጀል ተሳትፎ ተለይቶ እንዲቀርብ ትዛዝ በመስጠት ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ የ 11 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።

የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

Via Tarik Adugna
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja