Get Mystery Box with random crypto!

መልካም ዜና! በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል የኢፌዴሪ ጠ/ | ETHIO-MEREJA®

መልካም ዜና!
በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመረቀ።

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራ የሚገኝው የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ ብቁ የጤና ተቋማት በመገንባት ተመጣጣኝና ፍትሀዊ የጤና አገልግሎትን ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው በአሁን ሰአት ለምርቃት የበቃው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የተሰራው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ቀድሞ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው ተገልጿል።

በአጠቃላይ በሳምንት ለ240 ዜጎች አገልግሎት የመስጠት አቅም እንዳለው ተነግሯል። በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ዜጎች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል የተባለለት ማዕከሉ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች በነፃ አገልግሎቱን በመስጠት ተስፋ እንደሚሆንም ተጠቁሟል። ማዕከሉ አለም አቀፍ ደረጃውን ያሟላ የህንጻ ግንባታን ይዞ ተገንብቷል።

T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja